መምህሯ መጽሐፉን ቢያነቡት እንደሚጠቀሙ ነገረቻቸው
መምህሯ መጽሐፉን ቢያነቡት እንደሚጠቀሙ ነገረቻቸው
▪ ወጣቶች አስተማማኝ የሆነ ምክርና መመሪያ ከየት ማግኘት ይችላሉ? በጣሊያን የምትኖረውና የአሥራ ሦስት ዓመት ወጣት የሆነችው ኬረን ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ጠቃሚ ሆኖ አግኝታዋለች። ከመጽሐፉ ያገኘችውን ጥቅም አብረዋት ለሚማሩት ልጆች ለማካፈል አጋጣሚ አግኝታ ነበር።
ኬረን እንዲህ ብላለች፦ “የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፤ በትምህርት ክፍለ ጊዜ፣ በተለይ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች እንወያይ ነበር። አንድ ቀን መምህሬ፣ በጽሑፎቻችን ላይ ለወጣቶች ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦች እንደሚገኙ መስማቷን ገለጸችልኝ። ከዚያም አንዳንድ ጽሑፎች እንዳመጣላት ጠየቀችኝ። እኔም የወጣቶች ጥያቄ የተባለውን መጽሐፍ ሰጠኋት።
“ከጥቂት ቀናት በኋላ በመጽሐፉ በመጠቀም በክፍል ውስጥ ውይይት እንዲካሄድ አደረገች፤ ውይይቱ ‘መልክ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?’ የሚል ርዕስ ባለው በ10ኛው ምዕራፍ ላይ ያተኮረ ነበር። እንዲያውም በምዕራፉ መጨረሻ ላይ በሚገኘው ‘የመወያያ ጥያቄዎች’ በሚለው ክፍል ላይ የተመሠረተ የቤት ሥራ ሰጠችን። መምህሯ ‘ይህ በጣም ጥሩ መጽሐፍ ነው፤ መጽሐፉ የሌላችሁ መሆኑ ግን ያሳዝናል’ በማለት ተናገረች።
“እኔም መጽሐፉን ማግኘት ለሚፈልጉ ሁሉ ላመጣላቸው እንደምችል ገለጽኩላቸው፤ 16 ተማሪዎች እንዳመጣላቸው ጠየቁኝ። መጽሐፉን ሳመጣ ቀደም ሲል መጽሐፉን ያልፈለጉት ተማሪዎችም እንኳ ሳይቀር ሐሳባቸውን ቀይረው እንደሚፈልጉት ነገሩኝ!”
የወጣቶች ጥያቄ የተባለው መጽሐፍ “በጣም የምጨነቀው ለምንድን ነው?፣” “እውነተኛ ፍቅር መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?፣” “አደንዛዥ ዕፅ መውሰድ እምቢ መባል የሚኖርበት ለምንድን ነው?” እንዲሁም “ቴሌቪዥን የማየት ልማዴን ልቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው?” እንደሚሉት ያሉ ርዕሶችንም ይዟል። አንተም ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ መጽሐፉ እንዲላክልህ መጠየቅ ትችላለህ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።