መንግሥቲቱ ድል ትቀዳጃለች!
ምዕራፍ 18
መንግሥቲቱ ድል ትቀዳጃለች!
1. (ሀ) የሰው ዘር የወደፊት ሁኔታ ጥሩ እንደሚሆን ትምክህት ሊኖረን የሚችለው በምን ምክንያት ነው? (ለ) ምድርን ለሚያጠፉት አርማጌዶን ምን ማለት ይሆናል?
የሰው ዘር ከዚህች ምድር ይደመሰስ ይሆን? በጭራሽ። ለዚህም ምክንያቱ መንግሥቲቱ ነች። ምክንያቱም የሰይጣንን ምድራዊ ድርጅቶችና ጨቋኝ ሥርዓቶቹን ለመደምሰስ መንግሥቲቱ በምትመጣበት ጊዜ እርምጃ የሚወስደው “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” የሆነው በዙፋን ላይ የተቀመጠው ኢየሱስ ነው። ምድርን ሊያጠፏት የተነሡት ኃይላት ራሳቸው አርማጌዶን ላይ ይጠፋሉ። — ራእይ 11:15, 18፤ 14:19, 20፤ 19:11–16
2, 3. (ሀ) የሶፎንያስ ትንቢት ምን ማስጠንቀቂያ ያሰማል? (ለ) ከጥፋት ለመዳን የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?
2 አምላካችን ይሖዋ አርማጌዶን ላይ የሚያደርገውን በጣም ነቅተን መጠበቅ እንዳለብን አስጠንቅቆናል።
“መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፣ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ ይላል እግዚአብሔር።”
ይሁን እንጂ ከጥፋቱ የሚተርፉ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ! በቀጣዮቹ የትንቢቱ ቃላት ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ እነዚህን ሰዎች ማዘጋጀት ጀምሯል።
“በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ሶፎንያስ 3:8, 9
ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።” —3 ከጥፋቱ ከሚተርፉ አንዱ ትሆናለህን? ‘የይሖዋን ስም ከጠራህ ልትሆን ትችላለህ።’ ታዲያ የይሖዋን ስም መጥራት የምትችለው እንዴት ነው? ለውጥ አድርገህ “ንፁሕ ልሳን” በመያዝ ነው፤ የሚያነጻውን የመንግሥቱን ምሥራች ወደ ልብህ በማስገባትና ምሥራቹ የሚጠይቅብህን ነገር በመፈጸም ነው። (ማርቆስ 13:10) በክርስቶስ በኩል አምላክ ያደረገውን ዝግጅት አምንህ በመቀበል ጴጥሮስ ከ19 መቶ ዘመናት በፊት ለገዛ ራሱ ሕዝብ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ መከተል ይኖርብሃል:- “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ . . . ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።” — ሥራ 3:19
4, 5. (ሀ) ከይሖዋ ጋር ጥብቅ ቅርርብ ሊኖርህ የሚችለው እንዴት ነው? (ለ) ‘ለንፁሕ ልሳን’ የታዛዥነት ምላሽ የምትሰጠው እንዴት ነው?
4 ልክ እንደ ኢየሱስ አንተም የሰይጣን ዓለም ክፍል አለመሆንህን ማሳየት ይኖርብሃል። (ዮሐንስ 17:14, 16) በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራስህን ለይሖዋ በመወሰንና ይህንንም ለማሳየት በውኃ በመጠመቅ ከይሖዋ አምላክ ጋር የተቀራረበ ዝምድና ለመመሥረት ትችላለህ። (1 ጴጥሮስ 3:21) በምድር ላይ ካሉት ከተደራጁት የአምላክ ሕዝብ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ አምላክን ስታገለግል ይህን የቀረበ ዝምድና ለማዳበር መጣር ይኖርብሃል። ከእነርሱ ጋር በመሆን ባለህ አጋጣሚ “ይህንን የመንግሥት ምሥራች” ለሚሰሙህ ሁሉ በማስታወቁ ሥራ ለመካፈል ትፈልጋለህ። — ማቴዎስ 24:14፤ ሮሜ 10:10–18፤ ዕብራውያን 13:15
5 ለ“ንፁሕ ልሳን” ማለትም ለመጽሐፍ ቅዱሱ እውነት ምላሽ የምትሰጥ ሰው ነህን? ከሆነ በይሖዋ ላይ ሙሉ ትምክህት ጣል። እርሱ “ኃያል ነውና ያድናል።” — ሶፎንያስ 3:17 አዓት፤ ኢሳይያስ 12:2–5
6. ዮሐንስ ምን ጥሩ ምክር ሰጥቷል? ይህስ ምን እንድናደርግ ያበረታታናል?
