በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ወጣቶች ብቻ አይደለም

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ወጣቶች ብቻ አይደለም

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ወጣቶች ብቻ አይደለም

ዮላንታ የተባለች የ25 ዓመት ወጣት ፖላንድ ለሚገኘው ለይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በጻፈችው ደብዳቤ ላይ የመንፈስ ጭንቀት አጋጥሟት እንደነበር ገልጻለች። ዮላንታ ካለባት የአካል ጉዳት የተነሳ መራመድ የማትችል ስትሆን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ እናቷንም ሴት አያቷንም በሞት ተነጥቃለች። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ ጀመረች። እንዲህ ስትል ጽፋለች:-

“ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ብቻ እንደሆነ አድርጌ አስብ ነበር። ግን ምንኛ ተሳስቼአለሁ! ከ12 እስከ 16 ያሉትን ምዕራፎች በማንበብ ‘በጣም የምጨነቀውና ብቸኝነት የሚሰማኝ ለምንድን ነው?’ ‘ራሴን የማልወደው ለምንድን ነው?’ እንዲሁም ‘ይህን ያህል ማዘኔ የጤና ነውን?’ ለሚሉት ጥያቄዎቼ አጥጋቢ መልስ አግኝቻለሁ።”

እንዲህ በማለት ትቀጥላለች:- “በተለይ በገጽ 130 ላይ የተሰጡት ሁለት ሐሳቦች ማራኪ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ‘የምትወዱት ሰው ስለሞተባችሁ ማዘናችሁ በተፈጥሮ ያለ ነገር መሆኑን ማወቅ ኃዘኑን እንድትቋቋሙት የሚረዳ ትልቅ ነገር ነው። የደረሰውን ነገር አለመቀበል ግን ኃዘኑን ከማራዘም በስተቀር የሚፈይደው ነገር አይኖርም።’ እነዚህን ቃላት ማንበቤ በሞት ያንቀላፉትን የማየት ተስፋዬን ያጠናከረልኝ ከመሆኑም በላይ ለሕይወቴ ጥልቅ ትርጉም ጨምሮለታል።”

አንተም አሉታዊ ስሜቶችን መቋቋምና ሕይወትህ ጥልቅ ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ የምትፈልግ ከሆነ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ በማንበብ እንደምትጠቀም ይሰማናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት ትችላለህ።

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።