የጥናት ፕሮጀክት
በተቃውሞ ውስጥ ድፍረት ማሳየት
ኤርምያስ 38:1-13ን አንብብ፤ ከዚያም ከነቢዩ ኤርምያስና ከጃንደረባው ኤቤድሜሌክ ስለ ድፍረት ተማር።
አውዱን መርምር። ኤርምያስ የይሖዋን መልእክት ሲያውጅ ድፍረት ያሳየው እንዴት ነው? (ኤር. 27:12-14፤ 28:15-17፤ 37:6-10) ሰዎቹ መልእክቱን ሲሰሙ ምን ምላሽ ሰጡ?—ኤር. 37:15, 16
በጥልቀት ምርምር አድርግ። ኤርምያስ ምን ዓይነት ተቃውሞ አጋጥሞታል? (jr-E 26-27 አን. 20-22) በጥንት ዘመን ስለነበሩ የውኃ ጉድጓዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክር። (it-1-E 471) ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ጭቃ ውስጥ ሲሰምጥ ምን ተሰምቶት የነበረ ይመስልሃል? ኤቤድሜሌክን ምን አስፈርቶት ሊሆን ይችላል?—w12 5/1 31 አን. 2-3
ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ይህ ዘገባ ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን ስለሚጠብቅበት መንገድ ምን ያስተምረኛል? (መዝ. 97:10፤ ኤር. 39:15-18)
-
ድፍረት ማሳየት የሚያስፈልገኝ በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ነው?
-
ተቃውሞ ሲያጋጥመኝ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ድፍረት ማዳበር የምችለው እንዴት ነው? (w11 3/1 30) a
a የጥናት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት በሐምሌ 2023 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።