ወላጆችህን የምትመለከታቸው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 10
ወላጆችህን የምትመለከታቸው እንዴት ነው?
1–3. (ሀ) አንድ ሰው ለወላጆቹ ያለው ዝንባሌ ስለ ራሱ ምን ይናገራል? (ለ) አንተ የምታውቃቸው ወጣቶች ለወላጆቻቸው ምን ዝንባሌ አላቸው? በዚህ አቋማቸው ትስማማለህን? (ሐ) አንድ ወጣት ለወላጆቹ እንዲታዘዝ ምን ዓይነት ማሰልጠኛ ሊረዳው ይችላል? ለምንስ?
ሌሎች ስለ ወላጆቻቸው የሚሰማቸውን ሲነግሩህ ስለ ራሳቸውም አንድ ነገር እየነገሩህ ነው። አዎን፤ ስለ ወላጆችህ የምትናገረውና ለእነርሱ የምታደርገው ነገር ሁሉ በአእምሮህና በልብህ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ይገልጣል። አሁን ምን ዓይነት ሰው እንደሆንክ ስለ አንተ ብዙ ይናገራል። ለወደፊቱም ምን ዓይነት ሰው እንደምትሆን በግልጽ ይጠቁማል። ይህም የሆነበት ምክንያት እቤትህ ያዳበርከው ጠባይ የኋላ ኋላ የአንተው ክፍል ስለሚሆን ነው።
2 አንዳንድ ወጣቶች በሁሉም ነገር ስለ ወላጆቻቸው አፍራሽ ዝንባሌ ያድርባቸዋል። ወላጆቻቸው ችግራቸውን እንደማይረዱላቸው ወይም ሊረዱላቸው እንደማይሞክሩና በጭራሽ ጊዜ ያለፈባቸው በመሆናቸው በዚህ በፍጥነት በሚለዋወጥ ዓለም ምንም ዓይነት ጠቃሚ መመሪያ ሊሰጡን አይችሉም የሚል ስሜት ያድርባቸዋል። ይህ ስሜት ብዙም ሳይቆይ ወደ አጠቃላይ የዓመፀኝነት ዝንባሌ ያድጋል። በጊዜው ካልተገታ በቀላሉ ልማድ ይሆናል። ይህ ጠባይ ከቤተሰቡ ክልል ውጭ ካሉት ሰዎች ጋር ባለው ግንኙነትም መገለጥ ይጀምራል። ብዙም ሳይታወቅህ ለሰብዓዊው ኅብረተሰብ ጥቅምና ጥበቃ የወጡትን ሕጐች ለመታዘዝ ፈቃደኛ አለመሆንህ ወደ ከባድ ችግር ሊያስገባህ ይችላል።
3 ይሁን እንጂ እንደዚያ የማይሰማቸውና የማያደርጉ ሌሎች አሉ። ለወላጆቻቸው አክብሮት ይዘው ያድጋሉ። እነዚህ ወጣቶች ዓለም ይህን ያህል በችግር ውስጥ የወደቀው ለምን እንደሆኤፌሶን 6:4
ነና የወደፊቱ ጊዜ ለነርሱ ምን እንደያዘላቸው ያውቃሉ። በዚህ ምክንያት የሌሎቹን አፍራሽ ዝንባሌ እንዲከተሉ ለሚመጣባቸው ግፊት አይሸነፉም። ወላጆቻቸው በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው የአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙትን ለሰው የጠባይ መመሪያ እንዲሆኑ የወጡትን ከፍተኛ መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዲያከብሩ በውስጣቸው እንደቀረጹላቸው ይገነዘባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ “እናንተም አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን በጌታ [በይሖዋ አዓት] ምክርና በተግሳጽ አሳድጓቸው እንጂ አታስቆጡአቸው” በማለት ይመክራል። እነዚህ ወጣቶች ለዚህ ስልጠና አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት በፈቃደኝነት የበኩላቸውን አድርገዋል። በዚህም የተነሳ በቤተሰቡ አደረጃጀት ውስጥ ያላቸውን ቦታ ይገነዘባሉ። በቤቱም ውስጥ ጥሩ ዝምድና ይሰፍናል። —ለወላጆች የሚገባ ታዛዥነት
4–6. (ሀ) ወላጆችህ እስከ አሁን ድረስ ባለው ሕይወትህ ምን አድርገውልሃል? (ለ) ይህንንስ እንደምታደንቅ እንዴት ለማሳየት ትችላለህ? (ኤፌሶን 6:1, 2)
