በፍቅር እርስ በርስ ተስማምቶ መኖር
ምዕራፍ 28
በፍቅር እርስ በርስ ተስማምቶ መኖር
1. (ሀ) የአምላክ ድርጅት አካል ልትሆን የምትችለው እንዴት ነው? (ለ) ከዚያ በኋላ የትኛውን ትእዛዝ መከተል አለብህ?
ስለ ይሖዋ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ ያለህ እውቀትና አድናቆት እያደገ ሲሄድ ይኸው ዓይነት እምነትና ተስፋ ካላቸው ሰዎች ጋር ዘወትር ለመገናኘት ትፈልጋለህ። ይህንንም ስታደርግ የሚታየው የአምላክ ድርጅት አካል ትሆናለህ። ይህም በእርግጥ ክርስቲያናዊ የወንድማማችነት ማኅበር ነው። ከዚያ በኋላ “ለጠቅላላው የወንድማማች ማኅበር ፍቅር ይኑራችሁ ” የሚለውን ትእዛዝ ማክበር ይኖርብሃል። — 1 ጴጥሮስ 2:17፤ 5:8, 9
2. (ሀ) ኢየሱስ ለተከታዮቹ ምን አዲስ ትእዛዝ ሰጣቸው? (ለ) “እርስ በርሳችሁ” የሚለው አነጋገር በግልጽ የሚያሳየው ምንድን ነው? (ሐ) ፍቅር ማሳየቱ የቱን ያህል አስፈላጊ ነው?
2 ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮቹ እርስ በርሳቸው መፋቀራቸው የቱን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አጥብቆ ገልጿል። እንዲህ አላቸው:- “እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ . . . አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ። እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” (ዮሐንስ 13:34, 35) “እርስ በርሳችሁ” የሚለው አነጋገር እውነተኛ ክርስቲያኖች የሆኑት በሙሉ በአንድ ቡድን ወይም ድርጅት ውስጥ እንደሚሰባሰቡ በግልጽ ያሳያል። (ሮሜ 12:5፤ ኤፌሶን 4:25) ይህ ድርጅትም ተለይቶ የሚታወቀው አባሎቹ እርስ በርስ ባላቸው ፍቅር ነው። አንድ ሰው ፍቅር ከሌለው ሌላው ነገር ሁሉ ዋጋ አይኖረውም። — 1 ቆሮንቶስ 13:1-3
3. ክርስቲያን ወንድሞቻችንን ማፍቀሩና በጥሩ ሁኔታ መያዙ በጣም አስፈላጊ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ የሚገልጸው እንዴት ነው?
3 ይህም በመሆኑ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ እንደሚከተሉት ያሉ ማሳሰቢያዎች ይደርሷቸው ነበር:- “በወንድማማች [ዓይነት] መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።” “እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።” “እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።” “እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።” “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን ሮሜ 12:10፤ 15:7፤ ገላትያ 5:13፤ ኤፌሶን 4:32፤ ቆላስይስ 3:13, 14፤ 1 ተሰሎንቄ 5:11, 13፤ 1 ጴጥሮስ 4:8፤ 1 ዮሐንስ 3:23፤ 4:7, 11
አድርጉ፤ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር ተባባሉ።” “እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።” “እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ።” “እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።” —4. (ሀ) ክርስቲያኖች “እርስ በርሳቸው” ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ማፍቀር እንደሚገባቸው የሚያሳየው ምንድን ነው? (ለ) ክርስቲያኖች በተለይ እነማንን መውደድ አለባቸው?
