መዝሙር 41:1-13

  • የታመመ ሰው ጸሎት

    • አምላክ የታመመውን ይደግፈዋል (3)

    • የቅርብ ወዳጁ ከዳው (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 41  ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል።  2  ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል። በምድር ላይ ደስተኛ ይባላል፤+ለጠላቶቹ ምኞት* አሳልፈህ አትሰጠውም።+  3  ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ።  4  እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ።  5  ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ።  6  ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል። እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል።  7  የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤  8  “ክፉ ነገር ደርሶበታል፤ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ።+  9  ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትና+ከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ።*+ 10  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ። 11  ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣ አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ።+ 12  እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን* በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤+በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።+ 13  የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።+ አሜን፣ አሜን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ፍላጎት፤ ነፍስ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴን ፈውሳት።”
ወይም “እኔን ለማጥቃት ተነሳ።”
መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።