“እኔ ብቻ እንደሆንኩ አስብ ነበር”
“እኔ ብቻ እንደሆንኩ አስብ ነበር”
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተሰኘውን መጽሐፍ ካነበበች በኋላ ከላይ የተጠቀሰውን አስተያየት የሰጠችው በካሊፎርኒያ ዩ ኤስ ኤ የምትኖር ኡልሪኬ የተባለች የ13 ዓመት ልጅ ነች። እንዲህ ስትል ጽፋለች:-
“‘በነጠላ ወላጅ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች የተሳካ ሕይወት መምራት ይችላሉ!’ በሚለው ምዕራፍ ውስጥ እውነታውን ስላስቀመጣችሁ በጣም አመሰግናለሁ። እማማ ነጠላ ወላጅ ስለሆነች እኔም ለእናቴ ጥሩ ልጅና አሳቢ እንድሆን ረድቶኛል። እንዲሁም ምን እንደሚሰማት በደንብ እንዳስተውል አድርጎኛል። የስሜት ስቃይ ያለብኝ እኔ ብቻ እንደሆንኩ አድርጌ አስብ ነበር።” ወጣቷ ስታጠቃልል “መጽሐፉ በጣም ጠቅሞኛል!” ብላለች።
በምድር ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች 192 ገጾች ባሉት በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት እርዳታ አግኝተዋል። ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ ባሎችን፣ ሚስቶችን፣ ወላጆችን፣ ልጆችን እንዲሁም አያቶችን አዎን፣ ሁሉንም የቤተሰብ አባል ሊጠቅም ይችላል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “በጉልምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችሁን በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እና “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ።”
የግል ቅጂ ማግኘት ይችሉ ዘንድ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ። ችግሮችን ለመፍታት ሊረዱ የሚችሉና ፈጣሪያችን አቅዶት እንደነበረው የቤተሰብ ሕይወት አስደሳች እንዲሆን ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ ሐሳቦችን ያገኛሉ።
□ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።