ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠርና ጥናታዊ ቅርርብ መፍጠር
ምዕራፍ 19
ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠርና ጥናታዊ ቅርርብ መፍጠር
1–4. (ሀ) የተቃራኒ ፆታዎች ለጨዋታ መቀጣጠር የተለመደ ተግባር የሆነበት ጊዜ ምን ያህል ቅርብ ነው? (ለ) የተቃራኒ ፆታዎች መቀጣጠር ባልተለመደበት ቦታ የጋብቻ ዝግጅት የሚደረገው እንዴት ነው? (ሐ) በመጨረሻው እነዚህ ባሕሎች ምን ያህል ጥሩ ወይም መጥፎ መሆናቸውን የሚወስነው ምንድን ነው?
ማንኛውም ጤነኛ ሰው ከሕይወት እውነተኛ ደስታ ለማግኘት ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ ደስታ ከአምላክ መንፈስ “ፍሬዎች” አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ከሕይወት ደስታን ለማግኘት መፈለግ ተገቢ መሆኑን ያሳያል። (ገላትያ 5:22) ብዙ ወጣቶች በተለይም በምዕራባውያን አገሮች ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተቀጣጥሮ መጫወትን ደስታ የሚገኝበት ዋና መንገድ አድርገው ይመለከቱታል። ብዙውን ጊዜ የሚቆጣጠራቸው አዋቂ ሰው አብሯቸው ሳይኖር ከተቃራኒ ጾታ ጋር ተገናኝተው ለመጫወት ይቀጣጠራሉ። ስለዚህ ጉዳይ ምን ሊባል ይቻላል?
2 ከተቃራኒ ፆታ ጋር ጊዜን በጨዋታ ለማሳለፍ መቀጣጠር በብዙ ቦታ በጣም የተለመደ በመሆኑ መደረግ ያለበት ተገቢ ነገር እንደሆነ አድርገህ ታስብ ይሆናል። ሆኖም ቤተሰብ ከኅብረተሰብ አንፃር ሲታይ የተሰኘ መጽሐፍ “የተቃራኒ ፆታዎች በቀጠሮ ተገናኝቶ መጫወት አሁን በምናውቀው መልኩ የተጀመረው ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ሳይሆን አይቀርም” በማለት እንደሚገልጸው የተቃራኒ ፆታዎች መቀጣጠርና አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ምን ጊዜም የነበረ ነገር አይደለም። ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር በብዙ አገሮች እስካሁን አልተለመደም። እንዲያውም ዕጮኛሞቹ ወንድና ሴት እስከ ሠርጋቸው ቀን ድረስ ላይተያዩ ይችላሉ። የጋብቻቸው ዝግጅት የሚደረገው በወላጆቻቸው ወይም በ“አገናኝ” ወይም በ“መካከለኞች” በኩል ነው።
3 እርግጥ የምትኖረው ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣ
ጠርና ጥናታዊ ቅርርብ ማድረግ የተለመደ በሆነበት አገር ከሆነ በአንዳንድ አገሮች ይህ ባሕል ያልኖረበትን ምክንያት መረዳት አዳጋች ይሆንብህ ይሆናል። ይሁን እንጂ በነዚያ አገሮች የሚኖሩ ሰዎችም አንተ በምትኖርበት አገር ባለው ባሕል የአንተኑ ያህል ግራ ይገባቸው ይሆናል። ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠርና ጥናታዊ ቅርርብ ማድረግ ጥበብ የጎደለው ወይም ከናካቴው አሳፋሪ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱት ይሆናል። አንዲት ሕንዳዊት ልጃገረድ በጣም ታዋቂ ለሆነ አንድ ምዕራባዊ የጋብቻ አማካሪ እንዲህ ብላለች:- “ድንገት የተገናኘነውንና የተግባባነውን ልጅ ጠባይ እንዴት ለማወቅ እንችላለን? ወጣትና ተሞክሮ የሌለን ነን። ወላጆቻችን በዕድሜ የበሰሉና የበለጠ ጥበበኞች ስለሆኑ እንደኛ በቀላሉ ሊታለሉ አይችሉም። . . . የማገባው ሰው የሚስማማኝ ትክክለኛው ወንድ መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። እኔው ራሴ መምረጥ ቢኖርብኝ ኖሮ በቀላሉ ልሳሳት እችል ነበር።”4 ስለዚህ ጠባብ አመለካከት ይዞ ነገሮች መደረግ ያለባቸው እኛ ባለንበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በሚያደርጉት መንገድ ብቻ ነው ብሎ ከማሰብ ይልቅ አስተሳሰባችንን ሰፋ ብናደርገው ጥሩ ነው። ያም ሆነ ይህ በመጨረሻው አንድ ባሕል ምን ያህል ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን የሚወስነው ውጤቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በመክብብ 7:8 ላይ “የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል” ይላል። የተቃራኒ ፆታዎች ተቀጣ ጥሮ መጫወትና ጥናታዊ ቅርርብ መፍጠር ባሕል በሆነባቸው በብዙ አገሮች ከመቶ ጋብቻዎች ውስጥ የሚበዛው እጅ የተቃና ጋብቻ መሆኑ ቀርቶ በፍቺ ያከትማል።
ታዲያ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት ብሎ ስለ መቀጣጠር ምን ሊባል ይቻላል?
5–8. (ሀ) በመክብብ 11:9, 10 ላይ የተነገረው ነገር አድራጐታችን የሚያስከትለውን ነገር አርቀን እንድናይ የሚረዳን እንዴት ነው? (ለ) ብዙ ወጣቶች ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር የሚፈልጉት ለምንድን ነው?