4 ነገር ግን ወላጆቻቸው የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊያስተምሯቸው ስለማይሞክሩት ወጣቶችስ ምን ሊባል ይቻላል? ይህ ከሆነ ለወላጆቻቸው አክብሮት መስጠትና መታዘዝ የለባቸውም ማለት ነውን? የወላጆች አመራር ከአምላክ የአቋም ደረጃዎች የራቀ ከሆነ ችግር የሚያጋጥም መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም ይህ ሁኔታ ወጣቶች ለወላጆቻቸው መልካም ዝንባሌ የማዳበራቸውን አስፈላጊነት በምንም ዓይነት አይቀንሰውም። ለምን? ብዙ ምክንያቶች አሉ።
5 ከዚህ በፊት ራስህን ችለህ ኖረህ ስለማታውቅ ወላጆችህ ያደረጉልህን ነገር ሁሉ ዛሬ ሙሉ በሙሉ አትገነዘበው ይሆናል። እስቲ ቆም ብለህ አስብ:- አባትና እናትህ ከተወለድክበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ ለአንተ ክብካቤ ሲያደርጉልህ ኖረዋል። የምትበላው ምግብ፣ የምትለብሰው ልብስና የምትኖርበት ቤት ሰጥተውሃል፣ አስተምረውሃል።
6 ከተወለድክበት ቀን ጀምሮ ወላጆችህ ያደረጉልህን ነገር ሌላ ሰው ቀጥረህ ብታሠራ ኖሮ ከፍተኛ ወጪ ባስወጣህ ነበር።
ለዚህ ሁሉ ወላጆችህ ሊከበሩ ይገባቸዋል። ከጊዜ በኋላ አግብተህ ልጅ ብትወልድ ወላጆችህ ለአንተ ያደረጉልህን በይበልጥ ታደንቃለህ። ታዲያ ለምን አሁንኑ አድናቆትህን አታሳይም? ለወላጆችህ ያለብህን ፍቅር የማሳየት ዕዳ ለእነርሱ አክብሮትንና ታዛዥነትን በማሳየት ብትከፍላቸው ባለ አእምሮ እንደሆንክና መልካም የሚያደርጉልህን ሰዎች ከፍ አድርገህ የምትመለከት የበሰለ ሰው ወደ መሆን የዕድገት ደረጃ መድረስህን ታሳያለህ ማለት ነው።7–12. (ሀ) አንድ ወጣት ወላጆቹ የሚሠሩትን ስሕተት እንዴት መመልከት ይገባዋል? (ማቴዎስ 6:14, 15) (ለ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጸው አምላክ ለወላጆች ምን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል? (ምሳሌ 6:20) ይህስ አስፈላጊ ዝግጅት የሆነው ለምንድን ነው? (ሐ) ወላጆችን አለመታዘዝ ምን ያህል ከባድ ነገር ነው?
7 ይህ ሲባል ግን ወላጆችህ ፍጹማን ናቸው ማለት አይደለም። ስህተት መሥራታቸው የማይቀር ነው። ይሁን እንጂ አንተም ስህተት ትሠራለህ። እንዲያውም የእነርሱን ያህል የሕይወት ተሞክሮ ስለሌለህ እነርሱ ከሚሠሩት የበለጠ ስሕተት ሳትሠራ አትቀርም። ወላጆችህ ስለሚሠሩት ስሕተት እየነቀፍካቸው ስለአንተ ስሕተቶች ግን ምንም እንዳይናገሩ ትጠብቃለህን? ወጥ የሆነ አቋም በመያዝ አንተ የምትሠራቸውን ብዙ ስሕተቶች እንደሚያልፉልህ ሁሉ አንተም የነርሱን ስሕተቶች ማለፍን መማር ይገባሃል። የበለጠ ከባድ ሃላፊነት ስላለባቸው አንዳንድ ጊዜ ቢሳሳቱ በቂ ምክንያት አላቸው። “ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፣ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ጥሩ መመሪያ ነው። — ያዕቆብ 2:13
8 ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ወላጆችህ ስሕተት ሠርተዋል ብለህ የምትገምተው ከአንተ የተለየ አመለካከት ስላላቸው ብቻ ሊሆን ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜና ወላጆችህ በዚያ አከራካሪ ጉዳይ ላይ ጽኑ አቋም በሚወስዱበት ጊዜ ምን ማድረግ ይገባሃል?
