ከሕይወት ለማግኘት የምትፈልገው ምንድን ነው?
ምዕራፍ 23
ከሕይወት ለማግኘት የምትፈልገው ምንድን ነው?
1–6. (ሀ) ከሕይወትህ ከሁሉ የተሻለውን ነገር ለማግኘት ምን ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ይገባሃል? (ለ) አስደሳች ሕይወት እንዲኖርህ በአንድ ዓይነት ሙያ ብልጫ ከማሳየት የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገር ምንድን ነው? (ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳህ የሚችለው ለምንድን ነው?
በወጣትነት ጊዜ ሕይወትህ በአብዛኛው ያለው ከፊት ለፊትህ ነው። መጨረሻው ከአድማስ ባሻገር በሆነ አንድ ቦታ ላይ እንደሚያልቅ መንገድ ሕይወትህም ለረጅም ርቀት ተዘርግቶ ይታይህ ይሆናል። ወዴት ያደርስህ ይሆን?
2 የሕይወት ጎዳና አንዳንድ ያልታሰቡ አስደሳች ነገሮችና ያልጠበቅካቸው አስከፊ ሁኔታዎች ይዞ እንደሚጠብቅህ ጥርጥር የለውም። ይሁን እንጂ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንዳየነው ሕይወትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ እንድትጠቀምበት የሚያስችሉ አንተ ማድረግ የምትችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ጥያቄው:- አስፈላጊውን ጥረት ለማድረግ ፈቃደኛ ነህን? የሚል ነው።
3 ብዙ ወጣቶች ትምህርት ሲጨርሱ ስለሚይዙት ሥራ ያስባሉ። ምናልባት አንተም ስለዚህ ጉዳይ አስበህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት ሥራ ብትሠራ በጥራት ካልሠራኸው እምብዛም እርካታ አያመጣልህም። የሆነው ሆኖ ከዚህ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ሌላ ነገር አለ።
4 ጥሩ መሐንዲስ ወይም ሰዓሊ፣ መካኒክ፣ ሙዚቀኛ፣ ገበሬ፣ አስተማሪ ወይም ሌላ ነገር ሆንክ እንበል። ታዲያ ይህ ሞያህ ሕይወትህ ደስታ የሞላበት እንደሚሆን ዋስትና ይሰጣልን? አይሰጥም። ከዚህ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምን ዓይነት ሰው ይወጣህ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ነው። ብዙ ሰዎች በአንድ ዓይነት ሙያ ጥሩ ሥራ ነበራቸው፤ ይሁን እንጂ የግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ውድቀት ደርሶበታል። በጣም የተከፉ ግለሰቦች ሆነዋል።
5 መጽሐፍ ቅዱስ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። መላው መጽሐፍ ቅዱስ ከፈጣሪያችን የተላኩ ደብዳቤዎችን አሰባስቦ እንደያዘ መጽሐፍ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። ሰማያዊ አባታችን እንደመሆኑ መጠን ደስተኞች እንድንሆን ይፈልጋል፤ እኛም እርሱ የሚነግረንን ለማወቅና ለማድረግ መፈለግ ይኖርብናል። ለብዙዎቹ ችግሮቻችን መፍትሔ እንዲሆኑ የሰጠንን መመሪያዎች ተመልክተናል። መመሪያዎቹ በሙሉ ትክክለኛ መመሪያዎች ናቸው ቢባል እውነት አይደለምን? እርሱ የሰጠን መመሪያዎች ባይኖሩልን ኖሮ ምን ማድረግ እንደሚገባን ወይም ምን ነገር እንደሚበጀን እንዴት እርግጠኞች ለመሆን እንችል ነበር?
