“አምላክ ስም እንዳለው አላውቅም ነበር”
“አምላክ ስም እንዳለው አላውቅም ነበር”
▪ ይህ፣ አንዲት ሴት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ካነበበች በኋላ የሰጠችው አስተያየት ነው። አክላም እንዲህ ብላለች:- “አምላክ ስም አለው መባሉ በእርግጥም ምክንያታዊ ነው። የአምላክን ስም በመጽሐፍ ቅዱሴ ውስጥ ስፈልገው አገኘሁት!” የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አስመልክታም “ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር እንዲህ ያለ ለመረዳት የማያስቸግርና እጅግ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ አንብቤ አላውቅም” ብላለች።
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ፣ አምላክ ምድርን ገነት የማድረግ ዓላማ እንዳለው ብቻ ሳይሆን ዓላማውን ከግብ የሚደርሰው እንዴት እንደሆነም በግልጽ ያብራራል። መጽሐፉ የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ ምን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይገልጻል። ይህ መጽሐፍ ‘የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው? አምላክ ሥቃይና መከራ እንዲኖር ለምን ፈቀደ? እንዲሁም የአምላክ መንግሥት ሁሉንም ዓይነት መከራዎች የሚያስወግደው እንዴት ነው?’ እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ ይሰጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ከወጣ ገና ሦስት ዓመት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ በ220 ቋንቋዎችና ከ79 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ታትሟል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈለጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።