ምዕራፍ 17
‘እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ገንቡ’
“እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን እየገነባችሁ . . . ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ . . . ኑሩ።”
1, 2. በምን ዓይነት የግንባታ ሥራ ላይ እየተካፈልክ ነው? ሥራህ ጥራት ያለው መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
በአንድ የግንባታ ሥራ ላይ በትጋት እየሠራህ ነው እንበል። ግንባታው ከተጀመረ ረዘም ያለ ጊዜ ያለፈ ከመሆኑም በላይ ወደፊትም ይቀጥላል። እስከ አሁን የተሠራው ሥራ ከባድ ቢሆንም የሚያረካ ነበር። ይህን ሥራ የመጣው ቢመጣ ልታቆመው ወይም ልታጓትተው አትፈልግም፤ ምክንያቱም የሥራህ ጥራት የአሁኑንም ሆነ የወደፊት ሕይወትህን የሚነካ ነው። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? እየተገነባ ያለው ሕንጻ አንተው ራስህ ስለሆንክ ነው!
2 ደቀ መዝሙሩ ይሁዳ ራሳችንን መገንባት እንደሚገባን ጠበቅ አድርጎ ገልጿል። ክርስቲያኖች ‘ከአምላክ ፍቅር ሳይወጡ እንዲኖሩ’ ባሳሰበበት ወቅት ‘እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታቸው ራሳቸውን እንዲገነቡ’ በመንገር ይህን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ቁልፍ ነገር አመልክቷል። (ይሁዳ 20, 21) ከአምላክ ፍቅር ሳትወጣ ለመኖር በምታደርገው ጥረት እምነትህን በማጠናከር ራስህን ልትገነባ ከምትችልባቸው መንገዶች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? የዚህን መንፈሳዊ ግንባታ ሦስት ገጽታዎች እንመርምር።
በይሖዋ የጽድቅ መሥፈርቶች ላይ ያለህን እምነት ገንባ
3-5. (ሀ) ሰይጣን ስለ ይሖዋ መሥፈርቶች ምን ዓይነት አመለካከት እንዲኖርህ ይፈልጋል? (ለ) ስለ አምላክ የጽድቅ መሥፈርቶች ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ይህስ በስሜታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርበታል? በምሳሌ አስረዳ።
3 በመጀመሪያ ደረጃ በመለኮታዊ ሕግ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር ያስፈልገናል። ይህን መጽሐፍ ስታጠና ሥነ ምግባርን በሚመለከት ይሖዋ ያወጣቸውን በርካታ የጽድቅ መሥፈርቶች ተምረሃል። ለእነዚህ ዘፍጥረት 3:1-6) ዘዴው በአንተም ላይ ይሠራ ይሆን? ይህ በአብዛኛው የተመካው በአመለካከትህ ላይ ነው።
መሥፈርቶች ያለህ አመለካከት ምንድን ነው? ሰይጣን አታልሎህ የይሖዋ ሕጎች፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ደንቦች ነፃነት የሚገድቡ፣ አልፎ ተርፎም ጨቋኝ እንደሆኑ አድርገህ እንድትመለከታቸው ይፈልጋል። ይህን ዘዴውን በኤደን ገነት ከተሳካለት ጊዜ ጀምሮ ሲጠቀምበት ቆይቷል። (4 ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት፣ በአንድ የሚያምር መናፈሻ ውስጥ በምትዘዋወርበት ጊዜ በረጅም አጥር የተከለለ ቦታ ተመለከትክ እንበል። ወደ ውስጥ ስታይ ቦታው በጣም ያምራል። መጀመሪያ ላይ አጥሩ አላስፈላጊ እንደሆነና ነፃነትህን እንደሚገድብ ይሰማህ ይሆናል። ወደ ውስጥ ትኩር ብለህ ስትመለከት ግን አስፈሪ አንበሳ የሚበላውን ፈልጎ ወዲያ ወዲህ ሲንጎራደድ ታያለህ! አሁን አጥሩ ለአንተ ጥበቃ ሲባል የታጠረ እንደሆነ ትገነዘባለህ። አንተን ለመዋጥ እያደባ ያለ አዳኝ አውሬ አለ? የአምላክ ቃል “የማስተዋል ስሜቶቻችሁን ጠብቁ፤ ንቁዎች ሆናችሁ ኑሩ። ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል” በማለት ያስጠነቅቃል።
