የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው አምላክ ምን ልንሰጠው እንችላለን?
“አምላካችን ሆይ፣ እናመሰግንሃለን፤ ውብ የሆነውን ስምህንም እናወድሳለን።”—1 ዜና 29:13
1, 2. ይሖዋ ያለውን ሀብት በልግስና የተጠቀመበት እንዴት ነው?
ይሖዋ ለጋስ አምላክ ነው። ያለንን ማንኛውም ነገር ያገኘነው ከእሱ ነው። ወርቅንና ብርን ጨምሮ በምድር ላይ ያለው ማንኛውም የተፈጥሮ ሀብት የእሱ ነው፤ እነዚህን የተፈጥሮ ሀብቶች ደግሞ በምድር ላይ ያለ ሕይወት እንዲቀጥል ለማድረግ ይጠቀምበታል። (መዝ. 104:13-15፤ ሐጌ 2:8) ይሖዋ ለሕዝቦቹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላት እነዚህን የተፈጥሮ ሀብቶች ተአምራዊ በሆነ መንገድ እንዴት እንደተጠቀመባቸው የሚያሳዩ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች አሉ።
2 እስራኤላውያን በምድረ በዳ በተጓዙበት ወቅት ይሖዋ ለ40 ዓመታት ያህል መና እና ውኃ በማቅረብ መግቧቸዋል። (ዘፀ. 16:35) በዚህም ምክንያት “ምንም ያጡት ነገር አልነበረም።” (ነህ. 9:20, 21) ይሖዋ በነቢዩ ኤልሳዕ አማካኝነት አንዲት ታማኝ መበለት የነበራት ዘይት በተአምራዊ ሁኔታ እንዲበዛ አድርጓል። ይህ የአምላክ ስጦታ ይህች መበለት የነበረባትን ዕዳ እንድትከፍል አልፎ ተርፎም ለእሷና ለልጆቿ የሚሆን መተዳደሪያ እንድታገኝ አስችሏታል። (2 ነገ. 4:1-7) ኢየሱስም ይሖዋ በሰጠው ኃይል ተጠቅሞ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን መመገብ ችሏል፤ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት ደግሞ ገንዘብ እንዲያገኙ አድርጓል።—ማቴ. 15:35-38፤ 17:27
3. በዚህ ርዕስ ውስጥ ምን እንመረምራለን?
3 ይሖዋ በምድር ላይ የሚገኙ ፍጥረታቱን በሕይወት ለማኖር የሚያስችል ብዙ ነገር አለው። ሆኖም አገልጋዮቹ ድርጅቱ የሚያከናውነውን ሥራ ለመደገፍ፣ ዘፀ. 36:3-7፤ ምሳሌ 3:9ን አንብብ።) ይሖዋ ያሉንን ውድ ነገሮች መልሰን እንድንሰጠው የሚጠብቅብን ለምንድን ነው? በጥንት ዘመን የነበሩ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች የይሖዋ ወኪሎች ለሚያከናውኑት ሥራ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት እንዴት ነው? ድርጅቱ በዛሬው ጊዜ በመዋጮ የተገኘውን ገንዘብ የሚጠቀምበት እንዴት ነው? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ በዚህ ርዕስ ውስጥ ይብራራል።
ያላቸውን ቁሳዊ ነገር እንዲሰጡ ግብዣ አቅርቦላቸዋል። (ለይሖዋ መስጠት ለምን አስፈለገ?
4. የይሖዋን ሥራ መደገፋችን ምን ያሳያል?
4 ለይሖዋ የምንሰጠው ስለምንወደውና ላደረገልን ነገሮች አመስጋኝነታችንን መግለጽ ስለምንፈልግ ነው። ይሖዋ ስላደረገልን በጣም ብዙ ነገሮች ስናስብ ልባችን በአድናቆት ይሞላል። ንጉሥ ዳዊት ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ስለተያዘው እቅድ በተናገረበት ወቅት ሁሉንም ያገኘነው ከይሖዋ እንደሆነና ለይሖዋ የምንሰጠው ማንኛውም ነገር እሱ የሰጠን እንደሆነ ገልጿል።—1 ዜና መዋዕል 29:11-14ን አንብብ።
5. መጽሐፍ ቅዱስ በልግስና መስጠት የአምልኳችን አንዱ ክፍል እንደሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው?
