የዔድን ገነት በመላው ምድር ላይ እንደገና ትቋቋማለች
ምዕራፍ 21
የዔድን ገነት በመላው ምድር ላይ እንደገና ትቋቋማለች
1. (ሀ) የዔድን የአትክልት ቦታ የምትመለሰው በምን መንገድ ነው? የተወሰነውን የምድር ክፍል ብቻ የምትሸፍን የማትሆነውስ ለምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ ለክፉ አድራጊው የተናገራቸው ቃላት ምን ያመለክታሉ?
የዔድን የአትክልት ቦታ “የተድላ ገነት” ነበረች፤ በዚህም መንገድ እንደገና ትቋቋማለች። (ዘፍጥረት 2:8 ዱዌይ ቨርሽን) የመጀመሪያዋ ገነት የተወሰነን የምድር ክፍል ብቻ ትሸፍን ነበር። ይሁን እንጂ በቁጥር እያደገ የሚሄደው ሰብአዊ ቤተሰብ ዳር ድንበሯን በሁሉም አቅጣጫ እንዲያሰፋውና በመጨረሻው ገነት ጠቅላላውን ምድር ሸፍና አስደሳች የተፈጥሮ ውበት እንድታለብሳት የይሖዋ ዓላማ ነበር። (ዘፍጥረት 1:26–28፤ 2:8, 9, 15) በጌተሰማኒ በአጠገቡ ለሞተው የሐዘኔታ መንፈስ ያሳየ ክፉ አድራጊ የተነገሩት የኢየሱስ ቃላት ገነት እንደገና የመቋቋሟ ሂደት ብዙ ከገፋ በኋላ ከሞት እንደሚነሣ አረጋግጠውለታል። በዚያን ጊዜ በምድር መልክ ላይ የተደረገውን አስደሳች ለውጥ ይመለከታል። (ሉቃስ 23:43) እንደገና በምትቋቋመዋ ምድር አቀፍ ገነት ምን ትመስል ይሆን? ከመጀመሪያዋ የዔድን ገነት የምትለየውስ እንዴት ይሆን?
2. (ሀ) በመጀመሪያዋ የዔድን የአትክልት ቦታ ውስጥ የነበረ ነገር ግን በምድር አቀፍዋ ገነት ውስጥ የማይኖረው ምንድን ነው? (ለ) አምላክ በአንድ ነጠላ ዛፍ አማካኝነት የሰውን ዘር ታዛዥነት አይፈትንም ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ የሚሆነው ለምንድን ነው?
2 በፊታችን ስላሉት ክብራማ ነገሮች በሚገልጹት የመግቢያ ትንቢቶች ላይ እንደገና በተቋቋመችው ምድር አቀፍ ገነት ውስጥ አንድ ነገር እንደጐደለ እናያለን። ይህ ነገር ምንድን ነው? “በገነት መካከል” ዘፍጥረት 2:17፤ 3:3) ይህ አንድ ነጠላ ዛፍ እንደ ነበረ ከመግለጫዎቹ መረዳት ይቻላል። እንደገና በምትቋቋመው ምድር አቀፍ የዔድን ገነት መለኮታዊ ዕገዳ ያለበት እንደዚህ ያለ አንድ ዛፍ ይኖራል ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ ይሆናልን? አይሆንም። አለዚያ በምድር ዳርቻ አካባቢዎች የሚኖሩት ሰዎች የልዑሉን አምላክ ትእዛዝ በማፍረስ ከፍሬው ለመብላት እንዲችሉ ይህ ዛፍ ወደሚገኝበት ቦታ ይኸውም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመሄድ በጣም ረጅም ጉዞ ማድረግ ይጠይቅባቸው ነበር።
የነበረው “መልካምና ክፉን የሚያስታውቅ ዛፍ” ነው። (3. እንደገና በምትመለሰዋ ገነት ውስጥ ምን ሌላ ነገር አይኖርም?
3 ከዚህም በላይ፣ በዚህ ቦታ የአምላክን ትዕዛዞች ችላ በማለት ከሚያስጎመጀው ፍሬ እንዲወስዱ ወደ ዛፉ የሚቀርቡትን ለመጋበዝ ‘የሚናገር’ እባብ አይኖርም። እንዲሁም በእባብ የሚጠቀምና ማንኛውም ተመልካች የፈጣሪን ትእዛዝ እንዲያፈርስ የሚጋብዝና አደገኛ ውጤቶች እንዲደርስበት የሚያደርግ ክፉ መንፈስ አይኖርም።
4. ሰይጣን ዲያብሎስ ‘በሰላሙ መስፍን’ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት ከአካባቢው የሚጠፋው ለምንድን ነው?