4 እንደዚህ ሲባል ግን እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደ እነርሱ የአምላክ ድርጅት አባሎች የሆኑትን ብቻ መውደድ አለባቸው ማለት አይደለም። ሌሎችንም መውደድ ይኖርባቸዋል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ “እርስ በርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም” በማለት አጥብቆ ያሳስባል። (1 ተሰሎንቄ 3:12፤ 5:15) ሐዋርያው ጳውሎስ ተገቢና ሚዛናዊ የሆነ አስተያየት ሲሰጥ:- “ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰዎች መልካም እናድርግ” በማለት ጽፏል። (ገላትያ 6:10) እንግዲያው ክርስቲያኖች ሁሉንም ሰው፣ ጠላቶቻቸውንም ጭምር፣ መውደድ ያለባቸው ሲሆን ይልቁንም አብረዋቸው የአምላክ ድርጅት አባሎች የሆኑትን መንፈሳዊ ወንድሞቻቸውንና እኅቶቻቸውን ማፍቀር ይኖርባቸዋል። — ማቴዎስ 5:44
5. በፊትም ሆነ በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች በፍቅራቸው እንደታወቁ የሚያሳየው ምንድን ነው?
5 የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በመሀከላቸው በነበረው በዚህ ፍቅር በጣም የታወቁ ነበሩ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው ጸሐፊ ተርቱልያን በተናገረው መሠረት ብዙ ጊዜ ሰዎች ‘እርስ በርሳቸው እንዴት እንደሚዋደዱ ተመልከቱ፤ አንዱ ለሌላው ለመሞት ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ እዩ!’ በማለት ስለ እነርሱ ይናገሩ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ዛሬም በእውነተኛ ክርስቲያኖች መሀከል ይታያል። እንደዚህም ሲባል ግን በእውነተኛ ክርስቲያኖች መሀከል ችግሮች አይነሡም ማለት አይደለም።
አለፍጽምና ያስከተላቸው ውጤቶች
6. እውነተኛ ክርስቲያኖችም ቢሆኑ አልፎ አልፎ እርስ በርስ በደል የሚፈጽሙት ለምንድን ነው?
6 ሁላችንም ከመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ከአዳምና ከሔዋን ያለፍጽምናን እንደወረስን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ተረድተሃል። (ሮሜ 5:12) ስለዚህ ስሕተት መሥራቱ ይቀናናል። “ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለን” ሲል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ያዕቆብ 3:2፤ ሮሜ 3:23) የአምላክ ድርጅት አባሎች ያለፍጽምና እንዳለባቸውና አንዳንድ ጊዜ ትክክል ያልሆነውን እንደሚሠሩ ማወቅ አለብህ። ይህ ሁኔታ በእውነተኛ ክርስቲያኖች መሀከልም እንኳ ችግር ወይም አለመግባባት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
7. (ሀ) ኤዎድያንና ሲንጤኪ “ተስማሙ” ተብሎ እንዲነገራቸው ያስፈለገው ለምንድን ነው? (ለ) በመሠረቱ እነዚህ ጥሩ ክርስቲያን ሴቶች እንደነበሩ የሚያሳየው ምንድን ነው?
7 ለምሳሌ ያህል በጥንቱ የፊልጵስዩስ ጉባኤ ውስጥ የነበሩትን ኤዎድያን እና ሲንጤኪ የተባሉ የሁለት ሴቶችን ሁኔታ እንውሰድ። ሐዋርያው ጳውሎስ:- “በአንድ አሳብ በጌታ እንዲስማሙ ኤዎድያንን እመክራለሁ፤ ሲንጤኪንንም እመክራለሁ” በማለት ጽፏል። ሐዋርያው ጳውሎስ እነዚህ ሁለት ሴቶች “እንዲስማሙ” ያበረታታው ለምንድን ነው? በመሀከላቸው አንድ ዓይነት ችግር እንደነበረ ግልጽ ነው። ችግሩ ምን እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይነግረንም። ምናልባት እርስ በርሳቸው ቅናት አድሮባቸው ሊሆን ይችላል። በመሠረቱ ሲታዩ ግን ሁለቱም ጥሩ ሴቶች ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ ክርስቲያኖች ሆነው ቆይተዋል። ወደ ክርስትና የመጡት ከጳውሎስ ጋር በስብከቱ ሥራ ከመሳተፋቸው ከብዙ ዓመታት በፊት ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ለጉባኤው:- “እንድታግዛቸው እለምንሃልሁ . . . በወንጌል ከእኔ ጋር አብረው ተጋድለዋልና” በማለት ጽፏል። —8. (ሀ) በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ምን ችግር ተፈጠረ? (ለ) በቦታው ብትገኝና ችግሩን ብታይ ኖሮ ምናልባት ምን ብለህ ትደመድም ነበር?
