ንቁ! ቁጥር 3 2017 | መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው? ወይስ የሰዎችን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ?
ይህ ንቁ! መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል እንደሆነ የሚያሳዩ ሦስት ማስረጃዎችን ይዟል።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ “በአምላክ መንፈስ መሪነት” የተጻፈ ነው?
አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ በሆነ መንገድ ከአምላክ ጋር ግንኙነት ያለው መጽሐፍ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ ጥንታዊ ተረቶችን፣ አፈ ታሪኮችንና አንዳንድ ሰዎች የሰጧቸውን ምክሮች የያዘ መጽሐፍ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ መረጃ የያዘ መጽሐፍ
ሳይንቲስቶች ተፈጥሮን በተመለከተ ሳይንሳዊ ትንታኔ ከመስጠታቸው ከረጅም ጊዜ በፊት መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ ትክክለኛ መረጃ ይዟል። ይህ ብቻ ሳይሆን ስለ ዓለም መንግሥታት አነሳስና አወዳደቅ አስቀድሞ የሚናገር ከመሆኑም ሌላ በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።
ለቤተሰብ
ልጆች የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዲሠሩ ማድረግ ያለው ጥቅም
ወላጆች ልጆቻችሁ ቤት ውስጥ እንዲሠሩ ከማድረግ ወደኋላ ትላላችሁ? ከሆነ ልጆቻችሁ የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዲሠሩ ማድረግ ልጆች ኃላፊነት የሚሰማቸውና ደስተኛ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ምን ጥቅም እንዳለው ተመልከቱ።
ሆዳችን ውስጥ “ሁለተኛ አንጎል” አለ?
ይህ ኬሚካላዊ ውህደት የሚካሄድበት ቦታ የሚገኘው በሆዳችን አካባቢ ነው። ለመሆኑ ይህ የነርቭ ሥርዓት ምን ያከናውናል?
ቃለ ምልልስ
አንድ የሶፍትዌር ንድፍ አውጪ ስለሚያምኑበት ነገር ምን ይላሉ?
ዶክተር ፋን ዩ የሒሳብ ተመራማሪነት ሙያቸውን በጀመሩበት ወቅት በዝግመተ ለውጥ ያምኑ ነበር። አሁን ግን ሕይወት ንድፍ አውጪ እንዳለውና ሕይወት ያላቸውን ነገሮች የፈጠረው አምላክ እንደሆነ ያምናሉ። አመለካከታቸውን የቀየሩት ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መላእክት
መላእክት በተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችና ፊልሞች ላይ ይጠቀሳሉ፤ የመላእክትን ምስል የያዙ የሥነ ጥበብ ሥራዎችም አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?
ንድፍ አውጪ አለው?
የባሕር አቆስጣ ፀጉር
በቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ የሚኖሩ አንዳንድ አጥቢ እንስሳት ከቆዳቸው ሥር ብርድ ለመከላከል የሚረዳ ወፍራም ስብ አላቸው። የባሕር አቆስጣ ግን ለየት ያለ የብርድ መከላከያ አለው።
በተጨማሪም . . .
የበለጠ ነፃነት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
ወላጆችህ እንደ ትልቅ ሰው ሊያዩህ እንደሚገባ ይሰማህ ይሆናል፤ እነሱ ግን እንደዛ አይሰማቸውም። የወላጆችህን አመኔታ ለማትረፍ ምን ማድረግ ትችላለህ?
የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ሊባል ይችላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የማን ሐሳብ ነው?