4 በዔድን ገነት ውስጥ ‘ከሚናገረው’ እባብ በስተጀርባ የነበረው የማይታየው መንፈሳዊ ፍጡር ‘በሰላሙ መስፍን’ በኢየሱስ ክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት በቦታው አይኖርም። ይህ ክፉ ሰይጣን ዲያብሎስ ከአርማጌዶን በኋላ ሙሉ በሙሉ በጥብቅ እገዳ ስር ይደረጋል። ራእይ 20:2, 3 “የሰላሙ መስፍን” “ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን የቀደመውን እባብ ” እንደሚይዘውና ለአንድ ሺህ ዓመት አስሮ ወደ ጥልቁ እንደሚጥለው ይነግረናል።
እንደገና በምትቋቋመው ገነት ውስጥ የሚኖር እውነተኛ ሰላምና ዋስትና ያለው ኑሮ
5. እንደገና በምትቋቋመዋ ገነት ውስጥ እውነተኛ ሰላምና ዋስትና ያለው ሕይወት በመላው ምድር ላይ የሚስፋፋው ለምንድን ነው?
5 ከዚያ በኋላ እንዴት ያለ ሰላምና ዋስትና ያለው ኑሮ ይከተላል! ሰይጣን “የዓለም ገዥ” በመሆን በሰው ዘሮች ላይ ያለው ተጽዕኖና ገዥነት ይቀራል! (ዮሐንስ 14:30) የሰይጣን የአጋንንት ጭፍራ ወደ ጥልቍ ሲጣሉ፣ ምድር በመጨረሻው ከሁሉም ዓይነት የመናፍስትነት ድርጊቶች ከአስማትና ከጥንቆላ አዎን ይሖዋ ከሚጸየፈው ከሁሉም ዓይነት አጋንንታዊ ሥራ ነፃ ትሆናለች።— ዘዳግም 18:10–12
6, 7. (ሀ) የእንስሳት ፍጥረት ለሰዎች አስጊ የማይሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ይህንን በሚመለከት የትኛው ትንቢት ቃል በቃል ይፈጸማል?
6 እንደገና በምትቋቋመዋ ገነት ውስጥ የእንስሳት ፍጥረት ጉዳት አያደርሱም፤ ለነዋሪዎቹም አስጊ አይሆኑም። በኢሳይያስ 11:6–9 ላይ የተገለጸው አስደሳች መግለጫ ቃል በቃል እንደሚፈጸም ለመጠበቅ እንችላለን:-
በዝቅተኛ ፍጥረቶች ላይ በመጠኑ ጠፍቶ የነበረውን ሰዎችን የመፍራት ባሕርይ አምላክ ይመልሳል። በዚህም ምክንያት ‘በሰላሙ መስፍን’ የሺህ ዓመት ግዛት ውስጥ ስለሚኖረው የእንስሳት ሕይወት7 “ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፣ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል። ላምና ድብ አብረው ይሰማራሉ፣ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል። የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፣ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል። በተቀደሰውም ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጎዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር [ይሖዋን (አዓት)] በማወቅ ትሞላለችና።”
8. የእባብ መብል “ትቢያ ይሆናል” የሚለው ትንቢታዊ አነጋገር ትርጉም ምንድን ነው?
8 እንደዚህ ያለውን ትንቢት መንፈሳዊ ትርጉም ብቻ ቢኖረውና እንደዚህ ያሉት ነገሮች በምድራዊ ሕይወት ውስጥ ቃል በቃል እንዳይንፀባረቁ ቢያደርግ የአምላክን አቋም ተለዋዋጭ ያደርገዋል። በተመሳሳይም ኢሳይያስ 65:25 “ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፣ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፣ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል” በማለት ይነግረናል። ይህ ሲባል የእባብ ዘር ከምድር አቀፍዋ የዔድን ገነት ይጠፋል ማለት ነውን? አይደለም። የእባብ መብል “ትቢያ ይሆናል” ሲባል በሆዳቸው የሚሳቡ ፍጥረታት ዝርያዎች እንደገና ለሰብዓዊ ፍጥረታት ሕይወትና መልካም ጤንነት ፈጽሞ አስጊ አይሆኑም ማለት ነው። ልክ አዳም ለሁሉም እንስሳት ያለ ፍርሃት ስም ባወጣበት ጊዜ እንደነበረው የሰው ዘር በምድር ላይ በሚንቀሳቀሰው ነገር ሁሉ ላይ የሚገዛ ጌታቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።— ዘፍጥረት 2:19, 20፤ ሆሴዕ 2:18 አዓት። (በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ሆሴዕ 2:20)
9, 10. መዝሙር 65 እና ኢሳይያስ 25:6 ‘በሰላሙ መስፍን’ አገዛዝ ሥር ስለምትሆነዋ ምድር ምን ይተነብያሉ?