5 ሰይጣን ጨካኝ አዳኝ ነው። ይሖዋ በሰይጣን እጅ ውስጥ እንድንወድቅ ስለማይፈልግ ከክፉው “መሠሪ ዘዴዎች” የሚጠብቁንን ሕጎች ሰጥቶናል። (ኤፌሶን 6:11) በመሆኑም በአምላክ ሕጎች ላይ በምናሰላስልበት ጊዜ ሁሉ የሰማዩ አባታችን ለእኛ ያለው ፍቅር በእነዚህ ሕጎች ላይ እንደተንጸባረቀ መገንዘብ ይኖርብናል። የአምላክን ሕጎች በዚህ መንገድ ከተመለከትናቸው ደህንነት የሚያስገኙልን ከመሆኑም በላይ የደስታ ምንጭ ይሆኑልናል። ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ነፃ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ በትኩረት የሚመለከትና በዚያም የሚጸና ሰው . . . ደስተኛ ይሆናል” ሲል ጽፏል።
6. በአምላክ የጽድቅ ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ያለህን እምነት ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው? ምሳሌ ስጥ።
6 በሕግ ሰጪያችንና እሱ የሰጣቸው ሕጎች ባላቸው ጠቀሜታ ላይ ያለንን እምነት ለመገንባት በአምላክ ትእዛዛት ከመመራት የተሻለ መንገድ የለም። ለምሳሌ ያህል፣ ‘የክርስቶስ ሕግ’ እሱ ‘ያዘዘውን ሁሉ’ ለሌሎች እንድናስተምር የሰጠውን ትእዛዝ ይጨምራል። (ገላትያ 6:2፤ ማቴዎስ 28:19, 20) በተጨማሪም ክርስቲያኖች ለአምልኮና እርስ በርሳቸው ለመተናነጽ እንዲሰበሰቡ የተሰጣቸውን ትእዛዝ አክብደው ይመለከቱታል። (ዕብራውያን 10:24, 25) ከዚህም በላይ የአምላክ ትእዛዝ ዘወትር እንዲሁም ደጋግመን ከልባችን ወደ ይሖዋ እንድንጸልይ የተሰጠንን ማሳሰቢያ ያካትታል። (ማቴዎስ 6:5-8፤ 1 ተሰሎንቄ 5:17) እንደዚህ ያሉትን ትእዛዛት ጠብቀን ስንኖር ትእዛዛቱ በእርግጥም የአምላክ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች መሆናቸው ይበልጥ ግልጽ ይሆንልናል። እነዚህን ትእዛዛት መፈጸም በዚህ በችግር በተሞላ ዓለም ውስጥ የትም ልናገኝ የማንችለውን ደስታና እርካታ ያስገኝልናል። ከአምላክ ሕጎች ጋር ተስማምተህ መኖርህ አንተን በግል እንዴት እንደጠቀመህ በምታሰላስልበት ጊዜ በሕጎቹ ላይ ያለህ እምነት ይበልጥ አይጠናከርም?
7, 8. የአምላክን ሕጎች ከዓመት ዓመት እየጠበቁ መኖር አስቸጋሪ ሊሆንባቸው እንደሚችል የሚሰማቸውን ሰዎች የአምላክ ቃል የሚያጽናናቸው እንዴት ነው?
7 አንዳንዶች የይሖዋን ሕጎች ከዓመት ዓመት ጠብቆ መኖር አስቸጋሪ እንደሚሆን የሚሰማቸው ጊዜ ይኖራል። እነዚህ ሰዎች ‘አይሳካልኝ ይሆናል’ ብለው ይሰጋሉ። አንተም አልፎ አልፎ እንዲህ የሚሰማህ ከሆነ የሚከተሉትን ቃላት አስታውስ:- “እኔ [ይሖዋ፣ NW] አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ። ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።” (ኢሳይያስ 48:17, 18) እነዚህ ቃላት ምን ያህል የሚያጽናኑ እንደሆኑ ቆም ብለህ አስበህ ታውቃለህ?