6 ለይሖዋና ለጽድቁ ያለህን ፍቅር እያሳደግህ በሄድህ መጠን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችም ጋር ተስማምተህ
መኖር ያስፈልግሃል። ሐዋርያው ዮሐንስ የሚከተለውን ጠቃሚ ምክር ሰጥቷል:-“ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፣ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።” (1 ዮሐንስ 2:15–17)
“ለዘላለም”! ይህ ተስፋ በሰይጣን ክፉ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ውስጥ ስንኖር በቅንዓት የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ አያነሣሣንምን? በእነዚህ “የመጨረሻ ቀኖች” ውስጥ በምድር ላይ “በታማኝና ልባም ባሪያ” ወደ ተወከለችው የይሖዋ ድርጅት እንድንጠጋ አያበረታታንምን? — ማቴዎስ 24:45–47
ግዙፍ ሥራ
7. ከአርማጌዶን በኋላ ሳይጠፋ የሚቀረው ምንድን ነው?
7 የአርማጌዶን ጦርነት ጥላ ሲገፈፍ የምትታየው የይሖዋ ድርጅት እርሱ በሚመራት በየትኛውም መንገድ ለማገልገል ዝግጁ ሆና በዚሁ ምድር ላይ ትገኛለች። እኛም በግለሰብ ደረጃ በዚያ ለመገኘት የምንበቃ ያድርገን! — ሶፎንያስ 2:3፤ መዝሙር 25:8, 9, 20
8. (ሀ) በዚያን ጊዜ የአምላክን ሥራ ለማከናወን የሚያስፈልገው ምንድን ነው? (ለ)የአምላክ ሕዝቦችስ ለዚያ ቀደም ብለው የሚዘጋጁት እንዴት ነው?
8 የአምላክ ሕዝብ የጸዳችውን ምድር አስውበው እውነተኛ “የአምላክ ገነት” ለማድረግ የሚደቀንባቸውን ግዙፍ ሥራ ለማከናወን በንጉሣዊ መንግሥት ሥር እንደተደራጁ መቀጠል ያስፈልጋቸዋል። (ከሕዝቅኤል 31:8 ጋር አወዳድር።) በዚህ ሥራ አንተም ለመሳተፍ ትፈልጋለህን? ይህንን ሥራ ለማከናወን የፈቃደኝነት መንፈስና ከአምላክ የሚገኝ ኃይል ያስፈልጋል። በዛሬው ጊዜ ‘ይህንን የመንግሥት ምሥራች በምድር ሁሉ ላይ’ በመስበክ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያሳዩት ዓይነት ቅንዓት ያን ጊዜም ያስፈልጋል። ሰው ሁሉ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ” ሲል የተናገረውን የንጉሡን ምሳሌ በመከተል ከልብ የሚሠራ መሆን ያስፈልጋል። — ዮሐንስ 5:17፤ 4:34
9. (ሀ) በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት ሥራ ይኖራል? (ለ) ይህ ሥራ አሰልቺ እንደማይሆን የሚጠቁመውስ ምንድን ነው?