9 የዚያች የምድር አቀፍ የዔድን ገነት ውበትና ብልጽግና ልንገምተው ከምንችለው በላይ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ በሚናገረው በ65ኛው መዝሙር ውስጥ አንድ ትንቢታዊ መግለጫ ይሰጠናል። ይህ መዝሙር በከፊል እንዲህ ይላል:- “ምድርን ጎበኘሃት አጠጣሃትም፣ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፣ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተሞላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ፣ እንዲሁም [ምድርን] ታሰናዳለህና።” በዚያን ጊዜ በድርቅ ፋንታ ‘ጥሩ ዝናብ’ ይኖራል። (መዝሙር 65:1, 9–13) ለሁሉም የምድር ነዋሪዎች የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል።
10 ይህ መትረፍረፍ በኢሳይያስ 25:6 ላይም ተተንብዮአል:- “የሠራዊት ጌታ [ይሖዋ (አዓት)] ለሕዝቡ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ ያረጀ የወይን ጠጅ ቅልጥምም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፣ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።” እንደገና የተመለሰችው ገነት ነዋሪዎች ልብን የሚያጠነክሩና ፊትን የሚያበሩ የሰቡ ነገሮችን ይበላሉ። በደንብ የበሰለና የጠራ የወይን ጠጅ በመጠጣት ልባቸውን ደስ ያሰኛሉ። (መዝሙር 104:14, 15) ‘በሰላሙ መስፍን’ የሺህ ዓመት ግዛት ውስጥ ምንም የምግብ እጥረት አይኖርም! በዚህ ፋንታ “መትረፍረፍ” ይሆናል።— መዝሙር 72:16
የቋንቋና የአየር ጠባይ ለውጥ
11. በቋንቋ ምን ለውጥ ይደረጋል? ይህስ የሰውን ዘር እንዴት ይነካል?
11 ምድር አቀፍዋ ገነት ብዙ ቋንቋ በመኖሩ ምክንያት በሚመጣ ዝብርቅ ችግር ያጋጥማት ይሆንን? አይሆንም፤ ምክንያቱም ‘የሰላሙ መስፍን’ “ኃያል አምላክ” ተብሎም ተጠርቷል። (ኢሳይያስ 9:6) ስለዚህ የባቤል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የጀመረውን የቋንቋ ዝብርቅ ሊያስተካክለው ይችላል። (ዘፍጥረት 11:6–9) ‘የዘላለሙ አባት’ ምድራዊ ልጆች በሙሉ የጋራ ቋንቋቸው የሚሆነው ምንድን ነው? የፊተኛው አዳም የመጀመሪያ ቋንቋ ማለትም ይሖዋ የሰጠው ቋንቋ ይሆንን? ሳይሆን አይቀርም። በዚህም ይሁን በዚያ ሁሉም የቋንቋ አጥሮች ይወገዳሉ። የትም ቦታ ለመጓዝና ከሰዎች ጋር ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጥ ትችላለህ። እነርሱ የሚናገሩትን ለመረዳት ትችላለህ፤ እነርሱም አንተ የምትናገረውን ሊረዱ ይችላሉ። ለሁሉም የሰው ዘር አንድ ቋንቋ ይሆናል፣ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስም በዚሁ ቋንቋ መዘጋጀቱ ተገቢ ይሆናል። (ከሶፎንያስ 3:9 ጋር አወዳድር) “ውኃ ባሕርን እንደሚከድን” በዚህ ቋንቋ ምድር ሁሉ በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።— ኢሳይያስ 11:9
12. ዘካርያስ 14:9 የሚፈጸመው እንዴት ይሆናል?
12 በዚያን ጊዜም “[ይሖዋ (አዓት)] አንድ፣ ስሙም አንድ ይሆናል” የሚሉት የዘካርያስ 14:9 ቃላት ይፈጸማሉ። ይሖዋ ብቻውን እንደ አንድ እውነተኛ አምላክ ይመለካል። ‘በሰላሙ መስፍን’ በሚመራው በዚያ የይሖዋ መንግሥት “ቀን” አምላክ የስሙን ትክክለኛ አጠራር ይገልጣል። ከዚያ በኋላ በምድር ላይ የሚኖረው ሁሉም ሰው ያንን ቅዱስ ስም በአንድ መንገድ ብቻ ይጠራል። ስሙ አንድ ይሆናል።
13. የአየር ጠባይ፣ ነፋስና ማዕበሎች ለምድር ነዋሪዎች አስጊ የማይሆኑት ለምንድን ነው?