6 ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ በዕድሜ ከእርሱ ለሚያንሰው የሥራ ጓደኛው ለጢሞቴዎስ የጻፈውን ነገር ያስታውሰናል። ጢሞቴዎስ ከልጅነቱ ጀምሮ ከቅዱሳን መጻሕፍት በተማረው ነገር ጸንቶ እንዲኖር ጳውሎስ አጥብቆ አሳሰበውና እንዲህ አለ:- “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ፣ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” (2 ጢሞቴዎስ 3:14–17) በሕይወት ውስጥ ጉልበትና ጊዜ ቢጠፋለት የማይቆጭ የትኛውንም ዓይነት ሥራ ለማከናውን ብቻ ሳይሆን ያንን ሥራ ጥሩ አድርገህ ለመሥራት የተሻለ ብቃት የሚኖርህ በአምላክ ቃል የምትመራ ከሆነ ብቻ ነው። ይህን ማድረግህ የተሻልክ ልጅ፣ የተሻልክ ባል ወይም የተሻልሽ ሚስት፣ የተሻልክ አባት ወይም የተሻልሽ እናት፣ የተሻልክ ሠራተኛ፣ የተሻልክ ጓደኛ ከሁሉም በላይ ደግሞ የተሻልክ የፈጣሪህ አገልጋይ ሊያደርግህ ይችላል።
ኃላፊነትን መቀበል
7–11. በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው ከሕይወት ከሁሉ የተሻለውን ነገር ለማግኘት ቁልፉ ምንድን ነው?
7 በቅርብ ጊዜም ይሁን ወደፊት ከባድ ውሳኔዎችን የምታደርግበት ጊዜ ይመጣል። የራስህን የኃላፊነት ሸክም የምትሸከምበት ጊዜ ይመጣል። አንተ በአሁኑ ሰዓት እንደ ንሥር ጫጩት
ነህ። ንሥሮች ብዙውን ጊዜ ጎጆአቸውን የሚሠሩት በትልቅ ገደል ጫፍ ላይ መሆኑን ታውቅ ይሆናል። ጫጩቶቹ ክንፎቻቸውን ሲያርገበግቡና ለመብረር ሲዘጋጁ ወላጆቻቸው ወደ ጐጆው ጠርዝ ይወስዷቸውና ከዚያ በኋላ ወደ አየር ይለቋቸዋል! አንድ ተመልካች እናቲቱ ንሥር ጫጩቱን 90 ሜትር ያህል ወደታች ከለቀቀች በኋላ ሽው ብላ ከበታቹ ስትደርስ ክንፎቿን ዘርግታ ጀርባዋ ላይ እንዲያርፍ ስታደርግ እንደተመለከቱ ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እንደገና ወደ ጎጆዋ በርራ በመውጣት ጫጩቱ ንሥር መብረር እስኪለምድ ድረስ ሂደቱ በመደጋገም ቀጠለ። — የስሚትሶኒያን ኢንስቲትዩሽን ቡሌቲን ጥራዝ 167 ገጽ 3028 ወደ አንተ ስንመለስ ወላጆችህ በብዙ ጥረትና እቅድ በአንድ ቤት አብሮ የሚኖር ቤተሰብ ገንብተዋል። ይሁን እንጂ ዘላለም ለአንተ ሲሠሩልህ እንዲኖሩ ወይም ትላልቅ ውሳኔዎች እንዲያደርጉልህ በእነሱ ላይ ሃሳብህን ጥለህ ልትቀመጥ አትችልም። በተለይ ለአካለ መጠን ደርሰህ ጎጆ ለመውጣት በምትወስንበት ጊዜ ይህ አባባል ይሠራል። እናቲቱ ንሥር ለጫጩትዋ እንደምታደርገው ሁሉ ወላጆችህ ጎልማሳ ሰው ሆነህ ራስህን እስክትችል ድረስ ሁኔታዎች ቀላል እንዲሆኑልህ በማድረግ ኃላፊነትን ለመሸከም እንድትዘጋጅ ሊረዱህ ይችላሉ። ይሁን እንጂ አንተም የበኩልህን ማድረግ ይኖርብሃል።
9 የኃይለኞቹ የንሥር ክንፎች አሠራርና የተፈጥሮ የመብረር ችሎታ መጀመሪያ የተገኘው ከሁሉ በላይ ጥበበኛ ከሆነው ፈጣሪ ነው። ስለዚህ እያንዳንዳችን ከሕይወታችን ከሁሉ የተሻለውን ነገር ማግኘታችን የተመካው በእርሱ ላይ በመደገፍ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልገናል። ወላጆችህ ሊሰጡህ የቻሉት አጀማመር የቱንም ያህል ጥሩ ወይም መጥፎ ይሁን፣ የቱንም ያህል ጥሩ አእምሮና አካል ይኑርህ ይሖዋ አምላክ የሚሰጠውን መመሪያና መመሪያውንም ለመከተል የሚያስችል ኃይል እንዲሰጥህ ምን ጊዜም እርሱኑ ተስፋ ማድረግ እንደሚያስፈልግህ ለመርሳት አትፈልግም። እርሱም እንደ አንተ ላሉት ወጣቶች ጥቅም ብሎ የሚከተሉትን ቃሎች በመንፈሱ አነሳሽነት አስጽፎአል:-