9 በመላዋ ምድር የቤት ሥራ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ ምንም አያጠራጥርም። ሆኖም ግን ቆሻሻ ሰፈሮች ያሉባቸው አስቀያሚ ከተሞች አይቆረቆሩም። ከዚህ ይልቅ ገነት መሰል በሆኑ ስፍራዎች የተከበቡ ተፈጥሮአዊ ውበት የተላበሱ የቤተሰብ መኖሪያዎች ይሠራሉ። አዎን፣ ብዙ ሥራ ይኖራል፤ አስደሳች የሆነ፣ ስሜትን የሚቀሰቅስ፣ ውጤት ያለውና አመርቂ። ስለዚህ ዓይነቱ ሥራ ንጉሥ ሰለሞን:- “ለሰው ሁሉ በድካሙ ከመብላትና ከመጠጣት መልካሙንም ከማየት የተሻለ ነገር የለም” ብሏል። — መክብብ 3:12, 13 አዓት፤ ኢሳይያስ 65:17, 21–25
10. ራእይ 21:1–4 በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታዎች ይኖራሉ ይላል?
10 የጌታ “ሌሎች በጎች” ሥራቸውን የሚያከናውኑት በምን ዓይነት ሁኔታዎች ሥር ይሆናል? (ዮሐንስ 10:16) ራእይ ምዕራፍ 21 ምን ለመጠበቅ እንደምንችል ይነግረናል። ጥቅሱ ‘ስለ አዲስ ሰማይና ስለ አዲስ ምድር’ ይናገራል። ‘የቀደሙት ሰማያትና የቀደመችው ምድር ስለሚያልፉ’ ከዚያ በኋላ ምግባረ ብልሹ የሆኑ መንግሥታዊ ሥርዓቶች ኅብረተሰቡን አይቆጣጠሩም። በተጨማሪም ዲያብሎስና ረቂቅ የሆነው ተጽዕኖው ይወገዳሉ። ከዚያ ወዲያ “ባሕር” ይኸውም አምላክ የለሽ ዓላማ የሚያራምድ፣ ወዲያና ወዲህ የሚዋዥቅ፣ ግራ የተጋባ የሰው ዘር አይኖርም። በዚህ ፋንታ “አዲስ ምድር” ይኸውም የተረጋጋ ሰብአዊ ኅብረተሰብ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ጥልቅ መሠረት ይሆናል። በዚያም ከንጉሡና በ144,000 አባላት ከተገነባችው “ሙሽራው” ወይም በሌላ አነጋገር ከ“አዲስ ሰማይ” የሚመጡትን መመሪያዎች በታማኝነት ልትከተል ትችላለህ። ይህች መንግሥት የሆነች “ሙሽራ” “ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም” በመሆን ከሰማይ ትወርዳለች። ማለትም በምድር ላይ ወደሚከናወነው የመልሶ ግንባታ ትኩረትዋን ታደርጋለች። በጣም አስደሳች የሆኑ ውጤቶችም ይገኛሉ! ዮሐንስ እንዲህ ይለናል:-
“እነሆ፣ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችን ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።” —11. (ሀ) በሚልዮን የሚቆጠሩትን የጥፋቱን ተራፊዎች ምን ታላቅ ተስፋ ይጠብቃቸዋል? (ለ) አምላክ ምድርን በሕዝብ የሚሞላት እንዴት ነው?
11 በዚህ ታላቅ ተስፋ ውስጥ “ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም” የሚል ቃል የተካተተ መሆኑን ልብ በል። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ “አዲስ ምድር” በረከቶች ለመግባት ‘ከታላቁ መከራ’ በሕይወት እንደሚያልፉ ይጠበቃል። (ራእይ 7:9, 14) ውሎ አድሮ ግን በዚህች ምድር ላይ በመንግሥቲቱ ሥር ሕይወት የሚያገኙት ብዙ ሺ ሚልዮን፣ አዎን፣ በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይሆናሉ። “በቢልዮን የሚቆጠሩ” የምንለው ለምንድን ነው? በኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ ከደረሰ በኋላ ይሖዋ በሕይወት ለተረፉት ጻድቃን “ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት” በማለት ትእዛዝ ሰጥቷቸው ነበር። ይህ ነገር ከአርማጌዶን በኋላ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ ሰብአዊ ጋብቻ እንደሚኖርና ጽድቅ በሰፈነበት ሁኔታ ልጆች እንደሚወለዱ ፍንጭ ይሰጣል። (ዘፍጥረት 9:1, 7፤ 10:1–32፤ ማቴዎስ 24:37) ይሁን እንጂ አምላክ በዚያን ጊዜ ‘ምድርን በሰዎች ለመሙላት’ የሚጠቀምበት ዋነኛው መንገድ ይህ አይሆንም። ታዲያ አምላክ የመጀመሪያውን ዓላማውን ለማሳካት ምድራችንን የሚሞላት እንዴት ነው? (ዘፍጥረት 1:28፤ ኢሳይያስ 45:18) ታላቁን የትንሣኤ ተአምሩን ብዙ ቢልዮን ጊዜ ደጋግሞ በመፈጸም ነው።
“የሕያዋን አምላክ”
12. ሕዝቡን እንዲገረሙ ያደረገው የትኛው የኢየሱስ ትምህርት ነው?