8 እዚህ ላይ ይሖዋ እሱን ብንታዘዝ እንደምንጠቀም እያሳሰበን ነው። ትእዛዛቱን ብንጠብቅ ሁለት በረከቶች እንደምናገኝ ቃል ገብቶልናል። በመጀመሪያ፣ ሰላማችን እንደ ወንዝ የተረጋጋ፣ የተትረፈረፈና የማይቋረጥ ይሆናል። ሁለተኛ፣ ጽድቃችን እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል። አንድ ባሕር ዳርቻ ላይ ቆመህ እየተከታተሉ የሚመጡትን ሞገዶች ብትመለከት ፈጽሞ እንደማይቋረጡ ማስተዋልህ አይቀርም። ወደፊትም ለዘመናት ሞገዶቹ ወደ ባሕሩ ዳርቻ መምጣታቸውን እንደሚቀጥሉ ታውቃለህ። ይሖዋ ጽድቅህ ማለትም ትክክል የሆነውን በማድረግ የምትከተለው አካሄድ ልክ እንደ ባሕር ሞገድ ዘላለማዊ መሆን እንደሚችል ተናግሯል። ለእሱ ታማኝ ሆነህ ለመኖር እስከተጣጣርክ ድረስ እንዲሳካልህ እንደሚረዳህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ! (መዝሙር 55:22) እንደነዚህ ያሉት የሚያጽናኑ ቃላት በይሖዋና በጽድቅ መሥፈርቶቹ ላይ ያለህን እምነት አያጠናክሩልህም?
‘ወደ ጉልምስና ግፋ’
9, 10. (ሀ) ጉልምስና ለክርስቲያኖች ግሩም ግብ የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) መንፈሳዊ አመለካከት መያዝ ደስተኞች እንድንሆን አስተዋጽኦ የሚያደርገው እንዴት ነው?
9 የመንፈሳዊ ግንባታህ ሁለተኛ ገጽታ “ወደ ጉልምስና እንግፋ” በሚሉት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ቃላት ውስጥ ተገልጿል። (ዕብራውያን 6:1) ጉልምስና ለአንድ ክርስቲያን ግሩም ግብ ነው። በአሁኑ ጊዜ ፍጽምናን ማንም ሰው ሊደርስበት አይችልም፤ ጉልምስና ግን ሊደረስበት የሚችል ግብ ነው። ከዚህም በላይ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ በጎለመሱ መጠን ይሖዋን ማገልገል የበለጠ አስደሳች እየሆነላቸው ይሄዳል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
10 አንድ የጎለመሰ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሰው ነው። ነገሮችን የሚያየው ከይሖዋ አመለካከት አንጻር ነው። (ዮሐንስ 4:23) ጳውሎስ “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ሰዎች አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ በሥጋዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው” ሲል ጽፏል። (ሮም 8:5) ሥጋዊ አመለካከት ራስ ወዳድነት የሚንጸባረቅበት፣ አርቆ የማይመለከትና በቁሳዊ ነገሮች ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ያን ያህል ደስታ አያመጣም። መንፈሳዊ አመለካከት ‘ደስተኛ አምላክ’ በሆነው በይሖዋ ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ደስታ ያመጣል። (1 ጢሞቴዎስ 1:11) መንፈሳዊ ሰው ይሖዋን ለማስደሰት ይጓጓል፤ አስቸጋሪ ሁኔታ በሚያጋጥመው ጊዜም ሳይቀር ደስተኛ ነው። ለምን? ምክንያቱም ፈተናዎች ሰይጣን ውሸታም መሆኑን ለማረጋገጥና የአቋም ጽናታችንን ለማጠናከር የሚያስችል አጋጣሚ ይፈጥሩልናል። ይህ ደግሞ የሰማዩን አባታችንን ያስደስተዋል።
11, 12. (ሀ) ጳውሎስ ስለ ክርስቲያኖች “የማስተዋል ችሎታ” ምን ብሏል? ‘ማሠልጠን’ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ምን ትርጉም አለው? (ለ) ሰውነት እንዲጠነክርና ጥሩ የአካል ብቃት እንዲኖረው ምን ዓይነት ሥልጠና ያስፈልገዋል?