ማርቆስ 4:37–41) ምድር አቀፍዋ የዔድን ገነት የአየሩ ጠባይ ፍጹም ትክክል ይሆንላታል። መላዋ ምድር ሁሉም የሰው ዘሮች ዋስትና ያለው ሕይወት አግኝተው ፍጻሜ ለሌለው ጊዜ ለመኖር አስደሳች መብት ሊያገኙ ወደሚችሉበት የደስታ ገነትነት ትለወጣለች።
13 ወደፊት የሚኖሩትን የአየር ጠባይና የአካባቢ ለውጦችም ቢሆኑ ‘የሰላሙን መስፍን’ ምድር አቀፍ ገነት በጉጉት የሚጠብቁት ሁሉ ለማወቅ የሚጓጉላቸው ነገሮች ናቸው። ሆኖም አንድ ነገር የተረጋገጠ ነው፤ መላዋ ምድር ለመኖር የምታስደስት ቦታ ትሆናለች። ይህች ገነት አውዳሚ በሆኑ ልዩ ልዩ ማዕበሎችና በኃይለኛ አውሎ ነፋስ የምትረበሽ አትሆንም። ነፋስ፣ ማዕበሎችም ሆኑ አየሩ ሁሉም ‘ለሰላሙ መስፍን’ የሚታዘዙ ይሆናሉ። (14, 15. (ሀ) በራእይ 21:3, 4 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የትኛው ተስፋ ይፈጸማል? (ለ) አምላክ በሰዎች መካከል ድንኳኑን የሚዘረጋው እንዴት ነው? (ሐ) ለዘላለም የሚጠረገው ምን ዓይነት እንባ ነው?
14 በዚያን ጊዜ የኀዘን እንባ ለማፍሰስ ምንም ምክንያት አይኖርም! የይሖዋ ትንቢታዊ ቃል ይህንን ያረጋግጥልናል:- “የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።”— ራእይ 21:3, 4
15 ሰማያት የአምላክ ዙፋን ናቸው፤ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት። (ኢሳይያስ 66:1) ስለዚህ አምላክ ቃል በቃል በምድር ላይ ሊኖር አይችልም። ነገር ግን ከሰው ዘሮች ጋር ድንኳኑን ያደርጋል። በሺው ዓመት ግዛት ወቅት ይሖዋ ክብር በተቀዳጀው ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ተወክሎ ድንኳኑን በሰዎች መካከል ያደርጋል። በእርሱ “የሰላም መስፍን” አማካኝነት የይሖዋ መገኘት መወከሉ ምንኛ ተገቢ ይሆናል! ይህ በኢሳይያስ 7:14 ላይ ለመሲሑ ስለ ተሰጠው አማኑኤል ስለሚለው ስም የተነገሩትን ቃላት ያስታውሰናል። የዚህ ስም ትርጉም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” የሚል ነው። (ማቴዎስ 1:23) አምላክ በውድ ልጁ አማካኝነት ከሰው ዘር ጋር ‘ማደሩ’ ምንኛ የሚያስደስት ይሆናል! በዚያን ጊዜ በዚህ “ኃያል አምላክ” አማካኝነት አስደናቂ ተዓምራቶች ሲደረጉ ስናይ፣ በተለይም የሞቱ ዘመዶቻችን በትንሣኤ ወደ ገነታዊ ሁኔታዎች ሲመለሱ ዓይናችን የደስታ እንባ ማቅረሩ አይቀርም። (ሥራ 24:15) እንደዚህ ያሉት ተዓምራት አምላክ ከሰው ዘር ጋር ለመሆኑና የሐዘን እንባዎችን ለዘላለም ከዓይኖቻችን ለመጥረጉ አስደናቂ ማስረጃ ይሆናሉ።
ወሰን በሌለው አጽናፈ ዓለም ውስጥ ያለች አንዲት ውብ ነጥብ
16. የሙታን ትንሣኤ ገነት መላዋን ምድር ለመሸፈን እስከምትስፋፋ ድረስ መቆየት ያስፈልገዋልን? አብራራ።
16 የመጀመሪያ አዳም ከዚያችው ከዔድን የአትክልት ቦታ ገነትን የማስፋቱን ፕሮጀክት እንዴት እንደሚጀምር ተነግሮት ነበር። በመላው ምድር ላይ ገነትን የማስፋፋቱ የመጀመሪያ ዓላማ ይፈጸማል። ይሁን እንጂ የሙታን ትንሣኤ ገነት በምድር ዙሪያ እስክትስፋፋ ድረስ መቆየት ይኖርበታልን? አይኖርበትም። ለምሳሌ፣ በመጀመሪያው ላይ የሚነሡት ሰዎች የአርማጌዶን ተራፊዎች በሚገኙባቸውና ወደ ገነትነት በለወጡአቸው የምድር ክፍሎች ላይ ይነሣሉ። የሰው ዘሮች ትንሣኤ በአጠቃላይ እየጨመረ ሲሄድ እነዚህ ገነት የሆኑ አካባቢዎች ምድር አቀፍ ገነት እስከሚሆኑ ድረስ ይስፋፋሉ።
17. ስለ ዓለም አቀፍዋ ገነት ምን መግለጫ ተሰጥቶአል?