12 አንድ ጊዜ ኢየሱስ ለተቃዋሚዎቹ እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር:-
“ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን:- እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር
ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።”በአምላክ አመለካከት እነዚህ ታማኝ ሰዎች በሕይወት እንዳሉ ያህል ናቸው፤ ትንሣኤ ያገኛሉ። ሕዝቡ በዚህ ትምህርት ተደንቀው ነበር። — ማቴዎስ 22:31–33፤ ሉቃስ 20:37, 38
13. የሞቱትን ታማኝ “ሌሎች በጎች” በተመለከተ ምን ነገር ሊጠበቅ ይቻላል?
13 ‘የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት’ ሲሉ ስደትን የተቋቋሙት እንደነዚህ ያሉት ታማኞችና ንጹሕ አቋማቸውን እንደያዙ ከአርማጌዶን በፊት የሚሞቱ የ“ሌሎች በጎች” አባላት “አዲስ ምድር” እንደ ጀመረ ብዙም ሳይቆዩ ይነሣሉ ተብሎ ሊጠበቅ ይቻላል። ምናልባት አንተም ራስህ የምታፈቅራቸውን ሰዎች፣ ምናልባትም የአምላክ አገልጋይ የሆኑ ዘመዶችህን በሞት ተነጥቀህ ይሆናል። እነዚህን ከሞት ሲነሡ መቀበሉና ይሖዋ ሉዓላዊነቱን ለማረጋገጥ ስለ ወሰደው ታላቅ እርምጃ ለእነርሱ ማውራቱ እንዴት የሚያስደስት ይሆናል! — ዕብራውያን 11:35
14. በዮሐንስ 5:28, 29 እና በራእይ 20:11–13 ላይ ምን አስደናቂ ተስፋ ተገልጿል?
14 ይሁን እንጂ ባለፉት 6,000 ዓመታት የሞቱት ሌሎቹ የሰው ዘሮችስ ምን ይሆናሉ? ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “[በመታሰቢያ መቃብር አዓት] ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ . . . ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።” (ዮሐንስ 5:28, 29) “ሙታንም፣ ታላላቆችና ታናናሾች” በአምላክ የፍርድ ዙፋን ፊት ለመቆም ከመቃብር ይወጣሉ። — ራእይ 20:11–13
15. የፍርድ ቀን አስፈሪ የማይሆነው ለምንድን ነው?
15 ያ ጊዜ ከሞት ለሚነሡት ሰዎች አስፈሪ ይሆንባቸዋልን? ሃይማኖቶች ስለ መጨረሻው የፍርድ ጊዜ በሰዎች አእምሮ ላይ የሚቀርጹት ሥዕል ይህን የመሰለ ቢሆንም ያ ሰዓት በጣም የሚያስደስት ይሆናል። እንደዚያ የምንልበት ምክንያት ከሞት የሚነሡ ሰዎች የሚዳኙት ቀደም ሲል በሠሩት የተሳሳተ ሥራ መሠረት ሳይሆን በአምላክ መንግሥት ውስጥ ከገቡ በኋላ በሕይወት ለመኖር የሚያበቁትን የጽድቅ ትእዛዛት ለማክበር ባላቸው ፈቃደኝነት መሠረት ስለሚሆን ነው? (ከሮሜ 6:7 ጋር አወዳድር።) ከአምላክ ጋር ሙሉ በሙሉ ለመታረቅ በሚያደርጉት ጥረት እነርሱን ለማገዝ ማንኛውም ነገር ይደረጋል። መንግሥቲቱ በምታደራጀው ሥርዓት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ሰፊ የትምህርት ዘመቻ ይካሄዳል።
16. (ሀ) “መጻሕፍት” የተባሉት ምንድን ናቸው? (ለ) ‘በአዲሲቱ ምድር’ ላይ የሚሰጠው ትምህርት እጅግ የላቀ የሚሆነው ለምንድን ነው?
