ጋብቻህ ሊሠምርልህ ይችላልን?
ምዕራፍ 20
ጋብቻህ ሊሠምርልህ ይችላልን?
1–4. (ሀ) አንድ ሰው ወደፊት የሠመረ ትዳር እመሠርት ይሆንን ብሎ አጥብቆ ለማሰብ ጥሩ ምክንያት ያለው ለምንድን ነው? (ለ) የሠመረ ጋብቻ ለመመሥረት ስለ ምንጩ መታወቅ ያለበት ምንድን ነው? ለምንስ? (ዘፍጥረት 2:21–24፤ ማቴዎስ 19:4–6)
ለማግባት የምትፈልግበት ጊዜ ሲደርስ ትዳርህ የሠመረ እንዲሆን መመኘትህ ያለ ነገር ነው። በፍጥነት እያደገ ካለው የፍቺ ቁጥር አንፃር ስትገመግመው አንተም የተሳካ ጋብቻ ለመመሥረት ያለህ ተስፋ የመነመነ ሊመስል ይችላል። በአንዳንድ ቦታዎች የፍቺው ቁጥር ከጋብቻው ቁጥር እኩል ለመሆን ተቃርቧል! ታዲያ ብታገባ ችግሮች የጋብቻ ደስታህን እንዳያበላሹት ለመከላከል የምትችለው እንዴት ነው?
2 የጋብቻ ምንጭ ማን መሆኑን ማወቅህ ስለ ጋብቻ ችግሮችም ሆነ ስለ መፍትሔው ብዙ ሐሳብ ለማግኘት ይረዳሃል። ብዙ ሰዎች ጋብቻን የጀመረው ሰው እንደሆነ፤ ማለትም በጥንት ጊዜ ሰዎች የፈለሰፉት ነገር እንደሆነ ያምናሉ። ይሁን እንጂ በዛሬው ጊዜ ላለው የቤተሰብ መፈራረስ መንስኤው ይህ አስተሳሰብ ነው። ለምን? ምክንያቱም ለጋብቻ ችግሮች የሚረዳ ከሁሉ የበለጠውን ምክር እንደማያስፈልግ በመቁጠር ወደ ጐን ገሸሽ ስለሚያደርገው ነው።
3 ጋብቻ በእርግጥ ከፍ ካለ ምንጭ የተገኘ ነው። የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ከአባለ ዘር ጋር ፈጥሮ በጋብቻ ያጣመራቸው ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክ ራሱ ነው። በተጨማሪም አምላክ ጋብቻን የተሳካ ለማድረግ የሚረዱ መመሪያዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስመዝግቧል። ትዳር ስትመሠርት ደስታ የሚያመጣልህ እነዚህን መመሪያዎች አጥብቀህ መከተልህ ነው።
4 ከረጅም ጊዜ ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ የነበራቸው ሰዎች ጋብቻቸው እንደ ፈረሰ በመናገር አንዳንድ ሰዎች ተቃውሞ ያሰሙ ይሆናል። የፍቺ ቁጥር እየጨመረ የሄደው ደስታ በታጣበት ትዳር ውስጥ ተቻችለው ለመኖር ፈቃደኛ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ስለመጣ ነው ይላሉ። ይህ ክርክር በመጠኑ እውነትነት አለው። በሚልዮን የሚቆጠሩ በትዳራቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች እውነትም መጽሐፍ ቅዱስ አላቸው ። ይሁን እንጂ አንብበውታልን? በይበልጥም ደግሞ በሕይወታቸው ውስጥ መሠረታዊ ሥርዓቶቹን በሥራ ላይ አውለዋቸዋልን ? ሐቁ ግን መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ባልና ሚስት የቤተሰብ ችግራቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈቱ ማስቻሉ ነው። በጋብቻህ ደስተኛ ለመሆን የምትፈልግ ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር አንተንም ሊረዳህ ይችላል።
በጋብቻ ውስጥ የሚገኝ አስደሳኝ የፆታ ግንኙነት
5–10. (ሀ) ብዙ ሰዎች በፆታ ግንኙነት ስለሚገኝ ደስታ ያላቸው የተጋነነ አመለካከት ምንድን ነው? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስ ራስ ወዳድ በመሆን ፈንታ ሰጪ ስለመሆን የሰጠውን ምክር በሥራ ላይ ማዋል ባልና ሚስት ከዚህ የጋብቻ ግንኙነት እርካታ እንዲያገኙ የሚረዳቸው እንዴት ነው?
