መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሰኔ 2020
ይህ እትም ከነሐሴ 3-30, 2020 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶች ይዟል።
“ስምህ ይቀደስ”
የጥናት ርዕስ 23፦ ከነሐሴ 3-9, 2020። የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጥረታትን ሁሉ የሚመለከት ምን ወሳኝ ጉዳይ ተነስቷል? ይህ ጉዳይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው? በዚህ ጉዳይ ውስጥ የእኛ ሚና ምንድን ነው? የእነዚህንና ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ማወቃችን ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና ለማጠናከር ይረዳናል።
“ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ”
የጥናት ርዕስ 24፦ ከነሐሴ 10-16, 2020። በዚህ ርዕስ ላይ፣ በመዝሙር 86:11, 12 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የንጉሥ ዳዊት ጸሎት እንመረምራለን። የይሖዋን ስም መፍራት ሲባል ምን ማለት ነው? ለዚህ ታላቅ ስም አክብሮታዊ ፍርሃት እንዲኖረን የሚያነሳሳን ምንድን ነው? አምላክን መፍራት መጥፎ ነገር ለማድረግ በምንፈተንበት ጊዜ ጥበቃ የሚሆንልን እንዴት ነው?
የአንባቢያን ጥያቄዎች
“የመንፈስ ፍሬ” ገጽታዎች በገላትያ 5:22, 23 ላይ የተጠቀሱት ባሕርያት ብቻ ናቸው?
“እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ”
የጥናት ርዕስ 25፦ ከነሐሴ 17-23, 2020። ይሖዋን ለበርካታ ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉ አንዳንድ ክርስቲያኖች ከጉባኤው የሚርቁት ለምንድን ነው? አምላክ ስለ እነዚህ አገልጋዮቹ ምን ይሰማዋል? ይህ ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። በተጨማሪም በጥንት ዘመን ይሖዋ ከእሱ የራቁ አንዳንድ አገልጋዮቹን ከረዳበት መንገድ ምን እንደምንማር ያብራራል።
“ወደ እኔ ተመለሱ”
የጥናት ርዕስ፦ ከነሐሴ 24-30, 2020። ይሖዋ ከጉባኤው የራቁ አገልጋዮቹ ወደ እሱ እንዲመለሱ ይፈልጋል። “ወደ እኔ ተመለሱ” በማለት ያቀረበውን ግብዣ መቀበል የሚፈልጉ ሰዎችን ለማበረታታት ማድረግ የምንችለው ብዙ ነገር አለ። በዚህ ርዕስ ላይ፣ እነዚህን ሰዎች መርዳት የምንችልበትን መንገድ እንመለከታለን።