መዝሙር 15:1-5

  • በይሖዋ ድንኳን የሚስተናገድ ማን ነው?

    • በልቡ እውነትን ይናገራል (2)

    • ስም አያጠፋም (3)

    • “ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን አያጥፍም” (4)

የዳዊት ማህሌት። 15  ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው? በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው?+  2  ያለነቀፋ* የሚመላለስ፣+ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣+በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው።+  3  በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤+በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤+የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም።*+  4  ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል። ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን* አያጥፍም።+  5  ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በንጹሕ አቋም።”
ወይም “ወዳጆቹን አያሳፍርም።”
ቃል በቃል “መሐላውን።”
ወይም “ፈጽሞ አይንገዳገድም (አይውተረተርም)።”