‘በጣም ያረጀ አንድ መጽሐፍ’ እንዲፈወሱ ረዳቸው
‘በጣም ያረጀ አንድ መጽሐፍ’ እንዲፈወሱ ረዳቸው
▪ በደቡብ አሜሪካ፣ ብራዚል ውስጥ የምትኖር አንዲት የይሖዋ ምሥክር ከቤት ወደ ቤት እየሄደች ሰዎችን በማነጋገር ላይ ሳለች ከአንዲት ሴት ጋር ትገናኛለች። ሴትየዋም የባሏ እናት በአንድ መጽሐፍ መፈወሳቸውን ትነግራታለች። በነገሩ ግራ የተጋባችው የይሖዋ ምሥክር መጽሐፉ የትኛው እንደሆነ ጠየቀቻት። “አንድ በጣም ያረጀ መጽሐፍ ነው” በማለት ሴትየዋ መለሰችላት፤ ከዚያም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን የልጇን የተቦጫጨቀ መጽሐፍ አውጥታ አሳየቻት።
ይህች ሴት፣ አማቷ በመንፈስ ጭንቀት ይሠቃዩ እንደነበረ እንዲሁም ሞትና በጨለማ ውስጥ መሆን ስለሚያስፈራቸው ከአልጋቸው መውረድ እንደማይፈልጉ ነገረቻት። የሴትየዋ ልጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች የተባለውን መጽሐፍ ያገኛል፤ ከዚያም ለአያቱ ያነብላቸው ጀመር። አያትየው የልጅ ልጃቸው በሚያነብላቸው ነገር ከመበረታታታቸው የተነሳ ከነበረባቸው ችግር ነፃ ሆኑ።
የይሖዋ ምሥክሯ እንዲህ ብላለች፦ “እኔም መጽሐፉ የተዘጋጀው በይሖዋ ምሥክሮች እንደሆነና የመጽሐፉን አዲስ ቅጂ ላመጣላት እንደምችል ለሴትየዋ ስነግራት ሁለት ቅጂዎችን ይዤላት እንድመጣ ጠየቀችኝ፤ አንዱን ለአማቷ ለመስጠት ሌላውን ደግሞ ለራሷ ፈልጋው ነበር።መጽሐፉን ይዤላት ስሄድ አሁንም ተጨማሪ መጽሐፍ እንዳመጣላት ጠየቀችኝ። በአጠቃላይ 16 መጽሐፍ ለወዳጆቿ ወስዳለች!”
እርስዎም፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለው መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ይህ መጽሐፍ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጹ ሰዎችና ክንውኖች የሚናገሩ 116 ታሪኮችን ይዟል። መጽሐፉ ከወጣ በኋላ ባሉት 30 ዓመታት ውስጥ ከ72 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ታትሟል። የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ከሞሉ በኋላ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።