11 መንፈሳዊነትና ጉልምስና የሚገኙት በሥልጠና ነው። የሚከተለውን ጥቅስ ተመልከት:- “ጠንካራ ምግብ ግን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት ላሠለጠኑ ጎልማሳ ሰዎች ነው።” (ዕብራውያን 5:14) ጳውሎስ የማስተዋል ችሎታን ‘ስለ ማሠልጠን’ ሲናገር የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል፣ ‘እንደ አንድ የጂምናስቲክ ስፖርተኛ መሠልጠን’ ተብሎ ሊተረጎም የሚችል ሲሆን ቃሉ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በግሪክ ጂምናዝየሞች በሰፊው ሳይሠራበት አይቀርም። እንዲህ ያለው ሥልጠና ምን ነገሮችን ሊያካትት እንደሚችል አስብ።
12 በተወለድንበት ጊዜ አካላችን የሠለጠነ አልነበረም። ለምሳሌ አንድ ሕፃን የእጆቹንና የእግሮቹን እንቅስቃሴ መቆጣጠር አይችልም። በዚህም ምክንያት እጆቹን በደመ ነፍስ ሲያወራጭ አንዳንድ ጊዜ የራሱን ፊት መትቶ ሊያለቅስ ይችላል። ይሁንና በጊዜ ሂደት የሕፃኑ አካል እየሠለጠነ ይመጣል። መጀመሪያ ላይ ይድሃል፣ ትንሽ አደግ ሲል ይራመዳል፣ ቆየት ብሎ ደግሞ መሮጥ ይጀምራል። * የጂምናስቲክ ስፖርተኛን በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል? በሚያስገርም ቅልጥፍናና ማራኪ በሆነ መንገድ በአየር ላይ ሲገለባበጥ እንዲሁም ሲተጣጠፍ ስትመለከት የስፖርተኛው ሰውነት በሚገባ ተቀናጅቶ እንደሚሠራ ማሽን ሆኖ ይታይሃል። ስፖርተኛው ይህን ችሎታ እንዲሁ በአጋጣሚ አላገኘውም፤ በጣም ብዙ ሥልጠና ማድረግ ጠይቆበታል። እንዲህ ያለው ሥልጠና ‘በጥቂቱ እንደሚጠቅም’ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። መንፈሳዊ የማስተዋል ችሎታችንን ማሠልጠን ምን ያህል የበለጠ ጥቅም ይኖረው!
13. የማስተዋል ችሎታችንን ማሠልጠን የምንችለው እንዴት ነው?
13 በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ መንፈሳዊ ሰው በመሆን ለይሖዋ ታማኝ ሆነህ መኖር እንድትችል የማስተዋል ችሎታህን ለማሠልጠን የሚረዱህ ብዙ ነገሮች ተብራርተዋል። በዕለት ተዕለት ሕይወትህ ውሳኔዎች በምታደርግበት ጊዜ መለኮታዊ መመሪያዎችንና ሕጎችን በጸሎት አስብባቸው። ማንኛውንም ዓይነት ውሳኔ ማድረግ በሚኖርብህ ጊዜ ‘ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚያያዙት የመጽሐፍ ቅዱስ ሕጎች ወይም መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው? እንዴትስ በሥራ ላይ ላውላቸው እችላለሁ? በሰማይ ያለውን አባቴን የሚያስደስተው የትኛው ውሳኔ ነው?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ። (ምሳሌ 3:5, 6፤ ያዕቆብ 1:5) በዚህ መንገድ የምታደርገው እያንዳንዱ ውሳኔ የማስተዋል ችሎታህን ይበልጥ ያሠለጥንልሃል። እንዲህ ያለው ሥልጠና ደግሞ እውነተኛ መንፈሳዊ ሰው እንድትሆንና በዚሁ አቋምህ እንድትቀጥል ይረዳሃል።
14. በመንፈሳዊ ለማደግ ምን የማድረግ ጉጉት ሊኖረን ይገባል? ሆኖም ምን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል?