8 አንድ ጊዜ በሐዋርያው ጳውሎስና የጉዞ ጓደኛው በነበረው በበርናባስ መሀከል ችግር ተነሥቶ ነበር። ለሁለተኛው ሚስዮናዊ ጉዞአቸው ሲነሡ በርናባስ የአጎቱን ልጅ ማርቆስን አብሮ ለመውሰድ ፈልጎ ነበር። ይሁን እንጂ ማርቆስ በመጀመሪያው ሚስዮናዊ ጉዞአቸው ወቅት ትቷቸው ወደ ቤቱ ተመልሶ ስለነበረ ጳውሎስ አሁን ማርቆስን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም። (ሥራ 13:13) መጽሐፍ ቅዱስ “እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ” ይላል። (ሥራ 15:37-40) ይህ ይሆናል ብለህ ልታስበው ትችላለህን? አንተ በቦታው ተገኝተህ ቢሆንና የተፈጠረውን “መከፋፋት” ብታይ ኖሮ ሁለቱም ባሳዩት ጠባይ ምክንያት የአምላክ ድርጅት አባሎች አይደሉም ብለህ ትደመድም ነበርን?
9. (ሀ) ጴጥሮስ ምን ኃጢአት ሠራ? እንደዚያ ለማድረግ የገፋፋውስ ምንድን ነው? (ለ) ጳውሎስ የሆነውን ነገር በተመለከተ ጊዜ ምን አደረገ?
ገላትያ 2:11-14) ሐዋርያው ጳውሎስ ጴጥሮስ ያደረገውን ካየ በኋላ በቦታው በነበሩት ሁሉ ፊት ተገቢ ያልሆነ ድርጊቱን አወገዘ። አንተ ጴጥሮስ ብትሆን ኖሮ እንዴት ይሰማህ ነበር? — ዕብራውያን 12:11
9 በሌላም ጊዜ ሐዋርያው ጴጥሮስ ስሕተት ሠራ። ከአሕዛብ የመጡ ወንድሞቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ዝቅ አድርገው የሚመለከቱ አንዳንድ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች እንዳይነቅፉት ፈርቶ ከአሕዛብ ከመጡት ክርስቲያኖች ተለየ። (ችግሮችን በፍቅር መፍታት
10. (ሀ) ጴጥሮስ በታረመ ጊዜ ምን አለ? (ለ) ከጴጥሮስ ምሳሌ ምን ለመማር እንችላለን?
10 ጴጥሮስ በጳውሎስ ላይ ሊቆጣ ይችል ነበር። በሌሎች ፊት ለምን ያርመኛል በማለት ስሜቱ ሊጐዳ ይችል ነበር። ሆኖም እንደዚያ አላደረገም። (መክብብ 7:9) ጴጥሮስ ትሑት ነበር። እርማቱን ተቀበለ እንጂ ለጳውሎስ የነበረውን ፍቅር እንዲያቀዘቅዝበት አልፈቀደም። (1 ጴጥሮስ 3:8, 9) በሌላ ጊዜ ጴጥሮስ ለክርስቲያን ወንድሞቹ በጻፈው የማጽናኛ ደብዳቤ ላይ ጳውሎስን እንዴት አድርጎ እንደጠቀሰው ተመልከት:- “የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደሆነ ቁጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ።” (2 ጴጥሮስ 3:15) አዎን፣ ጴጥሮስ ፍቅር ችግሩን እንዲሸፍነው ፈቅዶለታል። የችግሩ መንስዔም ራሱ ነበር። — ምሳሌ 10:12
11. (ሀ) ጳውሎስና በርናባስ በቁጣ ቢገነፍሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው? (ለ) ከምሳሌያቸው እንዴት ልንጠቀም እንችላለን?
