ሀ7-ሀ
የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት አበይት ክንውኖች—ኢየሱስ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት የተከናወኑ ነገሮች
አራቱ ወንጌሎች በጊዜ ቅደም ተከተል
እነዚህ ሰንጠረዦች ኢየሱስ የተጓዘባቸውንና የሰበከባቸውን አካባቢዎች የሚያሳዩ ካርታዎች አሏቸው። በካርታው ላይ ያሉት ቀስቶች ኢየሱስ የተጓዘበትን ትክክለኛ መንገድ የሚያመለክቱ ሳይሆኑ የተጓዘበትን አቅጣጫ የሚጠቁሙ ናቸው። “ገ.” የሚለው ምልክት “ገደማ” ማለት ነው።
ኢየሱስ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት የተከናወኑ ነገሮች
ጊዜ |
ቦታ |
ክንውን |
ማቴዎስ |
ማርቆስ |
ሉቃስ |
ዮሐንስ |
---|---|---|---|---|---|---|
3 ዓ.ዓ. |
ኢየሩሳሌም፣ ቤተ መቅደስ |
መልአኩ ገብርኤል መጥምቁ ዮሐንስ እንደሚወለድ ለዘካርያስ አስቀድሞ ነገረው |
||||
2 ዓ.ዓ. ገ. |
ናዝሬት፤ ይሁዳ |
መልአኩ ገብርኤል ኢየሱስ እንደሚወለድ ለማርያም አስቀድሞ ነገራት፤ እሷም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ልትጠይቅ ሄደች |
||||
2 ዓ.ዓ. |
የይሁዳ ኮረብታማ ምድር |
መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ፤ ስምም ወጣለት፤ ዘካርያስ ትንቢት ተናገረ፤ ዮሐንስ በበረሃ ይኖራል |
||||
2 ዓ.ዓ.፣ ጥቅምት 1 ገ. |
ቤተልሔም |
ኢየሱስ ተወለደ፤ “ቃልም ሥጋ ሆነ” |
||||
ቤተልሔም አቅራቢያ፤ ቤተልሔም |
አንድ መልአክ ለእረኞች ምሥራች አበሰረ፤ መላእክት አምላክን አወደሱ፤ እረኞቹ ሕፃኑን ሊያዩት ሄዱ |
|||||
ቤተልሔም፤ ኢየሩሳሌም |
ኢየሱስ ተገረዘ (በ8ኛው ቀን)፤ ወላጆቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ይዘውት ሄዱ (ከ40ኛው ቀን በኋላ) |
|||||
1 ዓ.ዓ. ወይም 1 ዓ.ም. |
ኢየሩሳሌም፤ ቤተልሔም፤ ግብፅ፤ ናዝሬት |
ኮከብ ቆጣሪዎቹ ሊያዩት መጡ፤ ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሸሸ፤ ሄሮድስ ሕፃናት ወንዶችን አስገደለ፤ ቤተሰቡ ከግብፅ ተመልሶ በናዝሬት መኖር ጀመረ |
||||
12 ዓ.ም.፣ የፋሲካ በዓል |
ኢየሩሳሌም |
የአሥራ ሁለት ዓመቱ ኢየሱስ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ መምህራኑን ጥያቄዎች ጠየቃቸው |
||||
ናዝሬት |
ወደ ናዝሬት ተመለሰ፤ ወላጆቹንም ይታዘዛቸው ነበር፤ የአናጺነት ሙያ ተማረ፤ ማርያም ሌሎች አራት ወንዶች ልጆች እንዲሁም ሴቶች ልጆች አሳድጋለች (ማቴ 13:55, 56፤ ማር 6:3) |
|||||
29፣ ሚያዝያ ገደማ |
ምድረ በዳ፣ ዮርዳኖስ ወንዝ |
መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን ጀመረ |