16 “መጻሕፍት” ይከፈታሉ። እነዚህ መጻሕፍት ከሞት የሚነሡት ራእይ 20:12) “በአዲሱ ምድር” ውስጥ በይሖዋና እርሱ በሾመው ንጉሥ የበላይ ተቆጣጣሪነት የሚካሄዱት ትምህርት መስጫ ተቋሞችና ፕሮግራሞች የሰይጣን ዓለም ካዘጋጀው ከማንኛውም ነገር ይበልጣሉ።
ሰዎች ለዘላለም ለመኖር የሚያበቋቸውን “ሥራዎች” መፈጸም ይችሉ ዘንድ እነርሱን ለመርዳት ታትመው የሚወጡ መመሪያዎች ይሆናሉ። (እጅግ ብዙ ሰዎች” የሚዘንቡላቸው በረከቶች
17. ከጥፋቱ ተርፈህ ወደ “አዲሲቱ ምድር” ብትገባ ምን ማድረግ ያስፈልግሃል?
17 ይሁን እንጂ ከአርማጌዶን በሕይወት ከሚተርፉት “እጅግ ብዙ ሰዎች” አንዱ ከሆንክ በዚህ መግለጫ ላይ የአንተ ቦታ ምን ይሆናል? ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ በኩል ሕያዋን ይሆናሉ” ብሏል። (1 ቆሮንቶስ 15:22) አንተም ብትሆን ክርስቶስ በ1,000 ዓመት ግዛቱ ውስጥ የሰውን ዘር ወደ ፍጽምና ለማድረስ ጥቅም ላይ የሚያውለው ቤዛ ያስፈልግሃል። ስምህ “በሕይወት መጽሐፍ” እንዲጻፍ የሚያስችሉ ‘ሥራዎችን’ በታማኝነት ለመፈጸም፣ በሺው ዓመት ግዛት በሚከፈቱት “መጻሕፍት” የሚሰጠውን ትምህርት ማግኘት ያስፈልግሃል።
18. የትኛው የመንግሥቲቱ መርሐ ግብር ልዩ ደስታ ያመጣልናል?
18 በአሁኑ ጊዜ ፍጹም ያልሆነው አንጎልህ መቅሰምና መያዝ የሚችለው እውቀት ከቅምጥ ችሎታው ውስጥ እጅግ በጣም ትንሹን ብቻ ነው። ምናልባት ‘ምነው ማስታወስ በቻልኩ!’ ብለህ ተናግረህ ይሆናል። ለክርስቶስ መሥዋዕት የቱን ያህል አመስጋኝ መሆን ይገባሃል! የመንግሥቱ መርሐ ግብር አካላዊ ሕመሞችንና ሥቃዮችን በማስወገድ የሰውን ዘር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ብቻ ሳይሆን አስደናቂ ፍጥረት የሆነው የሰው አንጎልም ለማጥናትና እውቀትን ለመሰብሰብ፣ በዚያ እውቀት ላይ ለመመራመርና ከሁሉም በላይ የአምላካችንን የይሖዋን ታላላቅ ባሕርዮች ሙሉ በሙሉ ለመረዳትና ለማድነቅ እንዲችል የፍጽምና ደረጃ ላይ እንዲደርስም ያደርጋል። የባቤል ግንብ ሲሠራ የሰው ቋንቋ በመደበላለቁ ምክንያት የተፈጠሩ የቋንቋ ድንበሮችም ይፈርሳሉ። ሁሉም የሰው ዘር ሶፎንያስ 3:9 እንደሚያመለክተው አንድ ሆኖ ይሖዋን በአንድነት ለማምለክ አንድ ቋንቋ ይማራል።
19. የመንግሥቲቱ ተገዢዎች ከየትኛው ተስፋ ነው ተካፋይ የሚሆኑት?