5 የነገሮችን ምክንያት አውጥተህና አውርደህ በማመዛዘን የምታምን ከሆነ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት ብሎ የመቀጣጠርን ያጭር ጊዜ ውጤት ብቻ ሳይሆን የረጅም ጊዜ መዘዙንም ከግምት ለማስገባት ትፈልጋለህ። ፈጣሪያችንም ነገሮችን ከዚህ የረዥም ጊዜ አመለካከት አንፃር እንድናያቸው ይረዳናል። እርሱ ለእኛ የሚመኝልን እውነተኛና ዘላቂ ደስታ የሚያመጣልንን ነገር ነው። ስለዚህ በቃሉ ውስጥ “አንተ ጐበዝ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፤ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው። በልብህም መንገድ ዓይኖችህም በሚያዩት ሂድ። ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ፤ ሕፃንነትና ጉብዝና ከንቱዎች ናቸውና ከልብህ ኀዘንን አርቅ ከሰውነትህም ክፉን ነገር አስወግድ” በማለት አጥብቆ ያሳስበናል። (መክብብ 11:9, 10) ይህስ ምን ማለት ነው?
6 ይህ ማለት ፈጣሪ በወጣትነትህ እንድትደሰት ይፈልጋል፤ ቢሆንም የኋላ ኋላ ሕይወትህን በሚጐዳ ተግባር እንድትጠመድ አይፈልግም ማለት ነው። የሚያሳዝነው ግን አንድ የዘመናችን ደራሲ “አብዛኞቹ የሰው ልጆች አፍላ የሕይወት ዘመናቸውን የሚጠቀሙበት የኋላ ሕይወታቸውን መራራ በሚያደርግ መንገድ ነው” በማለት እንደገለጹት ይህ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የሚደርስ መሆኑ ነው። ይህ በአንተ ላይ እንዲደርስ አትፈልግም፤ ትፈልጋለህ እንዴ? አምላክም ይህ እንዲደርስብህ አይፈልግም። ሆኖም ይኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የመክብብ መጽሐፍ ወጣቶች ስለሚያደርጉት ነገር በአምላክ ተጠያቂዎች እንደሆኑ
ይገልጻል። የመረጡት መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት ከመቀበል ለማምለጥ ወጣትነታቸው ሰበብ አይሆናቸውም።7 ይህ ሁሉ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት ከመቀጣጠር ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ አለው። እንዴት? እስቲ ራስህን “ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተቀጣጥሬ ለመጫወት የምፈልገው ለምንድን ነው?” “በቡድን ሆነን ብንጫወት ምን የሚቀር ነገር ቢኖር ነው በዚህ መንገድ ለመደሰት የመረጥኩት? ከተቃራኒ ጾታ ጋር ሁለታችን ብቻ ተገናኝተን ለመጫወት የምፈልገው ለምንድን ነው?” እያልክ ራስህን ጠይቅ። መሠረታዊው ምክንያት ለተቃራኒ ጾታ የሚሰማህ እያደር እየጨመረ የሄደው የመሳሳብ ስሜትህ አይደለምን? ይህንንም በግልጽ የሚያሳየው አንድ ወጣት ከማን ጋር ተቀጣጥሮ ለመጫወት እንደሚሻለው ሲያስብ ለምርጫው ከፍተኛ ድርሻ ያለው አብዛኛውን ጊዜ አካላዊ ውበት መሆኑ ነው።
8 ተቀጣጥረው የሚጫወቱ ብዙ ወጣቶች የጋብቻ ሐሳብ ወይም የተቀጣጠሩትን ሰው የትዳር ጓደኛ ለማድረግ ዓላማ የላቸውም። ከተቃራኒ ፆታ ጋር መቀጣጠር ልማድ በሆነባቸው በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ይህ ልማድ የሚታየው እንደ አንድ ዓይነት መዝናኛ፣ ምሽትን ወይም ቅዳሜና እሁድን ማሳለፊያ እንደሆነ ተደርጐ ነው። “የተለዩ” ሆነው ለመታየት የማይፈልጉ አንዳንድ ወጣቶች ደግሞ የሚቀጣጠሩት እኩዮቻቸው የሚያደርጉት ስለሆነ ብቻ ነው። የሆነው ሆኖ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር ወደ “ኀዘን” እንዲያውም ወደ “ክፉ ነገር” ሊመራ መቻሉ አያጠያይቅም። ለምን እንደዚህ ሊሆን እንደሚችል እስቲ እንመርምር።
የአካል መነካካት የሚያስከትለው ውጤት
9–11. (ሀ) ብዙውን ጊዜ ተቃራኒ ፆታዎች ተቀጣጥረው በሚጫወቱበት ጊዜ ምን የአካል መነካካት አይቀርም? በተፈጥሮ የመቀራረብ ፍላጎት እየጨመረ የሚሄደውስ ለምንድን ነው? (ለ) ይህስ ላላገባ ሰው የአእምሮ ጭንቀት የሚያመጣበት ለምንድን ነው? (ሐ) የአካል መነካካቱ ወደ ዝሙት ካደረሳቸው ብዙ ዓይነት መከራዎች ሊያስከትል የሚችለው እንዴት ነው?