10 “ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፣ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኟት ሕይወት፣ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና፣ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና . . . ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ። የእግርህን መንገድ አቅና፣ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።” —11 መመሪያ ለማግኘት ወደ ይሖዋ አምላክና ወደ ቃሉ በይበልጥ በተመለከትክ መጠን የሕይወት መንገድ ይበልጥ ቀና ይሆንልሃል።
አምላክን ወዳጅህ ማድረግ
12, 13. (ሀ) አምላክ ወዳጃችን እንዲሆን ከተፈለገ መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት ነው ከሚለው ነገር ከመራቅ ሌላ ምን ያስፈልገናል? (ለ) እንዲህ ዓይነቱን ወዳጅነት ለማግኘት መንገዱ የተከፈተልን እንዴት ነው? (ዮሐንስ 14:6)
12 ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? ቃሉ ኃጢአት እንደሆነ ከሚያመለክተው ነገር በመራቅ ብቻ አይደለም። ይሖዋ አምላክን እንደ ሰማያዊ አባትህ በማድረግ ከእርሱ ጋር የግል ዝምድና እንዲኖርህ ያስፈልጋል። ወላጆችህ ወደዚህ ዝምድና ሊመሩህ ይችሉ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ያንን ዝምድና ባንተ ፋንታ ሆነው ሊመሠርቱልህ አይችሉም። የይሖዋን ወዳጅነት እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መርምረህ ራስህ ይህን ማድረግ ይገባሃል። የዚህ እጅግ በጣም ሰፊ አጽናፈ ዓለም ፈጣሪ ወዳጅህ እንዲሆን ከፈለግህ እርሱ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
13 ይሖዋ አምላክ ለዚህ ወዳጅነት መንገድ ለመክፈት ሲል የበኩር ልጁ ሰው ሆኖ እንዲወለድ በማድረግ የሚያከናውነው ሥራ ሰጥቶ ወደዚህች ፕላኔት ወደ ምድር ላከው። የአምላክ ልጅ አድጎ ሙሉ ሰው በሆነ ጊዜ ስለ እኛ ሕይወቱን ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው “ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሳ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።” — ዕብራውያን 2:9
14, 15. (ሀ) ሁላችንም ፍጹማን አለመሆናችንን የሚያሳይ በሕይወታችን ውስጥ ምን ነገር ማየት እንችላለን? (ሮሜ 5:12፤ 7:21–23) (ለ) በማቴዎስ 6:12 ላይ ኃጢአት በምን ተመስሏል? ያ “ዕዳ” ሊከፈል የሚችለው እንዴት ነው?