14 ጉልምስና ሊደረስበት የሚችል ግብ ሲሆን መንፈሳዊ እድገት ግን ማቆሚያ የለውም። እድገት በምግብ ላይ የተመካ ነው። በመሆኑም ጳውሎስ ‘ጠንካራ ምግብ ለጎልማሳ ሰዎች ነው’ ብሏል። እምነትህን ለመገንባት የሚያስችልህ ወሳኝ ነገር ጠንካራ የሆነ መንፈሳዊ ምግብ ምሳሌ 4:5-7፤ 1 ጴጥሮስ 2:2) እርግጥ ነው፣ አንድ ሰው እውቀትና አምላካዊ ጥበብ ማግኘቱ እንዲኮራ ወይም እንዲታበይ ምክንያት ሊሆነው አይችልም። ኩራት ወይም ማንኛውም ዓይነት ድክመት በልባችን ውስጥ ሥር እንዳይሰድ ሁልጊዜ ራሳችንን መመርመር ይኖርብናል። ጳውሎስ “በእምነት ውስጥ እየተመላለሳችሁ መሆናችሁን ለማወቅ ዘወትር ራሳችሁን መርምሩ፤ ማንነታችሁን ለማወቅ ራሳችሁን ዘወትር ፈትኑ” ሲል ጽፏል።
15. ፍቅር መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
15 የአንድ ቤት ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላም እንኳ ቤቱን በጥሩ ሁኔታ ለመያዝ መሠራት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ። ጥገናና እድሳት ማድረግ ያስፈልጋል። ሁኔታዎች በሚለወጡበት ጊዜ ደግሞ ተጨማሪ ግንባታ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ወደ ጉልምስና ለመድረስና መንፈሳዊነታችንን ጠብቀን ለመኖር ምን ማድረግ ያስፈልገናል? ከሁሉ በላይ ፍቅር ያስፈልገናል። ለይሖዋና ለእምነት ባልንጀሮቻችን ያለን ፍቅር እያደገ መሄድ ይኖርበታል። ፍቅር ከሌለን እውቀታችንም ሆነ ሥራችን፣ ምንም ትርጉም እንደማይሰጥ የሚረብሽ ድምፅ ከንቱ ይሆንብናል። (1 ቆሮንቶስ 13:1-3) ፍቅርን በማዳበር ወደ ክርስቲያናዊ ጉልምስና መድረስም ሆነ መንፈሳዊ እድገት ማድረጋችንን መቀጠል እንችላለን።
አእምሮህ ይሖዋ በሚሰጠው ተስፋ ላይ ያተኩር
16. ሰይጣን ምን ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖረን ለማድረግ ይጥራል? ይሖዋስ ምን መከላከያ ሰጥቶናል?
16 አሁን ደግሞ የመንፈሳዊ ግንባታህን ሦስተኛ ገጽታ እንመልከት። ራስህን እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ አድርገህ ለመገንባት አስተሳሰብህን መቆጣጠር ያስፈልግሃል። የዚህ ዓለም ገዥ የሆነው ሰይጣን ሰዎች አፍራሽ ወይም አሉታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው፣ ተጠራጣሪዎች እንዲሆኑና ተስፋ እንዲቆርጡ በማድረግ ረገድ የተዋጣለት ነው። (ኤፌሶን 2:2) እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ለአንድ ክርስቲያን እንደ ነቀዝ ነው። የሚያስደስተው ነገር ይሖዋ ይህን ነቀዝ የምንከላከልበት መሣሪያ ሰጥቶናል፤ ይህ መሣሪያ ተስፋ ነው።
17. የአምላክ ቃል የተስፋን አስፈላጊነት የሚያስረዳው እንዴት ነው?