9 አብዛኛውን ጊዜ ከተቃራኒ ፆታ ጋር በቀጠሮ ተገናኝቶ መጫወት የሆነ ዓይነት የአካል መነካካትን ማለትም እጅ ለእጅ
መያያዝን፣ መሳሳምን፣ ወይም ከዚያ አልፎ መሄድን ይጨምራል። ለመጀመሪያ ጊዜ የሌላውን ሰው እጅ መጨበጥ ስሜትን ሞቅ የሚያደርግ በጣም አስደሳች ነገር ሊሆን ይችላል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እንደ መጀመሪያው አስደሳች ላይሆን ይችላል። ከዚህ የበለጠ ነገር፣ ለምሳሌ መሳሳምን ወደመፈለግ መሻገር ሊመጣ ይችላል። ይህም ቢሆን ጥቂት ቆይቶ ተራ ነገር፣ እንዲያውም የተሰለቸ ይሆናል። ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው?10 ምክንያቱም የፆታ ፍላጎት ስሜት ባለበት ቦታ ላይ ይህ ወደ አንድ የተወሰነ ውጤት የሚያደርሱ እንደ ሰንሰለት የተያያዙ ነገሮች ክፍል ስለሆነ ነው። የሰንሰለቱ የመጀመሪያው ቀለበት የመጀመሪያው መነካካት ነው። የመጨረሻው ቀለበት ደግሞ አምላክ ለተጋቡ የትዳር ጓደኛሞች ብቻ የመደበው የጾታ ግንኙነት ነው። በሰንሰለቱ ውስጥ ያለው ሌላው ነገር ሁሉ ወደ ሰንሰለቱ የመጨረሻ ቀለበት የሚመራ ነው። እንግዲያውስ ያላገባህ ከሆንክ በመጀመሪያው የሰንሰለቱ ቀለበት ወይም ከሌሎቹ በአንዱ መጀመሩ ጥበብ ነውን? ይህን ማድረግ በራስ ላይ “ኀዘንን” ሳያመጣ አይቀርም። ለምን? ምክንያቱም ሰውነትህ አሁን ማግኘት ለማይገባው ነገር ማለትም ለሰንሰለቱ የመጨረሻ ቀለበት እየተሰናዳ በመሆኑ ነው። ለፆታ ግንኙነት ፍላጎትን ቀስቅሶ ይህን ፍላጎት አለማርካት ወደ ብስጭትና የአእምሮ ጭንቀት ሊመራ ይችላል።
11 ዝሙት መፈጸም የተፈጠረውን “ኀዘን” አያስወግደውም። እንዲያውም ወደ “ክፉ ነገር” ሊመራ ይችላል። እንዴት? በብዙ መንገዶች ነው። የአባለ ዘር በሽታን ሊያስከትል ይችላል። ልጅቷ ልታረግዝ ትችላለች። ይህም ሁለቱም ወዳልተዘጋጁበት ጋብቻ ገፍቶ በማስገባት የወደፊት ደስታቸውን በጥልቅ ሊነካው ይችላል። ወይም ደግሞ ወጣቱ ወንድ ወጣቷን ሴት ለማግባት እምቢ ይልና የሚወለደውን ልጅ ያለባል ለማሳደግ ትገደዳለች። አለዚያም መጽሐፍ ቅዱስ ከነፍስ መግደል የሚመድበውን ውርጃ እንድትፈጽም ትገፋፋ ይሆናል። ታዲያ ይህ ሁሉ “ክፉ ነገር” አይደለምን? ምናልባት አንተ ከተቃራኒ ፆታ ጋር በቀጠሮ ተገናኝቶ መጫወት እነዚህን ውጤቶች እንዳያመጣብህ ለመጠንቀቅ ቁርጥ ሐሳብ ታደርግ ይሆናል። ይሁን እንጂ እንደ አንተ ይተማመኑ የነበሩ ብዙዎች በመጨረሻው ከነዚህ ችግሮች አላመለ
ጡም። እንግዲያስ በእርግጥ ለማግባት ተዘጋጅተሃል ወይስ አልተዘጋጀህም የሚለው ጥያቄ ተመልሶ ይመጣል።የግል እድገትህ
12, 13. ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር ያንድን ሰው እድገት ሊያደናቅፍ የሚችለው እንዴት ነው? ስለዚህ ይበልጥ ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው ምን ዓይነት ግንኙነት ነው?
12 ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር በቀጥታ ወደ “ክፉ ነገር” ባይመራም እንኳ ሌሎች ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል። ጉዳት የሚያስከትልበት አንዱ መንገድ ትውውቅህ ያለ ጊዜው እንዲጠብና በአንድ ሰው ላይ ብቻ እንድታተኩር በማድረግ ነው። አሁን ያለህበት ጊዜ የራስህን ስሜታዊ ብስለት ለማጎልበት ከልዩ ልዩ ዓይነት ሰዎች ጋር በመገናኘትና በመቀራረብ ብዙ ልትጠቀም የምትችልበት ነው። ወጣት ወንድ ከሆንክ አስቀድመህ ትክክል ለሆነው ነገር አክብሮት ካላቸው ወንዶች ጋር በመቀራረብ እውነተኛ ወንድ በመሆኑ ላይ ለምን አታተኩርም? ከእነርሱ የወንድነትን ችሎታዎችና መንገዶች ልትማር ትችላለህ። ወጣት ሴት ከሆንሽም አስቀድመሽ ጥሩ የሴትነት ችሎታዎችንና መንገዶችን እንድታዳብሪ ሊረዱሽ ከሚችሉ ሴቶች ጋር ጊዜ በማሳለፍ እውነተኛ ሴት የመሆን ፍላጎት ለምን አታሳድሪም? ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር በእርግጥም እንደዚህ ላለው እድገት እንቅፋት ይሆናል፤ ያዘገየዋልም።
13 ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመጫወት መቀጣጠር የአብዛኛው ሕዝብ ባሕል ከመሆኑ በፊት ወጣቶች ማድረግ የሚችሏቸው ደስታ የሚያመጡ ብዙ ነገሮች ነበሩአቸው። አንተም ልታገኝ ትችላለህ። ከሌሎች ጋር በመነጋገር፣ በመማር፣ ሙያ በማዳበር፣ አንዳንድ ዕቅዶች አውጥቶ በመሥራት፣ በጨዋታዎች፣ ልዩ ልዩ ቦታ በመጐብኘትና አዳዲስ ነገሮችን በማየት እውነተኛ ደስታ ልታገኝ ትችላለህ። እንደዚሁም እነዚህን ነገሮች በጾታ ከሚመሳሰሉህ ሰዎች ጋር ወይም በቡድን በማድረግ ታላቅ ደስታ ልታገኝ ትችላለህ። በቡድኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ዓይነት በሰፋ መጠን ማለትም አንዳንዶቹ በዕድሜ እኩዮችህ የሆኑ፣ አንዳንዶቹ ከአንተ ከፍ
የሚሉና ሌሎቹም ከአንተም የሚያንሱ ያሉበት በሆነ መጠን የበለጠ ደስታ ይኖርሃል።መቼ ማግባት ይሻላል?