9 ወላጆችህ ያላቸው ቦታ ከአንተ ቦታ ጋር አንድ እንዳልሆነ ልብ ልትለው ይገባሃል። በአምላክ የነገሮች አደረጃጀት ውስጥ ቆላስይስ 3:20
አንድ ወላጅ ከፍተኛ ቦታ አለው። አምላክ ለወላጆችህ አንተ እስከ አሁን ገና ያላገኘኸውን ሥልጣንና ሃላፊነት ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ አንተን በሚመለከቱ ጉዳዮች የመጨረሻውን ውሳኔ ማድረጉ የወላጆችህ ነው። የአምላክ ቃል:- “ልጆች ሆይ ይህ ለጌታ [ለይሖዋ አዓት] ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻቸሁ ታዘዙ” በማለት የሚመክረው ለዚህ ነው። ይህም ማለት ወላጆችህ በሚጠይቁት የአምላክን ሕጐች በማያስጥስ በማንኛውም ነገር ሁሉ መታዘዝ አለብህ ማለት ነው። —10 አየህ፤ በሰው ዘር ማኅበረሰብ ውስጥ ሥርዓት መኖር አለበት። ሥርዓት ከሌለ ትርምስ እንዲያውም ሥርዓት አልባነት ይፈጠራል። ለምሳሌ አንድ መርከበኛ ለካፒቴኑ መርከቢቱን እን
ዴት እንደሚነዳ መመሪያ ሊሰጠው ወይም አንድ ኳስ ተጫዋች ለአሰልጣኙ ክለቡን እንዴት አድርጐ መቆጣጠር እንዳለበት ሊነግረው አይችልም። ጥሩ ካፒቴንና ጥሩ አሰልጣኝ በአመራራቸው ሥር ያሉት ሰዎች የሚሰጡትን ሃሳብ የሚቀበሉና ሃሳብ እንዲሰጡም የሚያበረታቱ መሆናቸው የተረጋገጠ ነው። ይሁን እንጂ ሌሎቹ እንዲያዟቸውና ምን መደረግ እንዳለበት መመሪያ እንዲሰጡ ከፈቀዱላቸው ብዙም ሳይቆይ ሥልጣናቸው ይዳከምና ብጥብጥና ዝብርቅ ይፈጠራል። በዚህ አትስማማምን?11 በተመሳሳይም በቤተሰቡ ክልል ውስጥ ሥርዓት መኖር አለበት። አምላክ በቤተሰብ ውስጥ አባትን ራስ እናትን ደግሞ የእርሱ የቅርብ ረዳት አድርጐ መድቦአቸዋል። ሁለቱም ወላጆች የልጆቻቸው የበላይ ተቆጣጣሪ ሆነው ተሹመዋል። ስለዚህ ወላጆችህ ማታ በስንት ሰዓት እቤት መግባት እንዳለብህ፤ ከእነማን ጋር መዋል እንደምትችል፣ ስለ ፀጉር አያያዝህና ስለመሳሰሉት ነገሮች አንዳንድ ግዴታዎችን ሲጥሉብህ አንተም ስትታዘዛቸው የአምላክን ዝግጅት አከበርክ ማለት ነው። ለወላጆችህ ካልታዘዝክ የአምላክን የአደረጃጀት ሥርዓት ንቀሃል ማለት ነው። ይህም የአንተም ሆነ የወላጆችህ ፈጣሪ ከሆነው አምላክ ጋር መጋጨት ማለት ነው! በግጭቱ ማን ተሸናፊ እንደሚሆን ታውቃለህ። ስለዚህ ለወላጆችህ አመራር የምትሰጠው ምላሽ የእነርሱ የበላይ ለሆነውና ለእርሱ የመገዛት ግዴታ ላለባቸው ለይሖዋ አምላክ ያለህን ስሜት ያንጸባርቃል።
12 ለዚህም ነው የአምላክ ቃል “በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዓይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል። አሞራዎችም ይበሉአታል” በማለት የሚናገረው። አዎን፤ ወጣቶች ለወላጆች የተሳሳተ ዝንባሌ ማሳየታቸው ሕይወታቸውን ሊያሳጣቸው ይችላል። — ምሳሌ 30:17
የበታች ሆኖ ከመገዛት የሚገኝ ትምህርት
13–17. (ሀ) ወላጆችህን ማክበርንና መታዘዝን መማርህ ወላጅ በምትሆንበት ጊዜ ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው? (ለ) በትምህርት ቤትም ሆነ ተቀጥረህ በምትሠራበት ጊዜ ሊረዳህ የሚችለውስ እንዴት ነው? (ሐ) ከሁሉም በላይ ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና እንዴት ይነካዋል?
