በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 17

መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተሰብህ ሕይወት ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

 ባሎች/አባቶች

“በተመሳሳይም ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ አካላቸው አድርገው ሊወዷቸው ይገባል። ሚስቱን የሚወድ ሰው ራሱን ይወዳል፤ የገዛ አካሉን የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል፤ . . . ከእናንተ እያንዳንዱ ራሱን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱንም ይውደድ።”

ኤፌሶን 5:28, 29, 33

 “አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው፤ ከዚህ ይልቅ በይሖዋ ተግሣጽና ምክር አሳድጓቸው።”

ኤፌሶን 6:4

 ሚስቶች

“ሚስት ባሏን በጥልቅ ታክብር።”

ኤፌሶን 5:33

 “ሚስቶች ሆይ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ሊያደርጉት የሚገባ ስለሆነ ለባሎቻችሁ ተገዙ።”

ቆላስይስ 3:18

 ልጆች

“ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና። ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለው ትእዛዝ የሚከተለውን የተስፋ ቃል የያዘ የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው፦ ‘ይህም መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህ በምድር ላይ እንዲረዝም ነው።’”

ኤፌሶን 6:1-3

 “ልጆች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ እንዲህ ማድረጋችሁ ጌታን ያስደስተዋልና።”

ቆላስይስ 3:20