11 በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ተነሥቶ የነበረው ችግርስ ምን ሆነ? ይኸኛውም ቢሆን በፍቅር መፍትሔ አግኝቷል ምክንያቱም በሌላ ጊዜ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ጉባኤ ደብዳቤ ሲጽፍ በርናባስ የቅርብ የሥራ ጓደኛው መሆኑን ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 9:5, 6) ምንም እንኳ ጳውሎስ ማርቆስን የጉዞ ጓደኛው አድርጎ ለመምረጥ እንዲጠራጠር ያበቃው ጥሩ ምክንያት ቢኖረውም ይህ ወጣት ከጊዜ በኋላ ብስለት ስላገኘ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎ ለመጻፍ ችሏል:- “ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።” (2 ጢሞቴዎስ 4:11) ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ከሚያሳየው ከዚህ ምሳሌ ጥቅም ለማግኘት እንችላለን።
12. (ሀ) ኤዎድያንና ሲንጤኪ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት አስወግደውታል ብለን ለማሰብ የምንችለው ለምንድን ነው? (ለ) በገላትያ 5:13-15 መሠረት ክርስቲያኖች በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት ማስወገዳቸው በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
12 ታዲያ ኤዎድያንና ሲንጤኪስ ምን አደረጉ? አንዳቸው በሌላዋ ላይ ምንም ዓይነት ኃጢአት ሠርታ ብትሆንም ፍቅር እነዚያን ኃጢአቶች እንዲሸፍን በመፍቀድ በመሀከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት አስወግደውታልን? በመጨረሻው ገላትያ 5:13-15
ምን እንዳደረጉ መጽሐፍ ቅዱስ አይነግረንም። ይሁን እንጂ ከጳውሎስ ጋር በክርስቲያን አገልግሎት ጎን ለጎን ቆመው የሠሩ ጥሩ ሴቶች ስለነበሩ የተሰጣቸውን ምክር በትሕትና ተቀብለውታል ብለን ለማሰብ ምክንያት አለን። የጳውሎስ ደብዳቤ ከደረሰ በኋላ አንዷ ወደ ሌላዋ ሮጣ ስትሄድና ችግራቸውን በፍቅር መንፈስ ሲያስወግዱት ሊታየን ይችላል። —13. ፍቅርን በማሳየት በኩል ይሖዋ ምሳሌ የሚሆነን እንዴት ነው?
13 አንተም በጉባኤው ውስጥ ካለ ሰው ወይም ካሉት ሰዎች ጋር መግባባቱ ከባድ ሆኖ ታገኘው ይሆናል። እውነተኛ የክርስቲያን ጠባዮችን ለማዳበር ገና ብዙ የሚቀራቸው ቢሆንም እንደሚከተለው እያልክ አስብ:- ይሖዋ አምላክ ሰዎችን ለማፍቀር መጥፎ መንገዶቻቸውን በሙሉ እስኪያስወግዱ ድረስ ይጠብቃልን? አይጠብቅም። መጽሐፍ ቅዱስ “ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” ይላል። (ሮሜ 5:8) እኛም ይህንን የአምላክ ምሳሌ መከተልና መጥፎና ሞኝነት የሆኑ ነገሮችን ለሚፈጽሙት ፍቅር ማሳየት ይገባናል። — ኤፌሶን 5:1, 2፤ 1 ዮሐንስ 4:9-11፤ መዝሙር 103:10
14. ሌሎችን ከመንቀፍ ስለመቆጠብ ኢየሱስ ምን ምክር ሰጠ?