5 በተጨማሪም መስጠት የአምልኳችን አንዱ ክፍል ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ በሰማይ ያሉ የይሖዋ አገልጋዮች እንዲህ ብለው ሲናገሩ በራእይ ተመልክቷል፦ “ይሖዋ አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣ ክብርና ኃይል ልትቀበል ይገባሃል።” (ራእይ 4:11) ይሖዋ ግርማና ክብር የሚገባው አምላክ እንደመሆኑ መጠን ምርጣችንን በመስጠት ልናከብረው ይገባል ቢባል አትስማማም? ይሖዋ በዓመት ሦስት ጊዜ በሚከበሩት በዓላት ወቅት እስራኤላውያን በፊቱ እንዲቀርቡ በሙሴ በኩል አዟቸው ነበር። እስራኤላውያን ይሖዋን ለማምለክ በሚሰበሰቡባቸው በእነዚያ በዓላት ወቅት ‘ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቀርቡም’ ነበር። (ዘዳ. 16:16) ዛሬም በተመሳሳይ የይሖዋን ድርጅት ምድራዊ ክፍል ለመደገፍና አድናቆታችንን ለመግለጽ የራሳችንን ጥቅም መሥዕዋት በማድረግ በልግስና እንሰጣለን፤ ይህም የአምልኳችን አንዱ ክፍል ነው።
6. መስጠት ምን ጥቅም ያስገኝልናል? (በመግቢያው ላይ ያለውን ፎቶግራፍ ተመልከት።)
6 ለጋስ መሆን መልሶ ይክሳል። ሁልጊዜ ተቀባይ ከመሆን ይልቅ በልግስና መስጠት ጠቃሚ ነው። (ምሳሌ 29:21ን አንብብ።) ወላጆቹ ከሚሰጡት ትንሽ የኪስ ገንዘብ ላይ አጠራቅሞ ለእነሱ ስጦታ የሚሰጥን አንድ ልጅ ለማሰብ ሞክር። ወላጆቹ ስጦታውን በአድናቆት እንደሚመለከቱት መገመት አያዳግትም! ወይም ደግሞ በአቅኚነት እያገለገለ ከወላጆቹ ጋር የሚኖር አንድ ልጅ አንዳንድ የቤት ወጪዎችን ለመሸፈን ትንሽም ቢሆን የገንዘብ ድጋፍ ያደርግ ይሆናል። ምንም እንኳ ወላጆቹ ይህን ከእሱ ባይጠብቁም ልጁ እነሱ ለሚያደርጉለት ነገር ያለውን አድናቆት የሚገልጽበት መንገድ እንደሆነ ስለሚያስቡ ስጦታውን ሊቀበሉ ይችላሉ። በተመሳሳይም ይሖዋ ያሉንን ውድ ነገሮች መስጠታችን እኛኑ እንደሚጠቅመን ያውቃል።
ጥንት የነበሩ የአምላክ አገልጋዮች ያሳዩት ልግስና
7, 8. (ሀ) በጥንት ዘመን የነበሩ የይሖዋ ሕዝቦች ለአንድ የተለየ ፕሮጀክት መዋጮ በማድረግ ረገድ ምን ምሳሌ ትተውልናል? (ለ) ለሥራው አመራር ለሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ረገድስ ምሳሌ የተዉልን እንዴት ነው?