14 ይህ ያስፈለገበት ምክንያት አለፍጽምናና ኃጢአት ስላለብን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። አንዳንድ ጊዜ ስህተት ወይም ኃጢአት እንደሆነ ያወቅኸውን ነገር ላለማድረግ ትግል እንደሚጠይቅ አንተም ሳትገነዘበው ስለማትቀር ሁላችንም ፍጹማን ያልሆንንና ኃጢአተኞች መሆናችንን ለመረዳት ከባድ ሊሆንብህ አይገባም። አንዳንድ ጊዜ ተዳክመህ ለአንድ ዓይነት የተሳሳተ ምኞት ተሸንፈህ ይሆናል። ይህ ኃጢአትን የመሥራት የተፈጥሮ ዝንባሌ ከመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የወረስነው ነገር ነው። መላው የሰው ዘር ሟች የሆነውም ለዚህ ነው።
15 ይሁን እንጂ የአምላክ ልጅ በደላችንን ሁሉ ለመሠረዝ የሚያስችለውን መንገድ ለማዘጋጀት ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአትን ከ“ዕዳ” ጋር በማመሳሰል ይህ ነገር እንዴት ሆኖ እንደሚሠራ ለማስተዋል ይረዳናል። (ማቴዎስ 6:12) ለምሳሌ በአንድ ሰው ላይ የሐሰት አሉባልታ ብትነዛ ይቅርታ የመጠየቅ ‘ዕዳ’ አለብኝ ብለህ አትናገርምን? ይህም በሠራኸው በደል ምክንያት የእርሱ ባለ “ዕዳ” ነህ ማለት ነው። ለአምላክ ያለብን ዕዳ ግን በጣም ብዙ ከመሆኑ የተነሣ ራሳችን ልንከፍለው ፈጽሞ አንችልም። የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወት ግን በጣም ከፍተኛ ዋጋ ስላለው በወረስነው ኃጢአት ምክንያት በአምላክ ላይ የሠራነውን በደል ሁሉ ሊሰርዝ ይችላል። የአምላክ ልጅ ሕይወቱን ስለኛ አሳልፎ የሰጠውም በዚህ ምክንያት ነው።
16–18. (ሀ) አምላክ በልጁ በኩል ላደረገው ነገር የእኛን አድናቆት ሊያገኝ ይገባዋል ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው? (ሮሜ 5:6–10) (ለ) ይህንን አድናቆት ለማሳየት ልናደርጋቸው የምንችላቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?
16 ስለዚህ ከአምላክ ጋር ወዳጆች ለመሆን የሚያስችለው መንገድ ተከፍቶልናል። ይሁን እንጂ አምላክ ልጁን በመሠዋቱ ልጁም ለእኛ በመሞቱ የቱን ያህል ትልቅ ነገር እንዳደረጉልን የምናደንቅ መሆናችንን ማሳየት ይኖርብናል። በዚህ የአምላክ ዝግጅት ላይ እምነት እንዳለን ማሳየት ይኖርብናል። ኢየሱስ “አባት ልጁን ይወዳል፣ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። በልጁ የሚዮሐንስ 3:35, 36
ያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” በማለት ተናግሮአል። —17 የአንድ ሰው ሕይወት አድንሃል እንበል። ለምሳሌ በውኃ ሰጥሞ ከመሞት ወይም በቤት ቃጠሎ ምክንያት ከመሞት አዳንከው እንበል። እሱን ለማዳን ስትሞክር ግን አንተው ራስህ ሞትህ። ከሞት የዳነው ሰው ግን ምንም ዓይነት አመስጋኝነት ባያሳይ፣ ወደ ወላጆችህ ሄዶ ራስ ወዳድ ሳትሆን ራስህን ብትሰዋለትም ምንም የአድናቆት ቃል ባይናገር ምን ይባላል? ያንተ አባት ምን የሚሰማቸው ይመስልሃል? እንግዲያውስ ልጁ ለሰው ዘር ያደረገውን እያወቁ ምንም ዓይነት አድናቆት በማያሳዩ ሰዎች ይሖዋ አምላክ ቢያዝንና ወዳጅነቱን ቢነፍጋቸው ለምን ተገቢ እንደሆነ ልትረዳው ትችላለህ።
