በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጣዕም የመለየት ችሎታህ

ጣዕም የመለየት ችሎታህ

ንድፍ አውጪ አለው?

ጣዕም የመለየት ችሎታህ

▪ የምትወደውን ምግብ ስትጎርስ ከመቅጽበት ምግቡ ምን ዓይነት ጣዕም እንዳለው ትገነዘባለህ። አስገራሚ የሆነው ይህ ጣዕምን የመለየት ችሎታ የሚሠራው እንዴት ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ:- ምላስህ አልፎ ተርፎም አፍህ ውስጥ ያሉ ሌሎች ክፍሎችና ጉሮሮህ፣ ማጣጣሚያ ጉጦች (taste buds) ተብለው የሚጠሩ ጣዕምን ለመለየት የሚረዱ የቆዳ ሴሎች አሏቸው። ከእነዚህ ሴሎች ውስጥ አብዛኞቹ የሚገኙት ፓፒላ በሚባለው በምላስህ የላይኛው ክፍል ላይ ነው። እያንዳንዱ ማጣጣሚያ ጉጥ ከአራቱ የጣዕም ዓይነቶች (ማለትም ከኮምጣጣ፣ ከጨዋማ፣ ከጣፋጭ ወይም ከመራራ) መካከል አንዱን ብቻ መለየት የሚችሉ እስከ መቶ የሚደርሱ ጣዕም ተቀባይ ሴሎች አሉት። ቅመም የበዛበትን ምግብ ስንመገብ ጣዕሙን የምንለየው በማጣጣሚያ ጉጥ ሳይሆን በሕመም መለያ ሴል እርዳታ ነው። ጣዕም ተቀባይ ሴሎች ሴንሰሪ ከሚባሉ ነርቮች ጋር የተያያዙ ናቸው፤ እነዚህ ነርቮች በምግቡ ውስጥ ካሉት ኬሚካሎች ጋር ሲገናኙ በዚያው ቅጽበት ወደ ታችኛው የአንጎል ክፍል መልእክቶችን ያስተላልፋሉ።

ይሁን እንጂ ጣዕም የመለየቱን ሚና የሚጫወተው አፍ ብቻ አይደለም። በአፍንጫህ ውስጥ የሚገኙት 10,000 የሚያህሉ የሽታ ዓይነቶችን መለየት የሚያስችሉህ አምስት ሚሊዮን የማሽተቻ ሴሎች የአንድን ነገር ጣዕም በመለየት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታሉ። እንዲያውም የአንድን ምግብ ጣዕም በመለየቱ ሂደት 75 በመቶ የሚሆነውን ሚና የሚጫወቱት ለማሽተት የሚረዱት ሕዋሳት እንደሆኑ ይገመታል።

የሳይንስ ሊቃውንት ከኬሚካላዊ ጋዞች መልእክት በመቀበል ማሽተት የሚችል ኤሌክትሮኬሚካል አፍንጫ ሠርተዋል። ይሁን እንጂ ሪሰርች/ፔን ስቴት በተሰኘ አንድ የጥናት ውጤት ላይ የተጠቀሱትና የነርቮችን አሠራር የሚያጠኑት ጆን ካወር የተባሉ ዶክተር እንደገለጹት ከሆነ “ማንኛውም ሰው ሠራሽ የማሽተቻ መሣሪያ እጅግ ድንቅና ውስብስብ ከሆነው አፍንጫ ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የማይባል ተራ ነገር ነው።”

ጣዕም የመለየት ችሎታችን ምግብ በመብላት እንድንደሰት እንደሚያደርገን የሚካድ አይደለም። ይሁንና ሰዎች አንድን ዓይነት የምግብ ጣዕም ከሌላው አስበልጠው እንዲወዱ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ ተመራማሪዎች እስካሁን ሊደርሱበት አልቻሉም። ሳይንስ ዴይሊ የተሰኘው ጽሑፍ እንዲህ ይላል:- “የሳይንስ ሊቃውንት የሰው አካል ስለሚሠራበት መንገድ ዋና ዋና ነገሮችን ያውቁ ይሆናል፤ ጣዕም ስለ መለየትና ስለ ማሽተት ችሎታችን ግን እስካሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ምስጢር ሆነውባቸዋል።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ጣዕም የመለየት ችሎታህ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ ነው?

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ/ሥዕል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ምላስ መሃል ለመሃል ተሰንጥቆ ሲታይ ይህን ይመስላል

[ሥዕላዊ መግለጫ]

ፓፒላ

[ምንጭ]

© Dr. John D. Cunningham/Visuals Unlimited