7 ከጥንት ዘመን ጀምሮ የይሖዋ ሕዝቦች የእሱን ሥራ ለመደገፍ መዋጮ ያደርጉ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። ለአንድ የተለየ ፕሮጀክት መዋጮ ያደረጉባቸው ጊዜያትም ነበሩ። ለምሳሌ ያህል፣ ሙሴ እስራኤላውያን ለማደሪያ ድንኳኑ ግንባታ መዋጮ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ንጉሥ ዳዊት ሕዝቡ ለቤተ መቅደሱ ግንባታ መዋጮ እንዲያደርግ አበረታቷል። (ዘፀ. 35:5፤ 1 ዜና 29:5-9) በተጨማሪም በንጉሥ ኢዮዓስ ዘመን ካህናቱ የይሖዋን ቤት ለመጠገን የተሰበሰበውን ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ ተጠቅመውበታል። (2 ነገ. 12:4, 5) በመጀመሪያው መቶ ዘመን በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የነበሩ ወንድሞች በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ረሃብ የተነሳ በይሁዳ የሚኖሩ ወንድሞች ችግር ላይ እንደወደቁ ባወቁ ጊዜ “አቅማቸው በፈቀደ መጠን አዋጥተው . . . እርዳታ ለመላክ [ወስነዋል]።”—ሥራ 11:27-30
8 በሌላ በኩል ደግሞ፣ የይሖዋ ሕዝቦች ለሥራው ዘኁ. 18:21) በተመሳሳይም ኢየሱስና ሐዋርያቱ “በንብረታቸው ያገለግሏቸው” የነበሩ ሴቶች ያሳዩአቸውን ልግስና በደስታ ተቀብለዋል።—ሉቃስ 8:1-3
አመራር የሚሰጡትን በገንዘብ ይደግፉ ነበር። በሙሴ ሕግ መሠረት ሌዋውያን እንደ ሌሎቹ ነገዶች ውርሻ አልነበራቸውም። ከዚህ ይልቅ እስራኤላውያን አስራት ወይም አንድ አሥረኛ በማዋጣት ይሰጧቸው ነበር፤ ይህ ደግሞ ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በሚያከናውኑት ሥራ ላይ እንዲያተኩሩ ያስችላቸዋል። (9. በጥንት ዘመን የአምላክ ሕዝቦች መዋጮ ያደርጉ የነበረው ከየት ያገኙትን ነገር ነው?
9 እርግጥ ነው፣ የአምላክ ሕዝቦች እነዚህን መዋጮዎች ያደረጉት በተለያየ መንገድ ካገኟቸው ቁሳዊ ነገሮች ነው። እስራኤላውያን በምድረ በዳ የማደሪያ ድንኳኑን ለመገንባት መዋጮ ባደረጉ ጊዜ ከግብፅ ያመጧቸውን ነገሮችም ሰጥተው ሊሆን ይችላል። (ዘፀ. 3:21, 22፤ 35:22-24) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች እንደ ርስት ወይም ቤት ያሉ ንብረቶችን በመሸጥ ገንዘቡን ለሐዋርያት ይሰጡ ነበር። ከዚያም ሐዋርያቱ በመዋጮ የተገኘውን ገንዘብ ችግር ላይ ለወደቁ ክርስቲያኖች ያከፋፍላሉ። (ሥራ 4:34, 35) ሌሎች ደግሞ የተወሰነ ገንዘብ ለይተው በማስቀመጥና በቋሚነት መዋጮ በማድረግ ሥራውን ይደግፉ ነበር። (1 ቆሮ. 16:2) በዚህ መንገድ ሀብታም ድሃ ሳይል ሁሉም የይሖዋን ሥራ ለመደገፍ የበኩሉን ድርሻ ያበረክት ነበር።—ሉቃስ 21:1-4
በዛሬው ጊዜ የአምላክ አገልጋዮች የሚያሳዩት ልግስና
10, 11. (ሀ) በጥንት ዘመን የነበሩ ለጋስ የይሖዋ አገልጋዮች የተዉትን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (ለ) የመንግሥቱን ሥራ በመደገፍ ረገድ ስላገኘኸው መብት ምን ይሰማሃል?
