“አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ መማሪያ መጻሕፍት እንኳ ይህን ያህል ትክክል አይደሉም”
“አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ መማሪያ መጻሕፍት እንኳ ይህን ያህል ትክክል አይደሉም”
ይህ፣ አንድ ሰው ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ አስመልክቶ ከሰጠው ሐሳብ የተወሰደ ነው። በአውስትራሊያ ሲድኒ የምትኖር አንዲት የይሖዋ ምሥክር ይህን መጽሐፍ አበርክታለት ነበር። የዚያን ዕለት ማታ ምሥክሯ የስልክ መልእክት መቀበያ መሣሪያው ላይ የሚከተለውን መልእክት አገኘች:-
“ዛሬ ጠዋት ተገናኝተን ነበር። በዚያን ጊዜ የሰጠሽኝን “ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን?” የተባለውን መጽሐፍ አንብቤ ግማሽ ላይ ደርሻለሁ። የደወልኩልሽ መጽሐፉ ስለ ጽንፈ ዓለም አጀማመር የሚናገረው ነገር እጅግ ወቅታዊና ትክክል መሆኑ በጣም ስላስገረመኝ ነው። አሳይቼሽ የነበረው መጽሐፍ የያዘውን ዓይነት ትምህርት ይዟል . . .
“የሰጠሽኝ መጽሐፍ በጣም ትክክለኛና ወቅታዊ ነው! አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ መማሪያ መጻሕፍት እንኳ ይህን ያህል ትክክል አይደሉም። መሠረታዊ የሆኑትን አራቱን ፊዚካዊ ኃይሎች ማለትም የስበትን ኃይል፣ ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ኃይል፣ ጠንካራ የኑክሊየር ኃይልንና ደካማ የኑክሊየር ኃይልን ይጠቅሳል። እነዚህ በጣም ወቅታዊና የቅርብ ጊዜ ግኝቶች ናቸው። የዛሬ ሳምንት እጠብቅሻለሁ። ደህና ሁኚ።”
ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ለስላሳ ሽፋን ያለውን ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ።
□ ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
J. Hester and P. Scowen (AZ State Univ.), NASA