5 የፆታ ግንኙነት ችግር የብዙዎቹ የጋብቻ ችግሮች መንስዔ ነው ሲባል ሳትሰማ አትቀርም። ነገሩ እውነት ነው። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ በመገናኛ ብዙሃን በኩል በሚቀርቡት የተጋነኑ አመለካከቶች ምክንያት ነው። በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና ፊልሞች “ፍቅር ይዟቸው ከዚያ በኋላ ሁልጊዜ በደስታ ስለኖሩ” ወንድና ሴት ያወራሉ። ሥነ ጽሑፎችም በፆታ ግንኙነት የሚገኘውን ደስታ ከልክ በላይ አጋነው በማቅረብ በእውን ሊገኝ ከሚችለው የበለጠ ግምት ያሳድራሉ። ለምሳሌ ያህል አንዲት ወጣት ሚስት “የፆታ ግንኙነት ዓለምን በሙሉ የጨበጡ እንደሚያስመስል በደስታ የሚያስፈነጥዝ አደንዛዥ ዕፅ የሚሆን መስሎኝ ነበር። እንዲህ ስል መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም፤ ቢሆንም የፆታ ግንኙነት ማለት በቃ ይኸው ነው? በእርግጥ ይኸው ብቻ ነው? እያልኩ/ አስባለሁ” በማለት ተናግራለች።
6 በወጣትነትሀ ምክንያት ገና ያላገባህ ብትሆንም የዚች ወጣት ሚስት ችግር ይገባሃልን? የሚያሳስባት ትልቁ ነገር የራሷ የፆታ ግንኙነት እርካታ ብቻ ነበር፤ ሆኖም አልረካችም። የብዙ ሴቶች ስሞታም ይኸው ነው። ባሎቻቸው በፆታ ግንኙነት አያረኳቸውም። አንዲት ሚስት እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥማት ምን ማድረግ ትችላለች? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ የሚረዳ ነገር ይናገራልን? ቀጥሎ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ቀጥተኛ ማበረታቻ ልብ በለው:- “ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፣ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባሏ። ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ።” —7 በዚህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር መሠረት ስታገባ በቅድሚያ ሊያሳስብህ የሚገባው ማንን ማስደሰት ነው? ከላይ እንደተጠቀሰችው ሚስት የመጀመሪያ ፍላጎትህ ራስህን ማስደሰት መሆን ይገባዋልን? አይገባውም። ከዚህ ይልቅ የትዳር ጓደኛህን መሆን ይኖርበታል። እዚህ ላይ የሚሠራው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት መስጠት ነው። ቅድሚያ ማግኘት የሚገባው የራስህ ሳይሆን የትዳር ጓደኛህ ደህንነትና ደስታ ነው። ይህም ቀጥሎ ካሉት ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚስማማ ነው:- “እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።” “ፍቅር . . . የራሱን [ጥቅም] አይፈልግም።” — 1 ቆሮንቶስ 10:24፤ 13:4, 5