14 ሁላችንም ፍጽምና ስለሌለን ሌሎችን ከመንቀፍ እንድንቆጠብ ኢየሱስ አስተምሮናል። እውነት ነው፤ ሌሎች ያጠፋሉ። እኛም እናጠፋለን። “በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ? በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለምን አትመለከትም?” በማለት ኢየሱስ ጠይቋል። (ማቴዎስ 7:1-5) እንደዚህ ያለው ምክር ሁልጊዜ ትዝ የሚለን ከሆነ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ተስማምተን ለመኖር ይረዳናል።
15. (ሀ) በሌሎች ቅር ለመሰኘት ምክንያት ቢኖረንም ይቅር ማለታችን ለምን በጣም አስፈላጊ ነው? (ለ) ኢየሱስ በማቴዎስ ምዕራፍ 18 በሚገኘው ምሳሌው ላይ ይቅር ባይ የመሆንን አስፈላጊነት ያስተማረው እንዴት ነው?
ቆላስይስ 3:13 አዓት) ደግሞም የአምላክን ይቅርታ ለማግኘት ከፈለግን ሌሎችን የግድ ይቅር ማለት እንዳለብን ኢየሱስ ተናግሯል። (ማቴዎስ 6:9-12, 14, 15) ከኢየሱስ ምሳሌዎች በአንዱ ላይ እንደተጠቀሰው ንጉሥ ይሖዋም ብዙ ሺህ ጊዜ ይቅር ብሎናል። ታዲያ እኛስ ወንድሞቻችን ጥቂት ጊዜ ቢበድሉን ይቅር ማለት አንችልምን? — ማቴዎስ 18:21-35፤ ምሳሌ 19:11
15 መሐሪና ይቅር ባይ መሆናችን የግድ አስፈላጊ ነው። እውነት ነው፤ በአንድ ወንድም ወይም በአንዲት እህት ቅር ለመሰኘት ትክክለኛ ምክንያት ይኖርህ ይሆናል። ይሁን እንጂ “ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር ተባባሉ” ሲል መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውን ምክር አስታውስ። ነገር ግን በእነርሱ ቅር ለመሰኘት እውነተኛ ምክንያት እያለህ ሌሎችን ይቅር ማለት ያለብህ ለምንድን ነው? ምክንያቱም “ይሖዋ በነፃ ይቅር ብሎሀል” ሲል መጽሐፍ ቅዱስ ይመልሳል። (16. (ሀ) በ1 ዮሐንስ 4:20, 21 መሠረት ለአምላክ ያለን ፍቅር ለክርስቲያን ወንድሞቻችን ካለን ፍቅር ጋር የተያያዘው እንዴት ነው? (ለ) ወንድምህ በአንተ ላይ ቅሬታ ካለው ምን እርምጃ መውሰዱ አስፈላጊ ነው?
16 ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ፍቅርና ይቅር ባይነት በጎደለው መንገድ እየያዝን በእውነት ውስጥ እንመላለሳለን ለማለት አንችልም። (1 ዮሐንስ 4:20, 21፤ 3:14-16) እንግዲያው በአንተና በሌላው ክርስቲያን ወንድም መካከል ችግር ከተፈጠረ እሱን ፈጽሞ አታኩርፈው። ነገሩን በፍቅር መንገድ አስተካክለው እንጂ ቂም አትያዝ። ወንድምህን ጎድተህ ከሆነ ስሕተትህን ለመቀበልና ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ሁን። — ማቴዎስ 5:23, 24
17. አንድ ሰው ቢበድልህ ማድረግ ያለብህ ተገቢ ነገር ምንድን ነው?