10 በዛሬው ጊዜም ለአንድ የተወሰነ ዓላማ መዋጮ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ ለጉባኤያችሁ አዲስ የስብሰባ አዳራሽ ለመገንባት ዕቅድ ተይዞ ይሆን? ወይም ደግሞ አሁን የምትሰበሰቡበት አዳራሽ እድሳት እየተደረገለት ነው? ምናልባትም በአካባቢያችን የሚገኘውን ቅርንጫፍ ቢሮ ለማደስ፣ የክልል ስብሰባ ወጪዎችን ለመሸፈን ወይም የተፈጥሮ አደጋ ያጋጠማቸውን ወንድሞች ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ሰምተን ይሆናል። በተጨማሪም በዋናው መሥሪያ ቤትና በተለያዩ የምድር ክፍሎች በሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ የሚከናወነውን ሥራ የሚሠሩትን ወንድሞችና እህቶች ለመደገፍ መዋጮ እናደርጋለን። የምናደርገው መዋጮ ሚስዮናውያንን፣ ልዩ አቅኚዎችንና በወረዳ ሥራ የሚካፈሉትን ለመደገፍም ይውላል። ከዚህም ሌላ ጉባኤያችሁ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያሉ ወንድሞች የሚጠቀሙባቸውን የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾችና የስብሰባ አዳራሾች ለመገንባት ተብሎ የተያዘውን ዓለም አቀፍ ፕሮግራም ለመደገፍ ድምፀ ውሳኔ እንዳደረገና በዚህም መሠረት በቋሚነት መዋጮ እየላከ እንዳለ ጥርጥር የለውም።
11 በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ይሖዋ እያከናወነ ያለውን ሥራ ለመደገፍ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ማበርከት እንችላለን። አብዛኛውን ጊዜ መዋጮ ያደረገው ማን እንደሆነ አይታወቅም። የምናደርገውን መዋጮ በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ በሚገኙት ሣጥኖች ውስጥ መጨመር ወይም በjw.org አማካኝነት በኢንተርኔት መላክ እንችላለን፤ ምን ያህል መዋጮ እንዳደረግን ሌሎች አያውቁም። የምናደርገው አነስተኛ መዋጮ ያን ያህል የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ ይሰማን ይሆናል። ይሁንና ድርጅቱ አብዛኛውን ሥራ የሚያካሂደው ጥቂቶች በሚያደርጉት ከፍተኛ መጠን ያለው መዋጮ ሳይሆን ብዙዎች በሚያደርጉት አነስተኛ መጠን ያለው መዋጮ ነው። “በጣም ድሆች” ቢሆኑም እንኳ በእርዳታ አገልግሎቱ ለመካፈል መብት እንዲሰጣቸው እንደለመኑት የመቄዶንያ ክርስቲያኖች ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወንድሞቻችንም ተመሳሳይ የልግስና መንፈስ እያሳዩ ነው።—2 ቆሮ. 8:1-4
12. ድርጅቱ የሚዋጣው ገንዘብ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ጥረት የሚያደርገው እንዴት ነው?
12 የበላይ አካሉ የሚደረገውን መዋጮ የሚጠቀምበት መንገድ ታማኝና ልባም መሆኑን ያሳያል። (ማቴ. 24:45) የበላይ አካሉ አባላት በዚህ ረገድ ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ እንዲረዳቸው ወደ ይሖዋ ይጸልያሉ፤ ከዚያም በጥንቃቄ በጀት ያወጣሉ። (ሉቃስ 14:28) በጥንት ዘመን መዋጮዎችን እንዲይዙ ኃላፊነት የተሰጣቸው መጋቢዎች መዋጮዎቹ ለታሰበላቸው ዓላማ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎችን ይወስዱ ነበር። ለምሳሌ ዕዝራ በአሁኑ የዋጋ ተመን ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ሊያወጣ የሚችል ወርቅ፣ ብርና ሌሎች ውድ ነገሮች ከፋርስ ንጉሥ በስጦታ ተቀብሎ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ ሄዶ ነበር። ዕዝራ የተቀበላቸውን እነዚህን ስጦታዎች ለይሖዋ በፈቃደኝነት የሚቀርቡ መባዎች እንደሆኑ አድርጎ ተመልክቷቸዋል፤ በመሆኑም በዚያ አደገኛ ክልል ሲጓዝ እነዚህን ውድ ነገሮች ከዘራፊዎች ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጓል። (ዕዝራ 8:24-34) ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ በይሁዳ የሚገኙ ወንድሞችን ለመርዳት መዋጮ አሰባስቦ ነበር። መዋጮውን የሚያደርሱት ሰዎች ‘በይሖዋ ፊት ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ፊት ሁሉንም ነገር በሐቀኝነት እንዲያከናውኑ’ ለማድረግ ተገቢ እርምጃዎችን ወስዷል። (2 ቆሮንቶስ 8:18-21ን አንብብ።) ድርጅቱም የዕዝራንና የጳውሎስን ምሳሌ በመከተል በአሁኑ ጊዜ የሚዋጣው ገንዘብ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ጥብቅ የሆነ የአሠራር ሂደት ይከተላል።
13. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድርጅቱ አንዳንድ ማስተካከያዎችን ያደረገው ለምንድን ነው?