14, 15. (ሀ) በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች ቢጋቡ ጥሩ ነው ብለህ ታስባለህን? (ለ) ወላጆች የልጆቻቸውን የማግባት ፍላጎት በተመለከተ ምን ኃላፊነት አለባቸው?
14 ይሁን እንጂ ወጣቶች ለማግባት የሚፈልጉበት ጊዜ ይመጣል። ይህ በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው። ታዲያ ለዚህ ከሁሉ የተሻለው ጊዜ መቼ ነው? ገና በአሥራዎቹ ዓመታት የዕድሜ ክልል እያለህ ነውን? በአጠቃላይ ሲታይ መልሱ አይደለም ነው፤ ምክንያቱም በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ወጣቶች አብዛኞቹ የመሠረቱት ጋብቻ አንዱ ወይም ሁለቱም ተጋቢዎች ከዚህ በይበልጥ የበሰለ ዕድሜ ላይ በደረሱ ጊዜ የተመሠረተውን ጋብቻ ያህል እንዳልሠመረላቸው መራራው ሐቅ አሳይቷል። አንድ የኅብረተሰብ ጉዳይ ተመራማሪ “የምርምር ጥናቶቹ የሚያሳዩት በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ሳሉ የተጋቡት ወጣቶች ጋብቻቸው ዕድሜያቸው ከዚያ በላይ ሲሆን ከተጋቡት ሰዎች ጋብቻ ጋር ሲወዳደር የፍቺ ቁጥርም ሆነ የደስታ ዕጦት የሚበዛባቸው ሆነው ተገኝተዋል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
15 በሌላው በኩል ግን ወጣቶች ፈጽሞ ማግባት የለባቸውም ብለን ግትር ደንብ ለማውጣት ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት አይኖረንም። ወላጆች ለልጆቻቸው ይበጃቸዋል እንዲሁም ከሁሉ የበለጠ ደስታና ጥቅም ያመጣላቸዋል ብለው የሚያምኑበትን እንዲወስኑላቸው በአጠቃላይ የየአገሩ ሕግ መብት ይሰጣቸዋል። በስራቸው የሚተዳደሩትን ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆቻቸው እንዲያገቡ ለመፍቀድም ሆነ እንዳያገቡ ለመከልከል ሊወስኑ ይችላሉ። በጊዜያችን ያሉት ብዙ ችግሮችና ሳይሳኩ የሚቀሩት ጋብቻዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ወላጆች በጥንቃቄ እንዲወስኑ ሊያደርጋቸው ይገባል። አስተዋይ ወጣቶችም ቢሆኑ በችኮላ አግብተው ኋላ ከመጸጸት ይልቅ በጥንቃቄ እንዲወስኑ ሊያደርጋቸው ይገባል። ክፍት ስለተገኘ ብቻ በአንድ በር ዘው ብሎ መግባት ሞኝ
ነት ነው። በሩን አልፎ ምን እንደሚገኝ በመጀመሪያ በደንብ ማወቅ ያስፈልጋል።የትዳር ጓደኛ መምረጥ
16–19. (ሀ) የተቃራኒ ፆታዎች ጥናታዊ ቅርርብ በሚፈቀድባቸው ቦታዎች በገላትያ 5:13 ላይ ያለውን መሠረታዊ ሥርዓት በሥራ ላይ ማዋል ምን ያህል ጠቃሚነት ይኖረዋል? (ለ) የጥናታዊ ቅርርቡ ዓላማ ምን መሆን ይገባዋል? ይህን የጀመሩስ ለምን ነገር መዘጋጀት ይገባቸዋል? (ሐ) ተቃራኒ ጾታ የሆነን ሰው በደንብ ለማወቅ ከሰው ተነጥላችሁ ለብቻችሁ ከመሆን ይልቅ በቡድን ውስጥ ሆኖ ግለሰቡን ማጥናቱ የሚጠቅመው ለምንድን ነው?
