መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2017
ይህ እትም ከግንቦት 1-28, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
የሕይወት ታሪክ
ከጥበበኞች ጋር በመሄዴ ተጠቅሜያለሁ
ዊልያም ሳሙኤልሰን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ባሳለፋቸው በርካታ ዓመታት አስደሳች ሆኖም ተፈታታኝ የሆኑ ምድቦች ተሰጥተውት ነበር።
ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ
ክብር ልንሰጥ የሚገባው ለእነማን ነው? ለምንስ? ክብር መስጠት የሚያስገኛቸው አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?
እምነት በማዳበር ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ አድርጉ!
የምናደርጋቸው አንዳንድ ውሳኔዎች በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ታዲያ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ምን ሊረዳን ይችላል?
ይሖዋን በሙሉ ልብ አገልግሉ!
አሳ፣ ኢዮሳፍጥ፣ ሕዝቅያስና ኢዮስያስ የተባሉት የይሁዳ ነገሥታት ስህተት የሠሩ ቢሆንም አምላክ በሙሉ ልባቸው እንዳገለገሉት ተሰምቶታል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
አስቀድሞ ለተጻፉት ነገሮች ትኩረት ትሰጣላችሁ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን ሰዎች ጨምሮ ሌሎች ከሠሩት ስህተት ጠቃሚ ትምህርት ልናገኝ እንችላለን።
ወዳጅነት አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ እውነተኛ ወዳጅ መሆን
ወዳጅህ ችግር ላይ የሚወድቅበትና የአንተ እርዳታ የሚያስፈልገው ጊዜ ሊኖር ይችላል። እሱን ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?
በጥንታዊ ማሰሮ ላይ ተጽፎ የተገኘ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም
በ2012 የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች 3,000 ዓመታትን ያስቆጠረ የአንድ ማሰሮ ስብርባሪ በማግኘታቸው ተመራማሪዎች በጣም ተደስተዋል። ይህን ግኝት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?