18 አድናቆትህን ባኗኗርህ ማሳየት ትችላለህ። ስለሠራሃቸው በደሎች ከልብ እንደተጸጸትህ ልታሳይና በልጁ መሥዋዕት አማካኝነት ‘ዕዳህን እንዲሸፍንልህ’ አምላክን መለመን ትችላለህ። በቀሪው ሕይወትህ አምላክን ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እርሱን ለማገልገል ራስህን ለእርሱ ልትወስን ትችላለህ። ይህን ውሳኔያችንን በውኃ ጥምቀት ለማሳየት እንደምንችል መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። እርግጥ ይህ በችኰላ የሚደረግ ነገር አይደለም። ለአምላክ አንድ ነገር አደርግልሃለሁ ብለህ ከተናገርክ በኋላ ሃሳብህን መለወጥ አትችልም። ሕፃናት እንደዚህ ናቸው። ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ እርግጠኞች አይደሉም። ይሁን እንጂ ወደ ሙሉ ወንድነት ወይም ሴትነት እየተቃረባችሁ ከሆነ መወሰን ወደምትችሉበት ዕድሜ ላይ እየደረሳችሁ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ጉዳዩ በጥሞና ልታስቡበት የሚገባ ነው።
ተፈታታኙን ትግል መቀበል
19–21. (ሀ) አንተ የተያያዝከው ተፈታታኝ ትግል ዳዊት ጐልያድን ለመዋጋት በሄደ ጊዜ ከገባበት ግጥሚያ ጋር ተመሳሳይ የሆነው እንዴት ነው? (1 ሳሙኤል 17:4–11, 26–51፤ ዮሐንስ 15:17–20፤ ያዕቆብ 4:4) (ለ) ይህን ተፈታታኝ ትግል በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት እንደሚቻል እርግጠኞች ልንሆን የምንችለው ለምንድን ነው? (ዮሐንስ 16:33፤ ፊልጵስዩስ 4:13፤ ምሳሌ 3:5, 6)
19 የአምላክ ወዳጅ ሆነህ መቀጠል ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም።
እንዲያውም ዓለም ባጠቃላይ የአምላክ ጠላት ወዳጅ ስላልሆነ ትልቅ ግጥሚያ እንዳለብህ መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል። ቢሆንም አትፍራ። የአምላክ አገልጋይ ዳዊት ገና ትንሽ ልጅ ሳለ ያሳየውን ዓይነት መንፈስ ለማሳየት ትችላለህ። ዳዊት ወደ ሠራዊቱ ጦር ሠፈር የመጣው እሥራኤላውያን የሐሰት አማልክት አምላኪዎች ከሆኑ ፍልስጤማውያን ጋር ተፋጥጠው በነበረበት ጊዜ ነበር። የፍልስጤማውያን ታላቅ ጦረኛ የነበረ ጎልያድ የተባለ ግዙፍ ሰው እሥራኤላውያንን እንዲጋጠሙት እየተወራረደ ይሰድባቸው ነበር። ዳዊት ይህን ሰማ። ገና ወጣት ቢሆንም በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ነበረው። ግጥሚያውን ተቀበለ፣ ከባድ ትጥቅ ወደታጠቀው የሚጎማለል ጠላት ቀረበና በእረኛ ወንጭፉ በወነጨፈው አንድ ድንጋይ ጠብ አደረገው።20 ዛሬ ጠላት የሆነ ዓለም ይፈታተንሃል፤ ሆኖም አትፍራ። ይሖዋ አምላክ በዳዊት ጊዜ እንደነበረው ያው ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክ ነው። ስለዚህ ድፍረት ካሳየህና ከሁሉም በላይ ደግሞ እንደሚደግፍህና አስፈላጊውን ኃይል እንደሚሰጥህ እንጂ ፈጽሞ እንደማይተውህ እምነት ካሳየህ ድል ልታደርግ ትችላለህ።
21 አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች፣ ብዙ ወጣቶችም ጭምር የአንዳንድ ምድራዊ የፖለቲካ መንግሥታትን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ ከባድ ችግሮችን ችለዋል፤ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለዋል፤ አልፎ ተርፎም ሞተዋል። ይሁን እንጂ የመላውን አጽናፈ ዓለም ፈጣሪ ፍላጐት ለመፈጸም ሲባል ማገልገል እንዴት የበለጠ ታላቅ ክብር ነው! ይህም በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ያለ ማንም ሰው ከሚኖረው ሕይወት እጅግ በጣም የተሻለ ሕይወት እንዴት ሊሰጥህ እንደሚችል እስቲ እንመልከት።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]