13 ወደፊት ለአካለ መጠን ስትደርስና ምናልባትም የራስህ ገላትያ 6:7) አሁን ያለህበትን የበታችነት ቦታ እንዴት መወጣት እንደምትችል ተማር። ይህም ትልቅ ስትሆን ምናልባትም ወላጅ ስትሆን የሚመጣውን ኃላፊነት እንድትወጣ ይረዳሃል።
ቤተሰብ ስትመሠርት ልጆችህ እንዲያከብሩህና እንዲታዘዙህ አትፈልግምን? ይሁን እንጂ አንተ ወላጆችህን ማክበርና መታዘዝ ካልተማርክ ልጆችህ እንደዚህ ያለውን አክብሮት እንዲሰጡህ በተሳካ ሁኔታ የምታሰለጥናቸው ይመስልሃልን? የምታጭደው የዘራኸውን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (14 በተጨማሪም ለወላጆችህ አፍራሽ ዝንባሌ የምታሳድግ ከሆነ ይህ በኋላ በምታደርገው ሌሎች ነገሮችም ሊገለጽ ይችላል። ለምሳሌ ተቀጥረህ የምትሠራ ቢሆን አሠሪህ በአንተ ላይ ያለው ሥልጣን ሁልጊዜ ቅር ያሰኝሃልን? የምትሠራውን ሥራ ሲሰጥህ እሺ ብለህ ለመቀበል ያስቸግርሃልን? ስለ ሥራህ አዘውትረህ ታማርር ይሆን? አብረሃቸው ለምትሠራው ሰዎችስ የሚኖርህ ዝንባሌ ምን ይሆናል? ሁልጊዜ በእነርሱ የምታማርርና ለሚያደርጉልህ ነገሮች ምንም የማታመሰግን ሆነህ ትገኝ ይሆናል። ወይም የንግድ ሙያ ለመማር ወደ አንድ ትምህርት ቤት ብትገባ ወይም በሙያው ላይ ስልጠና ቢሰጥህ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከአስተማሪህ የበለጠ እንደምታውቅ ይሰማህ ይሆናል። እነዚህ ዝንባሌዎች ሁሉ በቀላሉ ብዙ ሐዘንና ችግር ሊያስከትሉብህ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ቀደም ብለህ ለወላጆችህ ያሳደግኸው የተሳሳተ ዝንባሌ ፍሬ ሊሆን ይችላል።
15 ስለዚህ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ያሉትን እውነታዎችና በእርሱም ውስጥ ያለህን ቦታ ተቀበል። ይህ የአምላክ መንገድ እንደሆነና የእርሱ መንገድም ከሁሉ የተሻለ መሆኑን ተቀበል።
16 ነገር ግን በወጣትነት ዕድሜህ በቤተሰብ ውስጥ ያለህን ተገቢ ቦታ ለመቀበል እምቢ የምትል ከሆነ ችግር እየጋበዝክ ነው። ይህም ከወላጆችህና ከሌሎች ጋር ያለህን ዝምድናና የወደፊቱን ሕይወትህን በመንካት ብቻ አያበቃም። ከሁሉ የበለጠ ከአምላክ ጋር ያለህን አቋም ያበላሸዋል። እርሱ በሚያመጣው አዲስ ሥርዓት ውስጥ መኖርህን ወይም ይህ ክፉ የነገሮች ሥርዓት በቅርቡ ሲጠፋ ከመኖር ውጭ መደረግህን የሚወስነው ምሳሌ 3:1, 2
እርሱ ነው። “ልጄ ሆይ፣ ሕጌን አትርሳ፣ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ። ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ይጨምሩልሃልና” ለሚለው የልመና ጥሪ እሺ የሚል ምላሽ ስጥ። —17 የሰማያዊ አባታችንን ትእዛዝ የሚፈጽሙና ሕጉንም የማይረሱ ሰዎች ስለሚያገኙት ሽልማት እስቲ አስብ። ሽልማቱ “ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ” ነው። አንተስ የምትፈልገው ይህን ነውን? ረጅም ዘመን ለመኖርና ሰላማዊና ደስተኛ ኑሮ ለማግኘት ትመኛለህን? እንግዲያውስ ወላጆችህን እንድትታዘዝ አምላክ የሚሰጥህን ማበረታቻ በመስማት ይህን እንደምትፈልግ አረጋግጥ።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 76 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ለወላጆችህ የሚገባቸውን አክብሮት ትሰጣቸዋለህን?