ኤርምያስ 45:1-5
-
ይሖዋ ለባሮክ ያስተላለፈው መልእክት (1-5)
45 የኢዮስያስ ልጅ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣+ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ይህን ቃል ከኤርምያስ አፍ እየሰማ በመጽሐፍ በጻፈበት ጊዜ፣+ ነቢዩ ኤርምያስ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
2 “ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦
3 ‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’
4 “እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ።+
5 አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ።* እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’*
“‘በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን* እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’”*+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ታላላቅ ነገሮች አገኛለሁ ብለህ ትጠብቃለህ።”
^ ወይም “መፈለግህን ተው።”
^ ወይም “በሰዎች።”
^ ወይም “ነፍስህን።”
^ ወይም “ሕይወትህ እንዲተርፍ አደርጋለሁ።”