16 በአንዳንድ ቦታዎች አንድ ወጣት ከወጣት ልጃገረድ ጋር አንድ ላይ እንዲሆን የሚፈቀድለት ቢያንስ ከወላጆች አንዱ ወይም ሌላ ጠና ያለ ሰው አብሯቸው ካለ ብቻ ነው። በብዙዎቹ የምዕራብ አገሮች ግን እንደነዚህ ያሉት ወጣቶች ማንም አብሯቸው ሳይሆን ለብቻቸው አብረው ሊሆኑ ይችላሉ። እንግዲያውስ ጥያቄው እንደዚህ ያለ ሰፊ ነፃነት በሚፈቀድበት ቦታ አንድ ወጣት ከተቃራኒ ፆታ ጋር ጥናታዊ ቅርርብ መፍጠሩ ደስታ ወደሚያስገኝና ወደሠመረ ጋብቻ እንዲመራ ምን ሊያደርግ ይችላል? የሚል ይሆናል።
17 ነፃነት ምን ጊዜም ኃላፊነትን አስከትሎ ያመጣል። ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ የተደቀነብህ ጥያቄ ይህ ከሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በገላትያ 5:13 ላይ የተሰጠውን ጥሩ መሠረታዊ ሥርዓት ልብ ብትለው ትጠቀማለህ። እርግጥ እዚህ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እየተናገረ ያለው ክርስትና ለተቀበሉት ሰዎች ስላመጣላቸው መንፈሳዊ ነፃነት ነው። ይሁን እንጂ መሠረታዊ ሥርዓቱ ለማንኛውም ዓይነት ነፃነት በተለይም የነፃነቱ አጠቃቀም ጥሩ ውጤትና የአምላክን ሞገስ እንዲያመጣ ለሚፈለገው ነፃነት ሁሉ ይሠራል። ሐዋርያው “ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፣ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ” ሲል ጻፈ። ለአምላክና ለጐረቤታችን፣ ለመጠናናት ሲባል ለተቀራረብነው ተቃራኒ ፆታም ጭምር ያለን እውነተኛ ፍቅር ማንኛውንም ነፃነት በራስ ወዳድነትና ጎጂ በሆነ መንገድ ከመጠቀም እንድንርቅ ይረዳናል።
18 ከተቃራኒ ፆታ ጋር ጥናታዊ ቅርርብ የምንፈጥረው ጋብቻን ዓላማ በማድረግ ብቻ መሆን ይኖርበታል። ስለዚህ ግለሰቡ የጋብቻ ኃላፊነቶችን ለመሸከም ዝግጁ ከመሆኑ በፊት ይህን መጀመር አይገባውም። እርግጥ አንዱን ወንድ ወይም አንዷን ሴት በመጨረሻው ለማግባት ትፈልጉ ወይም አትፈልጉ እንደሆነ ከመጀመሪያው ማወቅ አትችሉም። ስለዚህ ትኩረታችሁን በአንድ ሰው ላይ ለማሳረፍ አለመቸኮል አስተዋይነት ነው። ነገር ግን ይህ ጥናታዊ ቅርርብ በምታደርጉበት ጊዜ እንደ “ማሽኮርመም” ወይም እንደ መዳራት የሚቆጠር ከመጠን ያለፈ ቅርርብ ለመፍጠር ምክንያት አይሆናችሁም።
19 ከአንድ ሰው ጋር የመቀራረብ ፍላጎት ቢያድርባችሁም እንኳን ለጊዜው ግንኙነታችሁን እርሷ ወይም እርሱ ባሉበት ቡድን ውስጥ አብሮ በመሆን ብቻ እንዲወሰን መሞከሩ አስተዋይነት ይሆናል። ለምን? ምክንያቱም አንድ ሰው በእርግጥ ምን ዓይነት ሰው መሆኑን በተሻለ ሁኔታ ለማወቅ የሚቻለው በእንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ስለሆነ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የተለየ ትኩረት የሚያደርግብን ሰው እንዳለ በማይሰማን ጊዜ ይበልጥ “ማንነታችንን” ወደመደበቅ ስለማናዘነብል ነው። ወንዱና ሴቷ ከቡድኑ ተነጥለው ለብቻቸው በሚሆኑበት ጊዜ ግን ከዚያ በኋላ የሚኖረው የተፈጥሮ ዝንባሌ ሌላው ሰው እንደሚፈልገው ዓይነት ሆኖ መገኘት እንዲያውም እርሱ የሚወደውን ወይም የሚጠላውን እንደ መስተዋት ማንፀባረቅ ይሆናል። ይህም አንዳንድ ጊዜ የአንድን ሰው እውነተኛ ማንነት ሊሸሽገው ይችላል። ወንዱና ሴቷ ከሌሎች ተነጥለው ለብቻቸው በሚሆኑበት ጊዜ ወዲያውኑ ስሜት ሊያሸንፋቸው ስለሚቸል እርስ በርስ የሚተያዩት በባለቀለም መነጽር ይሆናል። በእንደዚህ ዓይነቱ የስሜት ግንፋሎት ተገፋፍተው ቢጋቡ ብዙውን ጊዜ የኋላ ኋላ ይቆጫቸዋል።
20–22. (ሀ) ጥናታዊ ቅርርብን ራስን ማታለልና ራስ ወዳድነት በሌለበት መንገድ መያዙ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? (ለ) በጥናታዊ ቅርርቡ ወቅት ስለ ወደፊቱ የትዳር ጓደኛችሁ ምን ለማወቅ ትችላላችሁ? በትዳር ጓደኛ ላይ በተለይ ምን ጠባዮችን ለማየት ትፈልጋላችሁ?