17 መጭዋ ገነት በአሁኑ ጊዜ ካሉት አስደሳች መናፈሻዎች ወይም የአትክልት ቦታዎች ሁሉ ትበልጣለች። ደማቅ በሆነ ሁኔታ
መላዋ ምድር እንደ አንድ ሰላማዊ ገነት ታብባለች፤ የሰውን ዓይን ብቻ ሳይሆን የፈጣሪንም ዓይን ጭምር ታስደስታለች። ለማየት ደስ የሚያሰኙና የፍጥረትን ሕይወት በፍጽምና ጠብቀው ሊያቆዩ የሚችሉ ቡቃያና ዛፎችን በማፍራት የተዋበች ምድር አቀፍ የዔድን ገነት ትሆናለች። ምድር ለዘላለም በይሖዋ ወሰን የለሽ ዓጽናፈ ዓለም ውስጥ ውብ ነጥብ ሆና ትቀጥላለች። በአንድነት የተባበረው ሁሉም የሰው ዘር ምድርን ውብ ስፍራ አድርጎ ለመጠበቅ ግዴታና መብት ይኖረዋል።18. ሁሉም ወንዶችና ሴቶች እንደ ወንድማማችና እህትማማች ሆነው በአንድነት በሰላም እንደሚኖሩ እንዴት እናውቃለን?
18 የዚህ አምላካዊ የሆነ ሰብዓዊ ቤተሰብ አባሎች በሙሉ “የዘላለም አባት” የሆነው “የሰላም መስፍን” ልጆች ስለሚሆኑ በንጽሕና እንደ ወንድማማችና እኅትማማች በመሆን በአንድነት በሰላም ይኖራሉ። ስለዚህም ወንዶች እህቶቻቸው በሆኑት በሴቶች ላይ የዕብሪት የበላይነት አያሳዩም። በዚህ ፈንታ ሔዋን ፍጹም ለነበረው ባልዋ ለአዳም “ረዳት” እንድትሆን የአምላክ ዓላማ እንደነበረ ሁሉ ፍጹም የሚሆኑት ሴቶችም ይሖዋ አምላክ ለእነርሱ ካለው ዓላማ ጋር በሚስማማ መንገድ ይኖራሉ።— ዘፍጥረት 2:18፤ በተጨማሪም 1 ጴጥሮስ 3:7 ተመልከት።
19. ገነትዋ ምድር በማይታዩት ሰማያት ውስጥ ለሚኖሩት ምን ዓይነት መልክ ይኖራታል?
19 በዚያን ጊዜ ገነታዊቷ ምድር ፍጹም በሆኑ ወንዶችና ሴቶች ስትሞላ የሚኖራት መልክ በማይታዩት ሰማያት ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ ምድር በመጀመሪያ ስትፈጠር ከነበረውና ‘አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት በደስታ ከዘመሩበት ሁሉም የአምላክ ልጆች በጭብጨባ መጮህ ከጀመሩበት’ ጊዜ ይልቅ በጣም ታላቅና አስደሳች ይሆናል። (ኢዮብ 38:7) ከሁሉም በላይ የሆነው አምላክ ይሖዋ በዚያን ጊዜ ክብራማ ዓላማው በፍጹም ሊከሽፍ እንደማይችል ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠለት አምላክ ይሆናል። ሁሉም ምስጋና ለእርሱ ይድረሰው!
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 172, 173 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ቃል በቃል የምትቋቋመዋ ገነት የአምላክ “የእግሩ መረገጫ” የሆነችውን ምድር ታስውባለች