ጥናት 13
የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
ኢሳይያስ 48:17
ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ፣ ትምህርቱ ከሕይወታቸው ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንዲሁም የተማሩትን ነገር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስተውሉ እርዳቸው።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
-
ስለ አድማጮችህ አስብ። የምታቀርበው ትምህርት ለአድማጮችህ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ቆም ብለህ አስብ፤ በተለይ እነሱን የሚጠቅማቸው የትኛው ነጥብ እንደሆነ ለማሰብ ሞክር።
-
የትምህርቱን ጠቀሜታ በንግግርህ ላይ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ከንግግርህ መጀመሪያ አንስቶ ሁሉም አድማጮች ‘ይህማ ለእኔ ነው’ ብለው እንዲያስቡ በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን አቅርብ። እያንዳንዱን ዋና ነጥብ ስታብራራ፣ ተግባራዊ መሆን የሚችልበትን መንገድም ግለጽ። በደፈናው ከመናገር ይልቅ ነጥቡ ቁልጭ ብሎ እንዲታይ አድርግ።