17 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከሰይጣንና ከዚህ ዓለም ጋር ለምናደርገው ትግል የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ የጦር ትጥቅ ይዘረዝራል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከተጠቀሱት መሣሪያዎች አንዱና በጣም አስፈላጊ የሆነው በራስ ቁር የተመሰለው ‘የመዳን ተስፋ’ ነው። (1 ተሰሎንቄ 5:8) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረ አንድ ወታደር የራስ ቁር ሳያደርግ በውጊያ ላይ ቢሰለፍ የጦርነቱ ሰለባ እንደሚሆን ያውቃል። በአብዛኛው የራስ ቁር የሚሠራው ከብረት ሲሆን ከውስጡ የቆዳ ወይም የጨርቅ ገበር ይደረግለታል። በመሆኑም ከጠላት ወገን የሚወረወሩ ፍላጾች ነጥረው እንዲወድቁ በማድረግ ጭንቅላት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ይከላከላል። የራስ ቁር ጭንቅላትን ከአደጋ እንደሚጠብቅ ሁሉ ተስፋም አእምሮህንም ሆነ አስተሳሰብህን ይጠብቅልሃል።
18, 19. ኢየሱስ ተስፋውን አጽንቶ በመያዝ ረገድ ምን ምሳሌ ትቶልናል? እኛስ እሱን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
18 ተስፋውን አጽንቶ በመያዝ ረገድ ዋነኛው ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው። በምድር ላይ ባሳለፈው የመጨረሻ ምሽት ምን ዓይነት መከራ እንደተቋቋመ አስብ። የቅርብ ወዳጁ በገንዘብ አሳልፎ ሰጠው። ሌላው ወዳጁ ደግሞ ከናካቴው አላውቀውም ሲል ካደው። የቀሩትም ትተውት ሸሹ። የገዛ ወገኖቹ ስለጠሉት በሮማውያን ወታደሮች እጅ ተሠቃይቶ እንዲገደል ጠየቁ። ኢየሱስ የደረሰበት መከራ ማናችንም ሊያጋጥመን ከሚችለው መከራ የበለጠ ነው ሊባል ይችላል። ታዲያ እንዲጸና የረዳው ምንድን ነው? ዕብራውያን 12:2 መልሱን ይሰጠናል:- “ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት ላይ እስከመሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።” ኢየሱስ ‘ከፊቱ የሚጠብቀው ደስታ’ ለአፍታ እንኳ ከአእምሮው ጠፍቶ አያውቅም።
19 ኢየሱስ ከፊቱ ይጠብቀው የነበረው ደስታ ምንድን ነው? በመከራ ወቅት መጽናቱ ለይሖዋ ስም መቀደስ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያውቅ ነበር። እንዲሁም ሰይጣን ውሸታም ለመሆኑ አቻ የማይገኝለት ምሥክርነት ይሰጣል። ለኢየሱስ ከዚህ የበለጠ ደስታ ሊሰጠው የሚችል ተስፋ አልነበረም! በተጨማሪም በታማኝነት በመጽናቱ ይሖዋ አብዝቶ እንደሚባርከው፣ ማለትም እንደገና ከአባቱ ጋር የሚሆንበት አስደሳች ጊዜ ከፊት ለፊቱ እንደሚጠብቀው ያውቅ ነበር። ኢየሱስ ባሳለፈው የመከራ ጊዜ ሁሉ ይህን አስደሳች ተስፋ በአእምሮው ይዞ ነበር። እኛም እንዲሁ ማድረግ ይኖርብናል። ልክ እንደ ኢየሱስ እኛም ከፊታችን የሚጠብቀን ደስታ አለ። ይሖዋ እያንዳንዳችን ለታላቅ ስሙ ቅድስና አስተዋጽኦ እንድናደርግ መብት በመስጠት አክብሮናል። ይሖዋን ሉዓላዊ ገዥያችን አድርገን በመቀበልና ምንም ዓይነት ፈተናና መከራ ቢደርስብን ከአባታችን ፍቅር ሳንወጣ በመኖር ሰይጣን ውሸታም መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን።
20. አስተሳሰብህ ሁልጊዜ አዎንታዊ እንዲሆንና ተስፋህ ብሩህ ሆኖ እንዲታይህ ምን ሊረዳህ ይችላል?