8 ይሁን እንጂ “ሳገባ ሚስቴን ወይም ባሌን ለማስደሰት መጣሬ የራሴን እርካታ እንዴት ሊጨምረው ይችላል?” ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። እንዲህ ነው:- በጋብቻ ውስጥ የፆታ ግንኙነት ደስታ በአብዛኛው በአእምሮና በልብ ሁኔታ ላይ የተመካ ነው። በመሆኑም የፆታ ግንኙነትን ለባልሽ የጠለቀ ፍቅርን የምታሳዪበት አጋጣሚ አድርገሽ ከተመለከትሽው በአጸፋው ዝምድናችሁ በይበልጥ አስደሳች ሆኖ ታገኚዋለሽ። ያንዲት ሚስት ሐሳብ በራሷ ስሜቶች ላይ ብቻ ካላተኰረ አብዛኛውን ጊዜ ትዝናናለች፤ ከፆታ ግንኙነት ለማግኘት የምትፈልገውን የግል እርካታም የማይቀር ተፈጥሮአዊ ውጤት ሆኖ ሊፈጸምላትና ልታገኘው ትችላለች።
9 በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ አስተማሪ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የራስን ጥቅም መሠዋት በአጸፌታው እርካታን እንደሚያመጣ አመልክቷል። “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው” ብሏል። ይህ መሠረታዊ ሥርዓት በጋብቻ ውስጥ በሚደረገው የፆታ ግንኙነቶችም በኩል በተደጋጋሚ እውነት ሆኖ ተገኝቷል። — ሥራ 20:35 አዓት
10 ስታገቢ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ ማድረጉ ደስታን ሊያስገኝልሽ የሚችልበት ሌላ ምክንያትም አለ። ባልሽ ራስ ወዳድ እንዳይሆን ለመግታትና አንቺ ለሚያስፈልጉሽ ነገሮችና ለምኞትሽ ይበልጡን አሳቢ እንዲሆን ለመገፋፋት ከማንኛውም ነገር የሚበልጠው ይህ ነው። ይህ ለብዙ ጋብቻዎች ሠርቷል። ለመስጠት የመጀመሪያ የሆነው ሰው በአጸፋው መልሶ ይቀበላል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በጋብቻ ውስጥ በፆታ ግንኙነት ረገድ ራስን አለመውደድና ፍቅርን ማሳየትን አጥብቆ ያሳስባል። ስታገቢ ይህን ካስታወስሽ ከባልሽ ጋር ለሚኖርሽ አስደሳች ዝምድና አስተዋጽኦ ያደርግልሻል።
11–15. (ሀ) ሚስት ፍቅራዊ አትኩሮት የሚያስፈልጋት ስለመሆኑ ለማግባት የፈለገ ሰው መገንዘብ ያለበት ነገር ምንድን ነው? (ለ) በዚህ ረገድ ባልየው ስላለበት ኃላፊነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
11 ምናልባት ባሎች ሚስቶቻቸው በጣም “ቀዝቃዛ” በመሆናቸው ለፆታ ግንኙነት ብቁ አይደሉም የሚል ቅሬታ ሲነገር ሰምተህ ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ ችግሩ ከምኑ ላይ እንደሆነ ታውቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ “ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዷቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና . . . ነገር ግን ይመግበዋል ይከባከበውማል” በማለት ይናገራል። (ኤፌሶን 5:28, 29) አዎን፤ ብዙውን ጊዜ ችግሩ ባልየው እዚህ ላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ባለመስማቱ የሚመጣ ነው።
