መዝሙር 143:1-12
የዳዊት ማህሌት።
143 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ።
እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ።
2 ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣+አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው።
3 ጠላት ያሳድደኛልና፤*ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል።
ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል።
4 መንፈሴ* በውስጤ ዛለ፤+ልቤ በውስጤ ደነዘዘ።+
5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።*
6 እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማሁ።*+ (ሴላ)
7 ይሖዋ ሆይ፣ ፈጥነህ መልስልኝ።+ጉልበቴ* ተሟጠጠ።+
ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤+አለዚያ ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+
8 በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ።
ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣*ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+
9 ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ።
የአንተን ጥበቃ እሻለሁ።+
10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+
መንፈስህ ጥሩ ነው፤በደልዳላ መሬት* ይምራኝ።
11 ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ።
በጽድቅህ ከጭንቅ ታደገኝ።*+
12 በታማኝ ፍቅርህ ጠላቶቼን አስወግዳቸው፤*+አገልጋይህ ነኝና፣+የሚያጎሳቁሉኝን* ሰዎች ሁሉ አጥፋቸው።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ነፍሴን ያሳድዳታልና።”
^ ወይም “ጉልበቴ።”
^ ወይም “አጠናለሁ።”
^ ወይም “ነፍሴ እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማች።”
^ ወይም “መቃብር።”
^ ቃል በቃል “መንፈሴ።”
^ ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁና።”
^ ወይም “በቅንነት ምድር።”
^ ወይም “ነፍሴን ከጭንቅ ታደጋት።”
^ ቃል በቃል “ጸጥ አሰኛቸው።”
^ ወይም “ነፍሴን የሚያጎሳቁሏትን።”