ክፍል 1
‘የሚያስደምም ኃይል ያለው’
በዚህ ክፍል ውስጥ ይሖዋ ኃይሉን ለመፍጠር፣ ለማጥፋት፣ አገልጋዮቹን ለመጠበቅና አንድን ነገር ለማደስ እንደሚጠቀምበት የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንመረምራለን። ‘የሚያስደምም ኃይል’ ያለው ይሖዋ ‘ገደብ የሌለው ብርቱ ጉልበቱን’ እንዴት እንደሚጠቀምበት መረዳታችን፣ ልባችን በድፍረትና በተስፋ እንዲሞላ ያደርጋል።—ኢሳይያስ 40:26
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 5
‘የሰማይና የምድር ፈጣሪ’—ለመፍጠር የሚጠቀምበት ኃይል
ግዙፍ ከሆነችው ፀሐይ አንስቶ ኢምንት እስከሆነችው ሃሚንግበርድ የተባለችው ወፍ፣ የአምላክ ፍጥረታት ስለ አምላክ አስፈላጊ ትምህርት ያስተምሩናል።
ምዕራፍ 7
‘መጠጊያችን የሆነው አምላክ’—ለመጠበቅ የሚጠቀምበት ኃይል
አምላክ ሕዝቡን የሚጠብቀው በሁለት መንገዶች ነው፤ አንደኛው ግን ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ነው።
ምዕራፍ 8
‘ሁሉንም ነገር አዲስ የሚያደርገው’ ይሖዋ—ለማደስ የሚጠቀምበት ኃይል
ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ንጹሑን አምልኮ መልሶ አቋቁሟል። ወደፊትስ ምን ነገር ያድሳል?
ምዕራፍ 10
በኃይል አጠቃቀም ረገድ “አምላክን የምትመስሉ ሁኑ”
አለኝ ብለህ ከምታስበው በላይ ኃይል ወይም ሥልጣን ይኖርህ ይሆናል፤ ይሁንና ይህን ኃይልህን በአግባቡ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?