20 አብዛኛውን ጊዜ ለሴቷ ፍላጎት እንዳለው በማሳየት የመቀራረቡን ሁኔታ የሚጀምረው ወንዱ ነው። እርሱም እውነተኛ ሰው ከሆነና ቅርርቡን በቁም ነገር ከፈለገው ለጋብቻ እንዳሰባት ለማመን መብት አላት። ከዚያ በኋላስ? እርሱን ለጋብቻ ትፈልገው እንደሆነና እንዳልሆነ ራሷን የመጠየቅ ኃላፊነት አለባት። ወደፊት ባሏ እንዲሆን እንደማትመኘው እርግጠኛ ከሆነች ግን ለርሷ ያደረበት ስሜት እያደገ እንዲሄድ መፍቀዷ ጭካኔ ይሆናል። አንዳንድ ልጃገረዶች ተወዳጅነታቸው ወይም ተፈላጊነታቸው ጐላ ብሎ እንዲታይና ሌሎች ወጣቶችም እንዲከታተሏቸው ለማድረግ ሲሉ ብቻ ከአንድ ወንድ ጋር በጣም ይቀራረባሉ። አንዳንድ ወጣት ወንዶችም አብረን ጥሩ ጊዜ ካሳለፍን በኋላ ሌላ ነገር ከመምጣቱ በፊት እንለያያለን ብለው በማሰብ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል። ይሁን እንጂ ነፃነትን በእንዲህ ዓይነት የራስ ወዳድነት መንገድ መጠቀም ለወራት እንዲያውም ለዓመታት የማሽር ከባድ ቁስል፤ አዎ ከባድ ጒዳት ሊያስከትል ይችላል።
21 ተቀራርቦ ለመጠናናት ያለው ነፃነት ጥቅም ሊያመጣ የሚችለው ራስ ወዳድነት በሌለው መንገድ ከተሠራበት ብቻ ነው። ቀሪ ሕይወታችሁን አብራችሁ ለማሳለፍ የምታስቡትን ሰው በተሻለ ሁኔታ ለማወቅ ዕድል ሊሰጣችሁ ይችላል። ሁለታችሁም ራሳችሁን የማትደብቁ ከሆናችሁ ሌላው ወገን የሚወደውንና የሚጠላውን፣ የአቋም ደረጃዎቹን፣ ልማዶቹንና አመለካከቶቹን፣ ቁጠኛ መሆኑንና አለመሆኑን፣ ዝንባሌውን እንዲሁም ችግርና መከራ ሲመጣበት የሚያሳየውን ስሜት ለማወቅ ትችላላችሁ። እንደሚከተሉት ያሉትን ነገሮች ለማወቅ መፈለጋችሁ ተገቢ ነው:- እርሱ ወይም እርሷ ደግ፣ ለጋስና ለሌሎች አሳቢ ነውን/ናትን? ለወላጆችና ለሸመገሉ ሰዎችስ አክብሮት አለውን/አላትን? አቅምንና ቦታን በማወቅና በትሕትናስ በኩል እነዚህ ጠባዮች መኖራቸውን የሚያሳይ ጥሩ ማስረጃ አለ ወይስ እርሱ/እርሷ ጉረኛና እልኸኛ ነው/ናት? በእርሱ/በእርሷ የማየው ራስ መግዛትንና ሚዛናዊነትን ነው ወይስ በምትኩ ደካማነትንና የልጅነትን ጠባይ፤ ምናልባትም አኩራፊነትንና በንዴት መጦፍን? አብዛኛው የሕይወት ክፍል ሥራ ስለሆነ ስንፍና፣ ግዴለሽነት ወይም የገንዘብ አባካኝነት ጠባይ ይታይበታልን/ይታይባታልን? የወደፊት እቅዱስ/እቅዷስ ምንድን ነው? ልጅ መውለድ ይፈልጋል/ትፈልጋለች? የሙያ ችሎታ ለማሻሻል ፍላጎት አለው/አላት? “ተቃራኒ ፆታ
ዎች ጥናታዊ ቅርርብ ሲፈጥሩ የሚታዩ የአደጋ ምልክቶች” በሚል ርዕስ በተጻፈ ሐተታ ላይ አንድ ደራሲ “ተጫጭተው ከዚያም ተጋብተው በደስታ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ባደረግነው ጥናት መሠረት ደስተኛ ያልሆነ ጋብቻ ያጋጠማቸው በወደፊት የሕይወት ግቦችና ቅድሚያ ሊሰጧቸው በሚፈልጓቸው ነገሮች ላይ እምብዛም ስምምነት ያልነበራቸው መሆናቸውን ደርሰንበታል” ሲሉ አትተዋል።22 ከሁሉ በላይ ለማወቅ መፈለግ የሚኖርባችሁ በግለሰቡ/በግለሰቧ ፍላጎትና እቅድ ውስጥ የአምላክ ዓላማዎች ምን ያህል ቦታ እንዳላቸው ነው። አዎን፤ አጠቃላዩን የሰውየው ምስል ከተረዳችሁ በኋላስ እርስ በርሳችሁ ለጋብቻ ምን ያህል ተስማሚ ናችሁ? አሳሳቢ ልዩነቶች ካሉ ጋብቻ ራሱ ያስተካክለዋል ብለህ በማሰብ ራስህን አታታልል። እንዲያውም ልዩነቶቹ የሚያደርሱት ግጭት ጋብቻ በይበልጥ ጠልቆ እንዲሰማችሁ ያደርጋል።
ጥናታዊ ቅርርብ ሲደረግ ማሳየት የሚገባው የተከበረ ጠባይ
23–26. (ሀ) ለመጋባት ያሰቡ ወንድና ሴት ስለሚደያርጉት እጅ ለእጅ መያያዝ፣ መሳሳምና መተቃቀፍ እንዴት ይሰማሃል? (ለ) አንድ ሰው “መዳራትን” ወይም “ርኩሰትን” በመፈጸም በደለኛ ሆኖ ሊገኝ የሚችለው እንዴት ነው? እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን ማስወገድ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ገላትያ 5:19, 21)
23 ወላጆች ልጆቻቸው አዋቂ ሰው በመካከላቸው ሳይኖር ለብቻቸው ከተቃራኒ ፆታ ጋር ጊዜን እንዲያሳልፉ በሚፈቅዱባቸው አገሮች ጥናታዊ ቅርርብ የሚፈጥሩ ወንድና ሴት አብዛኛውን ጊዜ እጅ ለእጅ መያያዝ፣ መሳሳምና አልፎ ተርፎም መተቃቀፍ በመሳሰሉት የፍቅር መግለጫዎች ይካፈላሉ። ወላጆች ልጆቻቸው ሊጠብቁት የሚፈልጉትን የአቋም ደረጃ የማስተማር ግዴታ አለባቸው። በክርስቲያን ጉባኤ የሚገኙ ሽማግሌዎችም የወጣት ሰዎችን ትኩረት በአምላክ ቃል ውስጥ ወደሚገኙት ጤናማ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊመሩት ይችላሉ። በሕይወት ውስጥ የጥበብን መንገድ ለመከተል ከልብ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እንደዚህ ያለውን ምክር በፈቃደኝነትና በደስታ ይቀበላል።
ገላትያ 5:19–21) እነዚህን ማስጠንቀቂያዎች የሚሰሙ ወንድና ሴት ራሳቸውን ከብዙ ኀዘን ያድናሉ፤ በሠሩት መጥፎ ተግባር ትዝታ ከመረበሽም ይድናሉ። ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ የአቋም ደረጃ መሠረት ርኩስ ተግባር ምንድን ነው? ምንንስ ሊጨምር ይችላል?
