“እነዚህን ሁሉ መቼ ልታነባቸው ነው?”
“እነዚህን ሁሉ መቼ ልታነባቸው ነው?”
በሐምሌ ወር 2001 በሩስያ ምሥራቃዊ ግዛት በምትገኘው የካባሮቭስክ ከተማ የሚኖር አንድ ሰው በከተማው ቤተ መጻሕፍት ውስጥ 34 የንቁ! መጽሔት እትሞች አገኘና በውሰት ወደ ቤቱ ወሰዳቸው። በነሐሴ ወር የሚመለሱበት ቀን ሲደርስ ሊመልሳቸው አልፈለገም። ስለዚህ የመመለሻውን ቀን እስከ መስከረም ወር ድረስ አራዘመው። መጽሔቶቹን በጣም ስለወደዳቸው በኅዳር ወር ከሌሎች ስድስት አዳዲስ እትሞች ጋር በድጋሚ ተዋሳቸው።
ከዚህ በፊት ይህ ሰው ሃይማኖታዊ ጽሑፎችን የማንበብ ፍላጎት አልነበረውም። ታዲያ ንቁ! መጽሔትን እንዴት ማንበብ ጀመረ? “በዚህ መጽሔት ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ሐሳቦች ትኩረት በሚስቡና ሁሉንም ሰው በሚነኩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚያተኩሩ ነው” በማለት ጽፏል።
አክሎም “አብዛኛውን ጊዜ የተለያዩ ባሕሎችን የሚመለከቱ መረጃዎች እንዲሁም ዘመናዊ ከተሞችንና አገሮችን ‘የሚያስጎበኙ’ በጥሩ ሁኔታ የተቀናበሩ ዘገባዎች ይወጣሉ” ብሏል። የተሳካ ሕይወት ለመምራት፣ መንፈሳዊነታቸውን ለመጠበቅ እንዲሁም ሌሎች መከራንና ችግርን ተቋቁመው እንዲያልፉ ለመርዳት ስለቻሉ ሰዎች የሚገልጹትን ርዕሶችም ወዷቸዋል። መጽሔቱን ከገመገመ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ንቁ! መጽሔት ታይም፣ ፖፑላር ሳይንስና ናሽናል ጂኦግራፊክ የተባሉትን መጽሔቶች በአንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘ ጽሑፍ ነው ለማለት ይቻላል” ብሏል።
ሰውየው ከ1995 ጀምሮ በሩስያኛ ቋንቋ የታተሙ የንቁ! እትሞችን የጠየቀ ሲሆን ከንቁ! በተጨማሪም በይሖዋ ምሥክሮች የታተሙ በርካታ መጻሕፍትና ብሮሹሮች እንዲላኩለት ጠይቋል። በደብዳቤው ላይ “‘እነዚህን ሁሉ መቼ ልታነባቸው ነው?’ ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል” ካለ በኋላ ራሱ መልሱን ሲሰጥ ቴሌቪዥን በማየት ወይም ኢንተርኔት በመቃኘት ብዙ ጊዜ ስለማያጠፋ ጠቃሚ የሆነ ነገር ለማንበብ ጊዜ እንደማያጣ ተናግሯል።
ንቁ! መጽሔት ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተትረፈረፈ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን ለጊዜያችን ችግሮች መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን በጥልቀት ይመረምራል። አንተም የይሖዋ ምሥክሮች በየወሩ የሚወጣውን የንቁ! መጽሔት እትም እንዲያመጡልህ መጠየቅ ትችላለህ።
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ልጆች ከወላጆቻቸው ምን ይፈልጋሉ?
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የስሜት መለዋወጥ የሚያስከትለውን ችግር መረዳት
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አምላክን በስም ታውቀዋለህ?
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የኑክሌር ፍንዳታ—በእርግጥ የሚያሰጋ ነው?
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ተስፋ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?
[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
የኑክሌር ፍንዳታ:- U.S. Department of Energy photograph