በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መቅድም

መቅድም

ውድ አንባቢ፦

አምላክ ወዳጅህ እንደሆነ ይሰማሃል? ብዙ ሰዎች ይህ ፈጽሞ የማይታሰብ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንዳንዶች አምላክ በምንም መንገድ ሊቀረብ እንደማይችል አድርገው ያስባሉ፤ ሌሎች ደግሞ ራሳቸውን በጣም ዝቅ አድርገው ስለሚመለከቱ ይህን መብት ሊያገኙ እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል” በማለት ፍቅራዊ በሆነ መንገድ ያበረታታናል። (ያዕቆብ 4:8) እንዲያውም “‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህ እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁ” የሚል ማረጋገጫ ሰጥቶናል።—ኢሳይያስ 41:13

ከአምላክ ጋር እንዲህ ያለ የቅርብ ወዳጅነት መመሥረት የምንችለው እንዴት ነው? ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ልንመሠርት የምንችለው በቅድሚያ ግለሰቡን በሚገባ ስናውቀው ብሎም ልዩ የሚያደርጉትን ባሕርያት ስናደንቅና ከፍ አድርገን መመልከት ስንጀምር ነው። በመሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን የአምላክ ባሕርያትና የተለያዩ ነገሮችን የሚያከናውንበትን መንገድ ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ይሖዋ እያንዳንዱን ባሕርይ የሚገልጥበትን መንገድ በጥሞና ማሰባችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ባሕርያት ፍጹም በሆነ መንገድ ያንጸባረቀው እንዴት እንደሆነ መመርመራችንና እኛም ባሕርያቱን እንዴት ማዳበር እንደምንችል መረዳታችን ወደ አምላክ ይበልጥ እንድንቀርብ ያደርገናል። ይሖዋ ሕጋዊ መብት ያለው ትክክለኛው የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ጌታ መሆኑን እንገነዘባለን። ከዚህም በተጨማሪ ሁላችንም እንደ እሱ ያለ አባት አናገኝም። ኃያል፣ ፍትሐዊ፣ ጥበበኛና አፍቃሪ በመሆኑ ታማኝ ልጆቹን ፈጽሞ አይጥልም።

ይህ መጽሐፍ ይሖዋ አምላክን ለዘላለም እያወደስክ መኖር ትችል ዘንድ ወደ እሱ ይበልጥ እንድትቀርብና ምንጊዜም የማይበጠስ ጠንካራ ዝምድና እንድትመሠርት እንዲረዳህ እንመኛለን።

አዘጋጆቹ