24 መጽሐፍ ቅዱስ ዝሙትን ይኸውም የተጫጩ ወንድና ሴትን ጨምሮ ባልተጋቡ ሰዎች መካከል የሚደረገውን የፆታ ግንኙነት በማያሻማ ሁኔታ ከማውገዙም ሌላ ወንድና ሴት ጊዜያቸውን አብረው በሚያሳልፉበት ጊዜ ሊደርሱ ከሚችሉ የፆታ ብልግናና “ከርኵሰት” ያስጠነቅቃል። (25 ለጋብቻ በሚተሳሰቡ ሰዎች መካከል እጅ ለእጅ መያያዝ ንጹሕ የፍቅር መግለጫ ሊሆን ይችላል። እርግጥ ነው፤ ስሜትን የመቀስቀስ ባሕርይ አለው፤ ቢሆንም ይህ ተፈጥሮአዊ ነው፤ መጥፎ ነው ማለት አይቻልም። ሌላው ቀርቶ ሊያገቡት የሚያስቡትን ሰው ማየት ብቻ እንኳ ‘የልብ ትርታን በመጨመር’ ስሜትን ሊቀሰቅስ ይችላል። (መኃልየ መኃልይ 4:9) የሆነው ሆኖ የሰው ተፈጥሮ ሆነና አካላዊ መነካካት ጾታዊ “መሳሳብን” ይበልጥ እንደሚጨምረው ማስታወስ ያስፈልገናል። ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ሊከተል የሚችለውን መዘዝ በመገንዘብ ጊዜያቸውን አብ ረው በሚያሳልፉበት ጊዜ ከአካላዊ መነካካት ራሳቸውን በጣም ለመቆጠብ ይመርጡ ይሆናል። ለጥንቃቄ ብለው የወሰዱትን አቋም ማንም ሰው ሊያንኳስስባቸው ወይም ሊያቃልልባቸው አይገባም።
26 መሰሳምም ለመጋባት በሚተሳሰቡ ሰዎች መሃል ንጹሕ የፍቅር መግለጫ ሊሆን ይችላል። ላይሆንም ይችላል። በእርግጥ ጥያቄው በጉዳዩ ውስጥ ፍትወተ ሥጋ የሚገባው ምን ያህል ነው? የሚለው ነው። መሳሳም ፍትወተ ሥጋ በሚቀሰቅስ መንገድ ተደርጎ ወንዱና ሴቷ የፆታ ግንኙነት ፍላጎታቸው በኃይል ሊነሳሳ ይችላል። የፆታ ግንኙነት ፍላጎት መቀስቀስ ደግሞ ወንዱንና ሴቷን ለፆታ ግንኙነት ያዘጋጃቸዋል። ይህ መብት ግን በአምላክ ሕግ መሠረት ለተጋቡ ሰዎች ብቻ የተጠበቀ ነው። ወንዱና ሴቷ አንዱ የሌላውን የፆታ ብልቶች በመደባበስ ይሁን ወይም በሌላ መንገድ ሆን ብለው ያለ ሃፍረት ፍትወትን በሚቀሰቅስ ተግባር በመካፈል የአምላክን ሕግ ከተላለፉ “ርኩሰት” እና “መዳራት” በመፈጸም በደለኞች ይሆናሉ።
27–30. ከጋብቻ በፊት ፍትወት ከሚቀሰቅስ ተግባር ለመራቅ ምን ጥሩ ምክንያቶች አሉ?
27 ራሳችንን ማታለል የለብንም። በነዚህ ነገሮች ላይ ጠንካራ ራስን የመግዛት ጠባይ የሚጐድለን ከሆነ አጉል በመዳፈር የራሳችንንም ሆነ የሌላውን ሰው የወደፊት ሕይወት ማጨናገፍ አይገባንም። ፍሬኑ የተበላሸ መሆኑን እያወቅህ በቍልቍለትና በጠመዝማዛ መንገድ መኪና ትነዳለህን? በነዚህ ነገሮች ላይ ሐሳብህን የምትቆርጠውና ከልብህ ጋር ተመካክረህ ከውሳኔ መድረስ ያለብህ ከመጀመርህ በፊት እንጂ ከዚያ በኋላ አይደለም። አንድ ጊዜ ፍትወተ ሥጋ መቀስቀስ ከጀመረ እየጨመረ እንዳይሄድ ለማቆም ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው። የፆታ ግንኙነት እስከሚፈልጉበት ደረጃ ድረስ ፍትወት በውስጣቸው እንዲቀሰቀስ የሚፈቅዱ ሰዎች ይህንኑ በጋብቻ አማካኝነት ለማግኘት ካልቻሉ ለጭንቀትና ለብስጭት ራሳቸውን ያጋልጣሉ። ይህ ሁኔታ ስሜትን በጣም የሚቀሰቅስ አንድን መጽሐፍ ማንበብ ጀምሮ የመጨረሻው ምዕራፍ ተቀዶና ጠፍቶ ከማግኘት ጋር የሚመሳሰል ነው።
28 ጥናታዊ ቅርርብ በሚያደርጉበት ጊዜ ግንኙነታቸውን በከፍ
ተኛ ደረጃ የሚጠብቁ ሰዎች ተደጋጋሚነቱና ግለቱ ሳያቋርጥ እየጨመረ ለሚሄድ ገደቡን ያለፈ መቀራረብ ከተሸነፉት ይልቅ በጋብቻ በጣም የተሻለ ጅምር ይኖራቸዋል። አንዲት ልጃገረድ ሊዳፈራት ሲሞክር ከላይዋ ላይ ለማራቅ ሁልጊዜ ለምትታገለው ሰው ምን ያህል አክብሮት ይኖራታል? ራሱን የሚገታና የስነ ምግባር ጥንካሬ ያለው ወጣት ግን አክብሮትን ያተርፋል። ለልጃገረዷም እንዲሁ ነው። እርሷ በተለይ ስሜቷ ለመቀስቀስ ጊዜ የሚወስድ ሲሆን የወንዱ ስሜት ግን እንደዚያ ያለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋታል። ወንድ በቀላሉና በቶሎ የፆታ ፍላጎቱ ሊቀሰቀስ ይችላል።