20 ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ ወሮታ ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑም ባሻገር ይህን ለማድረግ ይጓጓል። (ኢሳይያስ 30:18፤ ሚልክያስ 3:10) ለአገልጋዮቹ የልባቸውን መሻት መስጠት ያስደስተዋል። (መዝሙር 37:4) ስለዚህ አእምሮህ ከፊት ለፊትህ በሚጠብቅህ ተስፋ ላይ እንዲያተኩር አድርግ። የሰይጣን አሮጌ ዓለም ወራዳ፣ አፍራሽና ጠማማ አስተሳሰብ ፈጽሞ አያሸንፍህ። የዚህ ዓለም መንፈስ ወደ አእምሮህና ወደ ልብህ እየገባ እንደሆነ ከተሰማህ ይሖዋ ‘ከማሰብ ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነውን ሰላም’ እንዲሰጥህ አጥብቀህ ጸልይ። አምላክ ብቻ የሚሰጠው ይህ ሰላም ልብህንና አስተሳሰብህን ይጠብቅልሃል።
21, 22. (ሀ) ‘የእጅግ ብዙ ሕዝብ’ አባላት ምን ዓይነት ክብራማ ተስፋ ይጠብቃቸዋል? (ለ) አንተ ይበልጥ በጉጉት የምትጠባበቀው የትኛው ተስፋ ሲፈጸም ለማየት ነው? ቁርጥ ውሳኔህ ምንድን ነው?
ራእይ 7:9, 14) በዚያን ጊዜ ሰይጣንና አጋንንቱ ስለማይኖሩ፣ አሁን ልንገምተው ከምንችለው በላይ የሆነ ታላቅ እፎይታ እናገኛለን። ደግሞስ አስተሳሰብን የሚበክለው የሰይጣን ተጽዕኖ የሌለበትን ሕይወት ቀምሶ የሚያውቅ ማን አለ? ይህ ተጽዕኖ ከተወገደ በኋላ በኢየሱስና በ144,000ዎቹ ተባባሪ ገዥዎች አመራር ሥር ሆኖ ምድርን ወደ ገነትነት በመለወጡ ሥራ መካፈል ምንኛ አስደሳች ይሆናል! ማንኛውም ዓይነት ሕመምና የአካል ጉዳት ተወግዶ ማየት፣ የሞቱብንን ወዳጅ ዘመዶቻችንን በትንሣኤ መቀበል፣ እንዲሁም አምላክ አስቦልን በነበረው መሠረት መኖር እንዴት የሚያስደስት ነው! ወደ ፍጽምና ስንደርስ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ወሮታ፣ ማለትም በሮም 8:21 ላይ የተገለጸው ‘የአምላክ ልጆች ክብራማ ነፃነት’ ይጠብቀናል።
21 በእርግጥም ዘወትር በአእምሮህ ልታስበው የምትችለው አስደሳች ተስፋ አለህ! ‘ታላቁን መከራ በሕይወት ከሚያልፈው እጅግ ብዙ ሕዝብ’ መካከል ከሆንክ በቅርቡ ስለምታገኘው አስደናቂ ሕይወት አስብ። (22 ይሖዋ ልትገምተው እንኳ ከምትችለው በላይ የሆነ ታላቅ ነፃነት እንድታገኝ ይፈልጋል። ይህን ነፃነት ማግኘትህ የተመካው በታዛዥነትህ ላይ ነው። ታዲያ በየዕለቱ ለይሖዋ ታዛዥ ሆነህ ለመኖር ማንኛውንም ጥረት ብታደርግ የሚያስቆጭህ ይሆናል? እንግዲያው ለዘላለም ከአምላክ ፍቅር ሳትወጣ መኖር እንድትችል እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነትህ ራስህን መገንባትህን ቀጥል!
^ አን.12 የሳይንስ ሊቃውንት ሰውነታችን፣ የተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን ያሉበትን ቦታ የማወቅ እንዲሁም የእጃችንንና የእግራችንን እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ልዩ ችሎታ እንዳለው ይናገራሉ። ለምሳሌ ዓይንህን ጨፍነህ እንኳ በትክክል ማጨብጨብ የምትችለው አካልህ ይህ ችሎታ ስላለው ነው። ይህን ችሎታዋን ያጣች አንዲት ሕመምተኛ መቆም፣ መራመድም ሆነ ቀና ብላ መቀመጥ ተስኗታል።