ንቁ! ቁጥር 2 2017 | ምትሃታዊ ድርጊቶች ምን ጉዳት አላቸው?
በዛሬው ጊዜ እንደ አስማተኞች፣ ጠንቋዮችና ቫምፓየሮች ያሉ ምትሃታዊ ኃይል ያላቸውን ገጸ ባሕርያት የሚያሳዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እየተለመዱ መጥተዋል።
እንዲህ ያለው መዝናኛ ጉዳት ያለው ይመስልሃል?
ይህ “ንቁ!” መጽሔት እንዲህ ያሉ መዝናኛዎች የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ያሉት ለምን እንደሆነና እነዚህ መዝናኛዎች ምን ጉዳት እንዳላቸው ያብራራል።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
የብዙዎችን ቀልብ እየሳበ ነው!
አስማተኞች፣ ጠንቋዮች፣ ቫምፓየሮችና የሙታን መናፍስት የመዝናኛ ኢንዱስትሪዎችን እያጥለቀለቁ ካሉ ምትሃታዊ ኃይል ያላቸው ገጸ ባሕርያት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። ለመሆኑ እነዚህ መዝናኛዎች ይህን ያህል ተወዳጅ የሆኑት ለምንድን ነው?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
መጽሐፍ ቅዱስ መናፍስታዊ ድርጊቶችን በተመለከተ ምን ያስተምራል?
ብዙ ሰዎች ምትሃታዊ ወይም መናፍስታዊ ድርጊት የሚባል ነገር እንደሌለ አሊያም የፊልም ደራሲዎች ፈጠራ እንደሆነ ያስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለዚህ ጉዳይ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው ለምንድን ነው?
ንድፍ አውጪ አለው?
ንብ የምትፈልገው ቦታ ላይ ለማረፍ የምትጠቀምበት ዘዴ
ንቦች የሚፈልጉበት ቦታ ላይ ለማረፍ የሚጠቀሙበት ዘዴ በራሪ ሮቦቶችን የሚቆጣጠሩ ፕሮግራሞችን ለመሥራት አመቺ የሆነው ለምንድን ነው?
ልጆች ሐዘን ሲደርስባቸው
መጽሐፍ ቅዱስ የቤተሰብ አባላቸውን በሞት በማጣታቸው ምክንያት ሐዘን የደረሰባቸውን ሦስት ወጣቶች የረዳቸው እንዴት ነው?
አገሮችና ሕዝቦች
ስፔንን እንጎብኝ
ስፔን የተለያየ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያላትና ልዩ ልዩ ሕዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት። ስፔን ከየትኛውም አገር በበለጠ መጠን የምታመርተው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መስቀል
በርካታ ሰዎች መስቀል የክርስትና ምልክት እንደሆነ ይሰማቸዋል። ኢየሱስ የተሰቀለው በመስቀል ላይ ነው? የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መስቀልን ለአምልኮ ተጠቅመዋል?
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?
የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለመረዳት ምን እንደሚያስፈልግህና ምን እንደማያስፈልግህ ተመልከት።
በተጨማሪም . . .
የደረሰብኝን አሳዛኝ ሁኔታ መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ያጋጠማቸው ወጣቶች ችግሩን እንዲቋቋሙ ምን እንደረዳቸው ተናግረዋል።
አጋንንት በእርግጥ አሉ?
አጋንንት እነማን ናቸው? የመጡትስ ከየት ነው?