በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንድ ድርጅት አስተዳዳሪ በጸሐፊው ተጠቅሞ ደብዳቤ እንደሚያስጽፍ ሁሉ አምላክም ታማኝ ሰዎችን በመጠቀም ቅዱሳን መጻሕፍትን አስጽፏል

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያዘጋጃቸውን አስደሳች በረከቶች ያሳወቀን እንዴት ነው?

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያዘጋጃቸውን አስደሳች በረከቶች ያሳወቀን እንዴት ነው?

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ፈጣሪያችን፣ በመላእክትና በነቢያት አማካኝነት መልእክቱን ለሰው ልጆች ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ከዚህም በተጨማሪ ፈጣሪ፣ መልእክቱ እና ቃል የገባቸው በረከቶች በጽሑፍ እንዲሰፍሩ አድርጓል። አምላክ ወደፊት አስደሳች በረከቶችን እንደሚያመጣ ቃል ገብቷል። ታዲያ አምላክ ቃል ስለገባቸው ነገሮች በዛሬው ጊዜ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

አምላክ ያስተላለፈልን መልእክት የሚገኘው በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) አምላክ በነቢያት ተጠቅሞ መልእክቱን ያስጻፈው እንዴት ነው? (2 ጴጥሮስ 1:21) ሐሳቡን በጸሐፊዎቹ አእምሮ ውስጥ ያስቀመጠው ሲሆን እነሱም የአምላክን ሐሳብ በጽሑፍ አስፍረውታል። አንድ ምሳሌ እንውሰድ። የአንድ ድርጅት አስተዳዳሪ፣ ጸሐፊው መልእክት እንዲጽፍለት ቢያደርግ የደብዳቤው ባለቤት የድርጅቱ አስተዳዳሪ መሆኑን አንጠራጠርም። በተመሳሳይም አምላክ መልእክቱን ለማስጻፍ በሰዎች ቢጠቀምም በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘው ሐሳብ የእሱ እንደሆነ የታወቀ ነው።

የአምላክ ቃል በስፋት ተሰራጭቷል

ፈጣሪያችን ያስጻፈው መልእክት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ሁሉም ሰው መልእክቱን እንዲያነበውና እንዲረዳው ይፈልጋል። በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ የሚኖር “ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ” የአምላክን “የዘላለም ምሥራች” በቀላሉ ማግኘት ይችላል። (ራእይ 14:6) አምላክ፣ ቅዱሳን መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከ3,000 በሚበልጡ ቋንቋዎች እንዲገኙ አድርጓል፤ በመሆኑም ቅዱሳን መጻሕፍት ከየትኛውም መጽሐፍ ይበልጥ በስፋት ተሰራጭተዋል።