13 አንድ ቤተሰብ ገቢና ወጪውን ለማመጣጠን ወይም ኑሮውን በማቅለልና ወጪውን በመቀነስ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋት በሚያስብበት ጊዜ አንዳንድ ማስተካከያዎች ሊያደርግ ይችላል። በይሖዋ ድርጅት ውስጥም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አስደሳች የሆኑ በርካታ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ታቅደው ነበር። በዚህም ምክንያት የሚወጣው ወጪ በመዋጮ ከሚገኘው ገንዘብ ጋር ሊመጣጠን ያልቻለባቸው ጊዜያት ነበሩ። ስለዚህ ድርጅቱ በእናንተ ልግስና የተገኘውን መዋጮ በተቻለ መጠን አብቃቅቶ ለመጠቀም ሲል ወጪ መቀነስና ሥራውን ማቅለል የሚቻልባቸውን እርምጃዎች ወስዷል።
የምታደርጉት መዋጮ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
14-16. (ሀ) በምታደርጉት መዋጮ አማካኝነት ምን ነገሮች እየተከናወኑ ነው? (ለ) አንተስ ከእነዚህ ዝግጅቶች ምን ጥቅም አግኝተሃል?
14 ይሖዋን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩ ወንድሞችና እህቶች ‘የአሁኑን ያህል መንፈሳዊ ዝግጅቶች የተትረፈረፉበት ጊዜ ኖሮ አያውቅም’ ብለው ሲናገሩ እንሰማለን። እስቲ ከእነዚህ ዝግጅቶች መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ እንሞክር። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በjw.org እና በJW ብሮድካስቲንግ አማካኝነት ከሚቀርቡት መንፈሳዊ ምግቦች እየተጠቀምን ነው። አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በብዙ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። በ2014/2015 “ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥት መፈለጋችሁን ቀጥሉ!” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የሦስት ቀናት ብሔራት አቀፍ ስብሰባ፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ 14 ከተሞች በሚገኙ ትላልቅ ስታዲየሞች
ውስጥ ተካሂዷል። በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙ ሁሉ በጣም ተደስተዋል።15 ብዙዎች በይሖዋ ድርጅት በኩል ለሚቀርቡላቸው ዝግጅቶች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ለምሳሌ ያህል በእስያ ውስጥ በሚገኝ አንድ አገር የሚያገለግሉ ባልና ሚስት በJW ብሮድካስቲንግ አማካኝነት ስለሚቀርበው ዝግጅት እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦ “የምናገለግለው በአንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ ነው። በመሆኑም አንዳንድ ጊዜ ብቻችንን እንደሆንን ይሰማናል፤ ይሖዋ እያከናወነ ያለው ሥራ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ እንዘነጋለን። ሆኖም በJW ብሮድካስቲንግ ላይ የሚቀርቡትን የተለያዩ ፕሮግራሞች ስንመለከት የዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አባል መሆናችን ወዲያው ትዝ ይለናል። እኛ ባለንበት ከተማ ያሉ ወንድሞችና እህቶች JW ብሮድካስቲንግን በጣም ይወዱታል። ብዙውን ጊዜ ወርሃዊውን ፕሮግራም ከተመለከቱ በኋላ ከበላይ አካሉ አባላት ጋር ይበልጥ እንደተቀራረቡ እንደሚሰማቸው ይናገራሉ። የአምላክ ድርጅት አባላት በመሆናቸው ከምንጊዜውም ይበልጥ ኩራት ተሰምቷቸዋል።”
16 በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ 2,500 ገደማ የሚሆኑ የስብሰባ አዳራሾች እየተገነቡ አሊያም ከፍተኛ እድሳት እየተደረገላቸው ይገኛል። በሆንዱራስ የሚገኝ አንድ ጉባኤ አባላት አዲስ የስብሰባ አዳራሽ ከተሠራላቸው በኋላ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “የይሖዋ ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብና የዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበር አባላት በመሆናችን በጣም ደስተኞች ነን፤ በአካባቢያችን አዲስ የስብሰባ አዳራሽ ሲገነባ ለማየት የነበረን ሕልም እውን ሊሆን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።” ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጽሑፎች በራሳቸው ቋንቋ ተተርጉመው ሲያዩ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ወንድሞችና እህቶች እርዳታ ሲያደርጉላቸው አሊያም ጋሪዎችን በመጠቀም የሚሰጠው የአደባባይ ምሥክርነት በአካባቢያቸው ያስገኘውን ውጤት ሲመለከቱ በተመሳሳይ መንገድ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
17. በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ድርጅቱን እየደገፈ ነው እንድንል የሚያደርገን ምንድን ነው?