12 ሴቶች በእርግጥ በባሎቻቸው መወደድ ያስፈልጋቸዋልን? አዎ፤ ያስፈልጋቸዋል። የጋብቻ አማካሪዎችም ብዙውን ጊዜ ይህንኑ አጥብቀው ይናገራሉ። ይህ መሠረታዊ የሆነ እውነት ነው። ሚስቶች በእውነት ደስተኞች እንዲሆኑ ከተፈለገ የተወደዱ መሆኤፌሶን 5:33
ናቸው እንዲሰማቸው ያስፈልጋል። ስለዚህ ስታገባ ሞቅ ላለ የጋብቻ መቀራረብ ቁልፉ የሚስትህን የመወደድ ፍላጐት ማሟላት መሆኑን አስታውስ። መጽሐፍ ቅዱስ ባሎችን “ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጐ ይውደዳት” በማለት አጥብቆ ያሳስባል። —13 ይሁን እንጂ ሰብአዊ ነገሮችን እያሟላህ ሚስትህን ማስተዳደርህ በቂ የፍቅር መግለጫ እንደሆነ ይሰማህ ይሆናል። ነገር ግን ሚስቶች የፍቅር መግለጫዎች ከተነፈጋቸው በእነርሱ ላይ ውጤቱ ምን ይሆናል? ከአንዲት ሚስት የተጻፈው የሚከተለው ደብዳቤ ለዚህ ሐሳብ ይሰጥህ ይሆናል:- እንዲህ በማለት ጽፋለች:- “ችግሬ ይህ ነው:- ጥቂት የፍቅር ጭውውት፣ ሙገሳ፣ ምግብ በማበስልበት ጊዜ ሽንጤን በክንዱ አቀፍ ሲያደርገኝ የሚገኘው ስሜት ወይም በጭኑ ላይ መቀመጡ እንደ
ምግብ በጣም ይርበኛል። ያሉኝን ቁሳዊ ነገሮች ሁሉ ለአንድ የፍቅር መተቃቀፍ በለወጥኳቸው ነበር።”14 አዎን፣ ሚስቶች ባሎቻቸው ፍቅር እንዲያሳዩአቸው ያስፈልጋቸዋል። ፍቅር ሲያገኙ የበለጠ እርካታ ስለሚያገኙ ብዙውን ጊዜ በአካልም የበለጠ ማራኪ በመሆን እንደ አበባ ይፈካሉ። መወደድ እንዲያስፈልጋቸው ተደርገው ተፈጥረዋል። አምላክ ባሎች ሚስቶቻቸውን መውደድ አለባቸው ብሎ አጥብቆ የሚያሳስባቸውም ለዚህ ነው። ዛሬ በብዙ ጋብቻዎች ውስጥ ለሚገኘው የደስታ መጥፋት ዋነኛው መንስኤ ይህን ምክር ተግባራዊ አለማድረግ ነው። እንዲህ የሆነው ለምንድን ነው?
15 ምክንያቱም የባሏ ርኅራኄና ፍቅር የራባት ሚስት ስጋት ሊያድርባትና ስለ ሴትነቷ እምነት ልታጣ ስለምትችል ነው። አልፎ ተርፎም በባልዋ ላይ ቂም ልትይዝና እርሱ ችላ እንዳለኝ እኔም እንደዚያው አደርጋለሁ የሚል ብድር የመመለስ ምኞት ሊያድርባት ይችላል።
16–18. (ሀ) ሴቶች እንዴት ቢያዙ የሚወዱ ስለመሆናቸው አንዳንድ ወንዶች ምን የተሳሳተ አስተሳሰብ አላቸው? (ለ) በ1 ጴጥሮስ 3:7 ላይ ያለው ምክር ትርጉሙ ምንድን ነው?
16 ይሁን እንጂ የምታገባትን ሴት በፍቅርና በርኅራኄ መያዝ ወንድነት እንዳልሆነ ይሰማህ ይሆናል። ምናልባትም ሴቶች ዱላ ይወዳሉ ሲባል ሰምተህ ይሆናል። ይህ ግን እውነት አይደለም። እንዲያውም አምላክ ሴትን ሸካራና አስገዳጅ የሆነን ወንድ ሳይሆን ደግና አሳቢ የሆነን ወንድ እንድትተባበር አድርጎ የፈጠራት መሆኑን ባሏ ካልተገነዘበ የፆታ ግንኙነቱ እንኳን ሳይቀር እርካታ የሌለው ብቻ ሳይሆን የሚያስጠላ ሊሆንባት ይችላል።
17 ባሎች ለብዙ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች የተጋለጡ በመሆናቸው ሚስቶቻቸውን እንዴት ማፍቀር እንዳለባቸው ለማወቅ ትምህርት እንደሚያስፈልጋቸው ፈጣሪ ተገንዝቦአል። “እናንተ ባሎች ሆይ ለተሰባሪ ሸክላ እንደሚደረግ ለሚስቶቻችሁ ክብር እየሰጣችሁ ከእነርሱ ጋር በማስተዋል አብራችሁ በመኖር 1 ጴጥሮስ 3:7 አዓት
