ጥናት 7
ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
-
አስተማማኝ የመረጃ ምንጮችን ተጠቀም። የምትናገረው ሐሳብ በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ይሁን፤ የሚቻል ከሆነ ጥቅሱን በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብብ። ሳይንሳዊ መረጃ፣ የዜና ዘገባ፣ ተሞክሮ ወይም ሌላ መረጃ የምትጠቅስ ከሆነ ምንጩ አስተማማኝና ጊዜ ያላለፈበት መሆኑን አስቀድመህ አረጋግጥ።
-
የመረጃ ምንጮችን በአግባቡ ተጠቀም። ጥቅሶችን በዙሪያቸው ካለው ሐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መልእክት እንዲሁም “ታማኝና ልባም ባሪያ” ካዘጋጃቸው ጽሑፎች ጋር በሚስማማ መንገድ አብራራ። (ማቴ. 24:45) ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን የምትጠቅሰው ከጽሑፉ መልእክት ወይም ከጸሐፊው ሐሳብ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን ይኖርበታል።
-
መረጃውን መሠረት በማድረግ አስረዳ። አንድ ጥቅስ ካነበብክ ወይም አንድ መረጃ ከጠቀስክ በኋላ አድማጮችህ የራሳቸው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ለመርዳት ጥያቄዎችን ጠይቅ አሊያም ነጥቡን በምሳሌ አስረዳ።