17 ሌሎች ሰዎች በፈቃደኝነት በሚደረግ መዋጮ ብቻ ይህን ሁሉ ሥራ ማከናወን መቻላችን በጣም ያስገርማቸዋል። የአንድ ትልቅ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከማተሚያዎቻችን መካከል አንዱን ከጎበኙ በኋላ ሥራው ሁሉ የሚከናወነው ሌላ ምንም የገቢ ማሰባሰቢያ ምንጭ ሳይኖር በፈቃደኛ ሠራተኞችና በፈቃደኝነት በሚደረግ የገንዘብ መዋጮ መሆኑን ሲረዱ በጣም ተደንቀዋል። ይህ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነገር እንደሆነ ተናግረዋል። ደግሞም እውነታቸውን ነው! የይሖዋ ድጋፍ ባይኖር ይህን ማከናወን አይቻልም ነበር።—ኢዮብ 42:2
መልሰን ለይሖዋ መስጠታችን የሚያስገኘው በረከት
18. (ሀ) የመንግሥቱን ሥራ ለመደገፍ በልግስና የምንሰጥ ከሆነ ምን በረከቶች እናገኛለን? (ለ) ልጆቻችንም ሆኑ አዲሶች ለጋስ እንዲሆኑ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
18 ይሖዋ በዛሬው ጊዜ እየተካሄደ ያለውን ታላቅ ሥራ የመደገፍ መብት በመስጠት አክብሮናል። መንግሥቱን ለመደገፍ በልግስና የምንሰጥ ከሆነ እሱ ደግሞ በረከቱን እንደሚያፈስልን ማረጋገጫ ሰጥቶናል። (ሚል. 3:10) ይሖዋ በልግስና የሚሰጥ ሰው እንደሚበለጽግ ተናግሯል። (ምሳሌ 11:24, 25ን አንብብ።) በተጨማሪም በልግስና መስጠታችን ደስተኞች እንድንሆን ያደርገናል፤ ምክንያቱም “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።” (ሥራ 20:35) ልጆቻችንም ሆኑ አዲሶች ለጋስ እንዲሆኑ በማበረታታት እንዲሁም እኛ ራሳችን በዚህ ረገድ ምሳሌ በመሆን ልግስና የሚያስገኘውን በረከት እንዲያጣጥሙ ልንረዳቸው እንችላለን።
19. ይህ ርዕስ ምን እንድታደርግ አበረታቶሃል?
19 ሁሉንም ነገር ያገኘነው ከይሖዋ ነው። መልሰን ለእሱ መስጠታችን እንደምንወደውና ላደረገልን ነገር ሁሉ አድናቆት እንዳለን ያሳያል። (1 ዜና 29:17) እስራኤላውያን ለቤተ መቅደሱ ግንባታ “በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ [ተደስተው ነበር]፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና።” (1 ዜና 29:9) እኛም በተመሳሳይ ከይሖዋ እጅ ያገኘነውን መልሰን ለእሱ በመስጠት ምንጊዜም ደስታና እርካታ ማግኘት እንችላለን።