19 ፍጹም የሚሆነው የሰው ልብም በአምላክና በጎረቤት ፍቅር የሚገፋፋ ይሆናል። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ አድናቂ ለሆኑት ሕዝቦቹ የሚከተለውን መናገሩ የሚያስገርም አይሆንም:-
“እነሆ፣ አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፣ ወደ ልብም አይገቡም። ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ ለዘላለም ሐሤት አድርጉ፤ እነሆ፣ [አዲሲቱን] ኢየሩሳሌምን ለሐሤት፣ ሕዝብዋንም ለደስታ እፈጥራለሁና። እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።” (ከክርስቶስ ጋር በመንግሥቱ አብረው የሚገዙት 144,000ዎቹ የሚኖራቸው ከፍተኛ ደስታና ሐሤት በምድር በሚኖሩት በቢልዮን የሚቆጠሩ የመንግሥቱ ተገዥዎች ላይ ይንጸባረቃል፤ ምክንያቱም እነርሱም ወደ ሰብአዊ ፍጽምና ለመድረስ በየጊዜው እየተሻሻሉ ይሄዳሉ።
የይሖዋ ስም ለዘላለም ይቀደሳል
20. (ሀ) 1,000 ዓመቱ ቶሎ የሚያልፈው ለምንድን ነው? (ለ) ዳዊት ይሖዋን እንዴት ብሎ ባረከው? (ሐ) አንተስ ተመሳሳይ የምስጋና ቃላት ለመናገር ትገፋፋለህን?
20 በይሖዋ አመለካከት አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ሆኖ ሽው ብሎ ያልፋል። በግንባታው ሥራ ለተጠመደው የሰው ዘርም ቢሆን ጊዜው አጭር መስሎ ይታያል። (2 ጴጥሮስ 3:8) ከዚህም በተጨማሪ ከሌሎች ጋር ተገናኝቶ አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ፣ ለጤና ጠቃሚ የሆነ እንቅስቃሴ ለማድረግና በሙዚቃና በሌሎች ጥበቦች ለመደሰት እንዲሁም በታላቁ ፈጣሪያችን አምልኮ ለሁልጊዜው ለመካፈል የሚያስችሉ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ ለመገመት እንችላለን። ዳዊት ለመቅደሱ አምልኮ ዝግጅት ሲያደርግ እንደሚከተለው በማለት ይሖዋን እንደባረከ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜም ሁሉም ሰው ይሖዋን ይባርካል:-
“አቤቱ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፣ ክብርም፣ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ መንግሥት የአንተ ነው፣ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ። ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፣ አንተም 1 ዜና. 29:11–13
ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ለማድረግ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው። አሁንም እንግዲህ፣ አምላካችን ሆይ፣ እንገዛልሃለን፣ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።” —21. (ሀ) ክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛቱን የሚደመድመው እንዴት ነው? (ለ) በዚያን ጊዜ መንግሥቲቱ ምን ምን ነገር አጠናቃ መሆን ይኖርባታል?
21 ከዳዊት የሚበልጠው ክርስቶስ ኢየሱስ ከዚህ እፁብ ድንቅ ከሆነ የምስጋና መግለጫ ጋር በመስማማት ሐዋርያው ጳውሎስ ወደፊት የሚሆነውን በማስመልከት እንደሚከተለው ሲል የተናገረውን እርምጃ በመውሰድ የሺህ ዓመቱን የሰላምና የግንባታ ግዛቱን ይደመድማል:-
“በኋላም፣ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትን [ተቃዋሚ መንግሥታትን] ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፣ ፍጻሜ ይሆናል።”
የአምላክ አገዛዝ ይሖዋን ለሚያመልኩት ዘላለማዊ ጥቅሞችን ለማምጣት በቂ ኃይል ያለው ትክክለኛ ዓይነት መስተዳድር መሆኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይረጋገጣል። በመንግሥቲቱ ጥሩ አስተዳደር ሥር በአዳም ምክንያት የመጣው ሞት ስለሚወገድ ሁሉም ሰው “በክርስቶስ” ሕያው ይደረጋል። በዚህም ምክንያት በዚያን ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ‘ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጥተው ለአምላክ ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት ይደርሳሉ።’ — ሮሜ 8:21፤ 1 ቆሮንቶስ 15:22–28
22. (ሀ) ከዚያ በኋላ ምን አጭር የፈተና ጊዜ ይቀጥላል? (ለ) ኢየሱስ ምን ለማረጋገጥ የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል?