29 ፍትወታዊ ስሜታቸውን በተደጋጋሚ ከገለጹትና ይህም እየጨመረ ከሄደ ያለ ጊዜው ወደመጋባት ሊያደርስ ይችላል። ጒርምስናና ወጣትነት የተሰኘው መጽሐፍ “ጥናታዊ ቅርርብ እንደተጀመረ ያለው ጊዜ ከመጠን በላይ በፍቅር የሚያከንፍ ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ የሚፈጸም ጋብቻ አንድን ሰው ማንኛውም ጋብቻ ሊሰጥ ከሚችለው በላይ ከጋብቻው እንዲጠብቅ ሊያደርገው ይችላል። ጥናታዊ ቅርርቡ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየቱ መግባባት ያለበት ጋብቻ ይመሠረት ዘንድ አንዳቸው ስለ ሌላው የበለጠ ምክንያታዊ ግንዛቤ እንዲያገኝ ያደርጋል” ይላል። እንደ
ዚህ ዓይነቱ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ጥናታዊ ቅርርብ ደግሞ ራስን መግታትን ይጠይቃል። አለዚያ ገና ከጅምሩ የፍትወተ ሥጋ ግፊት ያይልና አደጋ ሊደርስ ይችላል።30 ጥናታዊ ቅርርብ በሚያደርጉበት ወቅት የፍትወት ስሜት ትርኢቱን በኃይል እንዲያደምቀው ከተፈቀደለት ከጋብቻው በኋላ ክፉ ጥርጣሬና አለመተማመን ሊፈጠር ይችላል። ባልና ሚስቱ:- የተጋባነው በእርግጥ ስለተዋደድን ነው ወይስ በሥጋ ፍትወት ተገፋፍተን ብቻ ነው? ምርጫችን ጥበብ ያለበት ነበረን? እያሉ ማሰብ ሊጀምሩ ይችላሉ። ሴቷም በበኩሏ ባሏ ያገባት እርሷን በእርሷነቷ በስብእናዋ ወዷት ሳይሆን ለአካልዋ ሲል ብቻ እንዳይሆን በማሰብ የፍቅሩን እውነተኛነት ወደመጠራጠር ትደርስ ይሆናል።
31, 32. ወንዱና ሴቷ በጥናታዊ ቅርርባቸው ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል ፍትወት ከሚቀሰቅስ ተግባር እንዲርቁ ሊረዳቸው የሚችለው ምንድን ነው?
31 ስለዚህ ራስህንና የወደፊት ደስታህን ከአደጋ ለመጠበቅ ከፈለግህ ፍትወት ከሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች ራቅ። ገለልተኛና ጨለማ ቦታዎች የጥናታዊ ቅርርቡን ክብር ያለው ለማድረግ አይረዱም። በተጨማሪም በፍቅር መግለጫዎች ከመካፈል በቀር ሌላ የሚደረግ ነገር እንደሌለ እስኪመስል ድረስ ውሎው በጣም ከረዘመም ጥናታዊ ቅርርቡን በክብር እንድትይዘው አይረዳህም። ነገር ግን በበረዶ ላይ እንደ መንሸራተት፣ የጤረጴዛ ኳስ ያሉ ወይም ተመሳሳይ ስፖርት በመጫወት፣ በምግብ ቤት አብሮ በመመገብ ወይም አንዳንድ ቤተ መዘክሮችን ወይም የምትወዱትንና የሚያምር ስፍራን አብራችሁ ሆናችሁ በመጐብኘት ብዙ ንጹሕ ደስታ ማግኘት ይቻላል። በምታውቋቸው ሰዎች አካባቢ ባለመሆናችሁ ለብቻችሁ የመሆን ስሜት ሊያስደስታችሁ የሚችል ሲሆን ከሌሎች ሰዎች ሙሉ በሙሉ ባለመገለላችሁ አብራችሁ በምታሳልፉት ጊዜ በመጥፎ ሥነ ምግባር እንዳትካፈሉ ይጠብቃችኋል።
32 ከዚህም በላይ ራስህን በመግታትህ ምክንያት “ስለቀረብህ” ነገር በማሰላሰል ፋንታ ለወደፊቱ ለምን ነገር በመዘጋጀት ላይ እንዳለህ አስብ። እንዲህ ካደረግህ አብረህ ያሳለፍከውን ጊዜ ወደፊት ስታስታውስ የሚያስጠላ ወይም የሚጸጽት ሳይሆን የሚያስደስትና የሚያረካ ይሆንልሃል።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 153 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ጥናታዊ ቅርርቡ ተደጋጋሚ ፍትወታዊ መግለጫ የሚፈጸምበት ከሆነና ራስን የመግታቱ ጉዳይ እየቀነሰ ከሄደ ይህ ለወደፊቱ የሠመረ ጋብቻ የመመሥረትን አጋጣሚ የሚነካው እንዴት ነው?
[በገጽ 155 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ወጣቶች ሊካፈሉበት የሚችሉት ንፁሕ የሆነ ብዙ አስደሳች ነገር አለ