በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ልቤን በጥልቅ ነካው’

‘ልቤን በጥልቅ ነካው’

‘ልቤን በጥልቅ ነካው’

ከአምላክ ጋር የቅርብ ዝምድና መመሥረት የምትችለው እንዴት ነው? ወደ ይሖዋ ቅረቡ (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ በዚህ ረገድ ብዙዎችን ረድቷል። ለምሳሌ ያህል ለ25 ዓመታት የይሖዋ ምሥክር የነበረች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች:- “የተዋጣለት መጽሐፍ ነው። ልቤን በጥልቅ የነካኝ ሲሆን ከዚህ በፊት አድሮብኝ የማያውቅ ቅንዓት ለይሖዋ እንዲያድርብኝ አድርጓል። ወደ ይሖዋ፣ ወደ ባለቤቴና ወደ ጉባኤው ይበልጥ እንድቀርብ አድርጎኛል።”

ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለው መጽሐፍ አንተንም እንዲሁ ሊረዳህ ይችላል። መጽሐፉ በመቅድሙ ላይ እንዲህ ይላል:- “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን የአምላክ ባሕርያትና መንገዶች ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ይሖዋ እያንዳንዱን ባሕርያቱን በገለጸበት መንገድ ላይ ማሰላሰላችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ባሕርያት ፍጹም በሆነ መንገድ ያንጸባረቀው እንዴት እንደሆነ መመልከታችንና እኛም ባሕርያቱን እንዴት ማዳበር እንደምንችል ማወቃችን ከአምላክ ጋር ይበልጥ ያቀራርበናል።”

ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።

ወደ ይሖዋ ቅረቡ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ብትልኩልኝ ደስ ይለኛል።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።