ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ አግኝተኸዋል?

ያሉት ሃይማኖቶች ሁለት ዓይነት ብቻ ናቸው ሊባል ይችላል፦ አንዱ ወደ ሕይወት የሚወስድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ወደ ጥፋት የሚወስድ ነው። የዚህ ብሮሹር ዓላማ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ እንድታገኝ መርዳት ነው።

መግቢያ

የአሁኑም ሆነ የወደፊቱ ሕይወታችን፣ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ላይ የተመካ ነው። ስለዚህ አምልኳችን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱ በጣም አስፈላጊ ነው!

ክፍል 1

ሁሉም ሃይማኖቶች እውነትን ያስተምራሉ?

ሃይማኖተኛ የሆኑ ሰዎች የተለያዩ እምነቶች አሏቸው። እነዚህ ሁሉ በእውነት ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ ይችላሉ?

ክፍል 2

ስለ አምላክ እውነቱን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ሃይማኖታዊ እውነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉም ሰው የሚስማማበት መለኪያ አለ?

ክፍል 3

በሰማያት የሚኖሩት እነማን ናቸው?

ባሕላዊ እምነቶች ሰዎች ስለ መናፍስት ባላቸው አመለካከት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ይሁንና እነዚህ እምነቶች ትክክል ናቸው? መጽሐፍ ቅዱስ መልሱን ይሰጠናል።

ክፍል 4

የሞቱ አያት፣ ቅድመ አያቶቻችን ያሉት የት ነው?

ብዙ ሰዎች ሞት የሕይወት ፍጻሜ ሳይሆን በሌላ ዓለም ወዳለ ሕይወት የሚያሸጋግር ድልድይ እንደሆነ ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?

ክፍል 5

አስማትን፣ መተትንና ጥንቆላን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?

መናፍስት ከፍተኛ ኃይል ያላቸው ከመሆኑም ሌላ አደገኞች ናቸው። ያም ሆኖ የእነሱን ኃይል ከልክ በላይ አጋንነን ማየት የለብንም።

ክፍል 6

አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል?

አንዳንድ ሰዎች ሁሉም ሃይማኖቶች አምላክን እንደሚያስደስቱ ይሰማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል?

ክፍል 7

እውነተኛውን ሃይማኖት የሚከተሉት እነማን ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ይረዳሃል።

ክፍል 8

ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ፤ እውነተኛውን ሃይማኖት ያዝ

ኢየሱስ “ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል” ብሏል። ከማን ጎን እንደቆምክ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ክፍል 9

እውነተኛው ሃይማኖት ለዘላለም ይጠቅምሃል!

ይሖዋን የምታመልክ ከሆነ አሁንም ሆነ ለዘላለም ይባርክሃል።