17 ይሁንና አንድ ሰው ቢያዋርድህ ወይም በሌላ መንገድ ቢበድልህስ? መጽሐፍ ቅዱስ “እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ እንደ ሥራውም እመልስበታለሁ አትበል” ሲል ይመክረናል። (ምሳሌ 24:29፤ ሮሜ 12:17, 18) ኢየሱስ ክርስቶስም “ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት” የሚል ምክር ሰጥቷል። (ማቴዎስ 5:39) ጥፊ አካልን ለመጉዳት ሳይሆን ሰውየውን ለማዋረድ ወይም ለማናደድ ታስቦ የሚሰነዘር ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እዚህ ላይ ተከታዮቹን ወደ ጥል ወይም ወደ ክርክር ተስባችሁ አትግቡ ብሎ ማስተማሩ ነበር። “ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ” ከመመለስ ይልቅ ‘ሰላምን ፈልግ ተከተለውም።’ — 1 ጴጥሮስ 3:9, 11፤ ሮሜ 12:14
18. አምላክ ሁሉንም ሰዎች በማፍቀር ካሳየን ምሳሌ ምን መማር ይገባናል?
18 “ለጠቅላላው የወንድማማች ማኅበር ፍቅር ሊኖረን እንደሚገባ” አስታውስ። (1 ጴጥሮስ 2:17 አዓት) ይሖዋ አምላክ ምሳሌውን አሳይቶናል፤ ለማንም አያዳላም። በፊቱ ሁሉም ዘሮች እኩል ናቸው። (ሥራ 10:34, 35፤ 17:26) በመጪው “ታላቅ መከራ” ጊዜ ጥበቃ ተደርጎላቸው ከዚያ የሚተርፉት ሰዎች “ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ” የተውጣጡ ናቸው። (ራእይ 7:9, 14-17) እንግዲያው አምላክ ያደረገውን መከተል አለብን እንጂ ሌሎች ሰዎች ዘራቸው፣ ብሔራቸው፣ በሕብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ቦታ፣ ወይም የቆዳ ቀለማቸው የተለየ ስለሆነ ለእነርሱ የምናሳየውን ፍቅር መቀነስ አይገባንም።
19. (ሀ) እንደ እኛው ክርስቲያን የሆኑትን ማየትና መያዝ የሚገባን እንዴት ነው? (ለ) ምን ታላቅ መብት ሊኖረን ይችላል?
19 በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያሉትን በሙሉ እወቃቸው። እነርሱን ለመውደድና ለማድነቅ ትገፋፋለህ። በዕድሜ የገፉትን እንደ አባቶችና እንደ እናቶች፣ ወጣቶችን እንደ ወንድሞችና እንደ እህቶች አድርገህ ያዝ። (1 ጢሞቴዎስ 5:1, 2) ቤተሰብ መሰል የሆነውና አባሎቹ በፍቅር እርስ በእርስ ተስማምተው በኅብረት የሚኖሩት የሚታየው የአምላክ ድርጅት ክፍል መሆኑ በእውነቱ ታላቅ መብት ነው። ወደፊት እንደዚህ ካለው አፍቃሪ ቤተሰብ ጋር ገነት በምትሆነዋ ምድር ለዘላለም መኖሩ እንዴት ጥሩ ነው! — 1 ቆሮንቶስ 13:4-8
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 233 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በኤዎድያንና በሲንጤኪ መካከል ከተፈጠረው ሁኔታ ምን ለመማር እንችላለን?
[በገጽ 235 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ጳውሎስና በርናባስ እርስ በርሳቸው መከራከራቸው የአምላክ ድርጅት አባላት አልነበሩም ማለት ነውን?
[በገጽ 236 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
እውነተኛ ክርስቲያኖች ቅር ለመሰኘት ምክንያት የሚሆኑትን ነገሮች በፍቅር ይሸፍናሉ
[በገጽ 237 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በአምላክ ድርጅት ውስጥ ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው በእኩልነት እየተያዩ ተስማምተው ለመኖር ፍቅር ይገፋፋቸዋል