ቀጥሉ” በማለት ርኅሩኆችና አሳቢዎች እንዲሆኑ የሚያበረታታቸው ለዚህ ነው። ” —18 ፆታ ግንኙነትን በሚመለከት ባል ይህንን መመሪያ መታዘዙ በጣም አስፈላጊ ነው። አምላክ ሴትን እንዴት እንደፈጠራት አውቆ ከዚሁ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይገባዋል። ሴቶች በአካል አብዛኛውን ጊዜ እንደ ወንድ ጠንካራ አይደሉም፣ በስሜትም ባጠቃላይ ከወንድ ይበልጥ ለስላሳና ሆደ–ቡቡ ናቸው። ስለዚህ ባሎች ለተሰባሪ ሸክላ እንደሚደረግ ለሚስቶቻቸው ክብር እንዲሰጡ፣ ለስሜታዊ አሠራራቸው፣ ለአቅመ ውስንነታቸውና ለጠባይ ተለዋጭነታቸው አክብሮት እንዲያሳዩ አምላክ ያዛቸዋል።
ሌሎች ችግሮችን መፍታት
19. ባልና ሚስት በደስታ አብረው እንዲኖሩ ከተፈለገ አንድ ሰው ስለ ሴት ተፈጥሮ ሊያስታውሰው የሚገባው ሌላው ነገር ምንድን ነው? (ቆላስይስ 3:12–14)
19 እንደ እውነቱ ከሆነ የፆታ ግንኙነት በጋብቻ ውስጥ የአምላክ መመሪያዎች በተግባር መተርጎም ከሚኖርባቸው ነገሮች ጥቂቱ ክፍል ብቻ ነው። ስታገባ የሚስትህ የተፈጥሮ ወርኀዊ ዑደት አንዳንድ ጊዜ በአካል፣ በአእምሮና በስሜት ሊነካት እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልግሃል። በዚህን ወቅት በሌላ ጊዜ የማታደርገውን ነገር ትሠራና ትናገር ይሆናል። በዚህ ጊዜ ይህን ከግምት በማስገባት አንዳንድ ጊዜ ሚስትህ በቁጣ ብትናገር ወይም አንዳንድ ነገር በችኮላ ብታደርግ ከልክ ያለፈ ቅሬታ ሊሰማህ አይገባም። ከዚህ ይልቅ እርሷን በደግነት መያዝህን መቀጠል አለብህ።
20–24. (ሀ) አምላክ ሴትን የፈጠራት በጋብቻ ላላት ሚና ብቁ ከሚያደርጓት ከየትኞቹ ጠባዮች ጋር ነው? (ለ) አንዲት ሚስት የባሏን ራስነት በእርግጥ እንደምታከብር ለማሳየት የምትችለው እንዴት ነው? (ሐ) ባል በእውነት አፍቃሪ የሆነ የቤተሰብ ራስ እንዲሆን ከተፈለገ ምን ማድረግ ይፈለግበታል?
20 ሆኖም አሁንም ገና ብዙ ነገር ይቀራል። የተሳካ ጋብቻ ትብብርና የሐሳብ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል። ከዚህ ደረጃ ለመድረስም ከአምላክ ቃል የምታገኘው ማስተዋል ይረዳሃል። የአምላክ ቃል ወንድና ሴት ጥምረታቸው የጋራ ደስታ እንዲያስዘፍጥረት 2:18 አዓት
ገኝ ታስቦ ከተለያዩ ጠባዮችና ኃላፊነቶች ጋር እንደተፈጠሩ ያሳያል። ፈጣሪ ወንድን ከፈጠረ በኋላ “ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” በማለት ተናገረ። —21 ስለዚህ ሁለቱ የተፈጠሩት ባሕርዮቻቸው የሚካካሱ ሆነው አንዱ ከሌላው የቀረውን በማሟላት አብረው የሚሄዱ እንዲሆኑ ነበር። እያንዳንዱ የተፈጠረው አንዱ የጐደለውን ሌላው እንዲያሟላለት ሆኖ ነው። በመሆኑም ሴት የተፈጠረችው ለባሏ ረዳት እንድትሆን ነበር። ከዚህም ሚና ጋር በመስማማት መጽሐፍ ቅዱስ “ሚስቶች ለባሎቻቸው ይገዙ . . . ባል የሚስት ራስ ነውና” በማለት አጥብቆ ያሳስባል። በመጨመርም መጽሐፍ ቅዱስ “ሚስት ለባልዋ የጠለቀ አክብሮት ይኑራት” ይላል። (ኤፌሶን 5:22, 23, 33 አዓት ) ይህም ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም በቤተሰቡ ውስጥ ሚስቱ እንደ ራስ አድርጋ የምታከብረው ሰው ከሌለ አብዛኛውን ጊዜ ብጥብጥና ዝብርቅ ይፈጠራል።