22 ፍጹም የተደረገው የሰው ዘር ዓለም ለይሖዋ ንግሥና ታማኝ መሆኑና አለመሆኑ ይፈተን ዘንድ ሰይጣን ለጥቂት ጊዜ ከጥልቁ ይፈታል። ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ዲያብሎስን ለመከተል ይመርጡ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ወዲያውኑ ፍርድ ይፈጸምባቸዋል። የአምላክ “ሴት” “ዘር” የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ የቀድሞውን እባብ ራስ በመቀጥቀጥ የአምላክን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የመጨረሻውን እርምጃ ይወስዳል። እርሱንና ጭፍሮቹን ጨርሶ ስለሚደመስሳቸው የሚጠፉበት እሳት “ለዘላለም ራእይ 20:7–10፤ ዘፍጥረት 3:15
ቀንና ሌሊት” እንደሚነድ ያህል ይሆናል። አምላክ በፍጥረቶቹ ላይ ባለው የሉዓላዊነት መብት ላይ በኤደን የተነሣው ታላቁ ጥያቄ መልሱ ታይቷል፣ ተሞክሯል፤ ከዚያ በኋላ ለዘላለሙ እልባት ያገኛል። —23. (ሀ) የአምላክን ተስፋዎች ወደኋላ መለስ ብሎ ማስታወሱ ምን እንድናደርግ ሊያንቀሳቅሰን ይገባል? (ለ) ‘የአምላክ መንግሥት መጥታ’ ለማየት መፈለግ የሚኖርብን ለምንድን ነው?
23 “የዘላለም ንጉሥ”፣ ሉዓላዊ ገዥያችን፣ ታላቁ ፈጣሪ ይሖዋ የሰጠንን አስደናቂ ተስፋዎች መለስ ብለን ስንመለከታቸው ልባችን በምስጋና ተሞልቶ ስሙን ለማወደስ አንገፋፋምን? በጰንጠቆስጤ ቀን አንዳንዶች “ስለ አምላክ አስደናቂ ሥራዎች” ለመናገር እንደተገፋፉ ሁሉ እኛም ስለ “ነገሥታት ንጉሥ” እና ስለ መሲሐዊው መንግሥት ለመናገር አንገፋፋምን? (ሥራ 2:11፤ ራእይ 15:3፤ 19:16) “መንግሥትህ ትምጣ” ብለን ወደ ሰማዩ አባታችን ለመጸለይ አንገፋፋምን? (ማቴዎስ 6:9, 10) አዎን፣ የሰይጣንን ሥራዎችና ድርጅቱን ከምድር ገጽ ጠራርጋ ለመደምሰስ መንግሥቲቱ “ትምጣልን”። አዎን፤ የሰው ዘር በሙሉ ትክክለኛ መስተዳድር እንዲያገኝ “ትምጣልን”። አዎን፤ ገነት እንደገና እንድትቋቋም፣ ሙታን እንዲነሡና ፈቃደኛ የሆኑ የሰው ልጆችን ወደ ሰብዓዊ ፍጽምና የሚያደርሰውን የሺ ዓመት ግዛት ለመዘርጋት “ትምጣልን”። አዎን፤ አቻ የለሹ የይሖዋ ስም ለዘላለም እንዲባረክ መንግሥቲቱ “ትምጣልን”።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 180, 181 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በአዲሱ ምድር ውስጥ በጽድቅ የሚወለዱት ሕፃናት በዛሬው ጊዜ በቤተሰቦች ላይ የሚደርሱት መከራዎች አይደርሱባቸውም