ኢሳይያስ 40:1-31

  • ለአምላክ ሕዝብ የተሰጠ ማጽናኛ (1-11)

    • በምድረ በዳ የተሰማ ድምፅ (3-5)

  • የአምላክ ታላቅነት (12-31)

    • “ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው” (15)

    • ‘አምላክ ክብ ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል’ (22)

    • ከዋክብትን ሁሉ በየስማቸው ይጠራቸዋል (26)

    • አምላክ ፈጽሞ አይደክምም (28)

    • ይሖዋን ተስፋ ማድረግ ኃይል ያድሳል (29-31)

40  “አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ” ይላል አምላካችሁ።+  2  “ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤*የግዳጅ አገልግሎቷ እንዳበቃናየበደሏ ዋጋ እንደተከፈለ ንገሯት።+ ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ከይሖዋ እጅ ሙሉ* ዋጋ ተቀብላለች።”+  3  አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦ “የይሖዋን መንገድ ጥረጉ!*+ በበረሃ ለአምላካችን አውራ ጎዳናውን+ አቅኑ።+  4  ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል። ወጣ ገባውም መሬት ይስተካከል፤ጎርበጥባጣውም ምድር ሸለቋማ ሜዳ ይሁን።+  5  የይሖዋ ክብር ይገለጣል፤+ሥጋም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤*+የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።”  6  አዳምጥ! አንድ ሰው “ጮክ ብለህ ተናገር!” አለ። ሌላውም “ምን ብዬ ልናገር?” አለ። “ሥጋ ሁሉ* ለምለም ሣር ነው። ታማኝ ፍቅሩ ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።+  7  ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤+ምክንያቱም የይሖዋ እስትንፋስ* ይነፍስበታል።+ ሕዝቡ በእርግጥ ለምለም ሣር ነው።  8  ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”+  9  አንቺ ለጽዮን ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣+ከፍ ወዳለ ተራራ ውጪ። አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ። ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ። ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ።+ 10  እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በኃይል ይመጣል፤ክንዱም ስለ እሱ ይገዛል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ።+ 11  መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል።+ ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤በእቅፉም ይሸከማቸዋል። ግልገሎቻቸውን የሚያጠቡትን በቀስታ ይመራል።+ 12  ውኃዎችን በእፍኙ የሰፈረ፣+ሰማያትን በስንዝሩ* የለካ፣ የምድርን አፈር ሰብስቦ በመስፈሪያ የያዘ+ወይም ተራሮችን በመለኪያ፣ኮረብቶችንም በሚዛን የመዘነ ማን ነው? 13  የይሖዋን መንፈስ የለካ*እንዲሁም አማካሪው ሆኖ ሊያስተምረው የሚችል ማን ነው?+ 14  ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?የፍትሕን መንገድ ያስተማረውአሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+ 15  እነሆ፣ ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤በሚዛንም ላይ እንዳለ አቧራ ይቆጠራሉ።+ እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ደቃቅ አፈር ያነሳቸዋል። 16  እሳት መንደዱን እንዲቀጥል ለማድረግ የሊባኖስ ዛፎች እንኳ አይበቁም፤*በውስጡም ያሉት የዱር እንስሳት የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በቂ አይደሉም። 17  ብሔራት ሁሉ በፊቱ የሌሉ ያህል ናቸው፤+በእሱም ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩና ዋጋ ቢስ ናቸው።+ 18  አምላክን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ?+ ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?+ 19  የእጅ ጥበብ ባለሙያ ብረት አቅልጦ ጣዖት* ይሠራል፤አንጥረኛውም በወርቅ ይለብጠዋል፤+የብር ሰንሰለትም ይሠራለታል። 20  አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠትየማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል።+ የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለትበእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል።+ 21  ይህን አታውቁም? ደግሞስ አልሰማችሁም? ከመጀመሪያ አንስቶስ አልተነገራችሁም? የምድር መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ማስረጃስ አላስተዋላችሁም?+ 22  እሱ ክብ* ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል፤+በእሷም ላይ የሚኖሩት እንደ ፌንጣ ናቸው። እሱ ሰማያትን እንደ ስስ ጨርቅ ይዘረጋል፤እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይወጥራቸዋል።+ 23  ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስወግዳል፤የምድር ፈራጆችንም* እንዳልነበሩ ያደርጋል። 24  ገና እንደተተከለ፣ገና እንደተዘራ፣ግንዱም በአፈር ውስጥ ሥር እንዳልሰደደ ተክል ናቸው፤ሲነፍስባቸውም ይደርቃሉ፤ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+ 25  “እኩያው እሆን ዘንድ ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱሱ። 26  “ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ። እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው?+ እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+ ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና ከሚያስደምመው ኃይሉ+ የተነሳአንዳቸውም አይጎድሉም። 27  ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣‘መንገዴ ከይሖዋ ተሰውሯል፤ከአምላክ ፍትሕ አላገኝም’ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?+ 28  ይህን አታውቅም? ደግሞስ አልሰማህም? የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው።+ እሱ ፈጽሞ አይደክምም ወይም አይዝልም።+ ማስተዋሉ አይመረመርም።*+ 29  ለደከመው ኃይል፣ጉልበት ለሌላቸውም የተሟላ ብርታት* ይሰጣል።+ 30  ወንዶች ልጆች ይደክማሉ፤ ደግሞም ይዝላሉ፤ወጣቶችም ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤ 31  ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ኃይላቸው ይታደሳል። እንደ ንስር በክንፍ ወደ ላይ ይወጣሉ።+ ይሮጣሉ፣ አይዝሉም፤ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ኢየሩሳሌምን በሚያጽናና ቃል አናግሯት።”
ወይም “እጥፍ።”
ወይም “አዘጋጁ።”
ወይም “ሰዎችም ሁሉ በአንድነት ያዩታል።”
ወይም “ሰው ሁሉ።”
ወይም “መንፈስ።”
ጣቶች ሲዘረጉ ከአውራ ጣት ጫፍ እስከ ትንሿ ጣት ጫፍ ድረስ ያለውን ርዝመት ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
“የተረዳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ሊባኖስ እንኳ በቂ ማገዶ ማቅረብ አትችልም።”
ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”
ወይም “ድቡልቡል።”
ወይም “ገዢዎችንም።”
ወይም “ሊደረስበት አይችልም።”
ወይም “ብርቱ ጉልበት።”