አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ድሃዋ መበለት
አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ድሃዋ መበለት
ኢየሱስ፣ ሀብታሞች በቤተ መቅደሱ የመዋጮ ዕቃ ውስጥ ገንዘብ ሲከቱ እየተመለከተ ነው። ከሕዝቡ መካከል አንዲት ድሃ መበለት “አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች” ስትከት አየ። (ሉቃስ 21:2) ኢየሱስ ይህች ሴት ያሳየችውን ልግስና አድንቆ ተናገረ። ለምን? ምክንያቱም ሌሎች መዋጮ ያደረጉት “ከትርፋቸው” ሲሆን እሷ ግን የከተተችው “በድሃ አቅሟ ያላትን ሁሉ፣ መተዳደሪያዋን በጠቅላላ” ነው።—ማርቆስ 12:44
አንተም እንደዚህች ሴት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ ትሰጣለህ? ጊዜህንና ገንዘብህን በአምላክ አገልግሎት ላይ ለማዋል ፈቃደኛ ነህ? ድሃዋ መበለት እንዳደረገችው አንተም የአምልኮ ቦታዎችን ለመንከባከብ የሚሆን ገንዘብ ማዋጣት ትችላለህ? ከዚህም በተጨማሪ በጊዜህና በገንዘብህ ተጠቅመህ ስለ ይሖዋ አምላክ እንዲማሩ ሰዎችን መርዳት ትችላለህ። ይሖዋ መበለቷ ሴት የእሱን አገልግሎት ለመደገፍ የሰጠችውን አነስተኛ መጠን ያለው መዋጮ የተመለከተ ከመሆኑም በላይ ባደረገችው ነገር ተደስቷል። አንተም ከሁሉ በላይ ቅድሚያ የምትሰጠው የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ከሆነ ይሖዋ ይደሰትብሃል እንዲሁም ይረዳሃል።—ማቴዎስ 6:33