22 በዛሬው ጊዜ የሴቶች ከወንዶች ጋር መፎካከርና መወዳደር የተለመዱ ነገሮች ሆነዋል። እነዚህም ጠባዮች የቤተሰብ ችግሮች ምንጭ እንደሆኑ የጋብቻ አማካሪዎች ተገንዝበውታል። ስለዚህ ሴት ብትሆኚና ብታገቢ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ ብታውይው ጥበበኛ ትሆኛለሽ። ባልሽ እንደሚገባው
ያህል የመሪነት ተግባሩን ካላከናወነ ራስሽን እንዲህ ብለሽ ለመጠየቅ ትፈልጊያለሽ:- በቤተሰቡ ውስጥ ተገቢ ድርሻውን እንዲያሟላ እርሱን ለማበረታታት ከአሁኑ የበለጠ ጥረት ማድረግ እችላለሁን? ሐሳብና መመሪያ እንዲሰጠኝ እጠይቀዋለሁን ? አመራር እንዲሰጠኝ እርሱን እንደምጠባበቅ አሳያለሁን? የሚሠራውን ነገር ከማንኳሰስ እቆጠባለሁን? በትናንሽ ጉዳዮች ውሳኔ ለማድረግ ወይም በቤተሰቡ ጉዳይ አመራር ለመስጠት ፈቃደኝነቱን ሲገልጽ ለዚህ አድናቆቴን እገልጻለሁን?’23 ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ በማዋል ጋብቻው እንዲሳካ ለማድረግ በሚያመች ቦታ ላይ ያለው በተለይ ወንዱ ነው። ወደፊት ካገባህ ይህን አስታውስ። በዚያን ጊዜ ባል እንደመሆንህ መጠን የቤተሰብህ ራስ ብትሆንም ይህ አምባገነን ለመሆን አይፈቅድልህም፤ ምክንያቱም የአምላክ ቃል “ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርሷም ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ” በማለት ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲወዷቸው ያዛቸዋል። (ኤፌሶን 5:25) ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ የምታውል ከሆነ ለምታገባት ሴት ስትል በፍቅርና በፈቃደኝነት የራስህን ጥቅሞች ትሠዋለህ። ውሳኔዎች ከማድረግህ በፊት ሐሳቧን፣ የምትወደውንና የምትጠላውን ከግምት ብታስገባውና እንዲያውም ጉዳዩ እምብዛም አሳሳቢ በማይሆንበት ጊዜ ለምርጫዋ ቅድሚያ ብትሰጥ መልካም ነው። እንዲህ ካደረግህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያዘውን ፍቅር እና አክብሮት ታሳያለህ።
24 አንድ ቀን የምታገባበት ጊዜ ሲመጣ እንደዚህ አድርገህ የአምላክን ምክር ተግባራዊ ካደረግህ በጋብቻህ ውስጥ ሰላምና ስምምነት ታገኛለህ። ከዚህም በላይ ፈጣሪ ይህ ታላቅ ዝግጅት ለሰው ዘር እንዲያመጣ አስቦት የነበረውን ዓላማ የሚፈጽምና እርካታ ያለበት የሠመረ ትዳር ይሆንልሃል።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 161 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሚስት ደስተኛ እንድትሆን ከተፈለገ እንደምትወደድ ሊሰማት ያስፈልጋል
[በገጽ 164 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የትዳር ጓደኛ ሲናገር ከልብ ማዳመጥ ለደስተኛ ጋብቻ በጣም አስፈላጊ ነው