ቤተሰብ የሚወያይበት
ቤተሰብ የሚወያይበት
ይህን ሥራ ይሠሩ የነበሩት እነማን ነበሩ?
1. የዘብዴዎስ ልጆችና የኢየሱስ ሐዋርያት የነበሩት ሁለቱ ዓሣ አጥማጆች እነማን ናቸው?
መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።
ፍንጭ፦ ማቴዎስ 4:21, 22ን አንብብ።
․․․․․
2. ዓሣ አጥማጆች የነበሩ ሌሎች ሁለት ሐዋርያት ማን ይባላሉ?
ፍንጭ፦ ማቴዎስ 4:18ን አንብብ።
․․․․․
ለውይይት፦
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ‘ሰዎች አጥማጆች’ እንደሚሆኑ የተናገረው ለምንድን ነው? (ማቴዎስ 4:19) ዓሣ ማጥመድና ሰው ማጥመድ ምን ተመሳሳይነትና ልዩነት ያላቸው ይመስልሃል?
ስለ ሐዋርያው እንድርያስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
3. እንድርያስ የኢየሱስ ተከታይ ከመሆኑ በፊት የማን ደቀ መዝሙር ነበር?
ፍንጭ፦ ማርቆስ 1:4ን እና ዮሐንስ 1:35-40ን አንብብ።
․․․․․
4. እንድርያስ ስለ ኢየሱስ የተነጋገረው ከማን ጋር ነበር? ውጤቱስ ምን ነበር?
ፍንጭ፦ ዮሐንስ 1:40-42ን አንብብ።
․․․․․
ለውይይት፦
ስለ ኢየሱስ የምታውቀውን ነገር ለዘመዶችህ መንገር ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? ሆኖም አንዳንድ ዘመዶችህ ምን ዓይነት ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ?
ፍንጭ፦ ማቴዎስ 10:32-37ን አንብብ።
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ገጽ 3 አስተዋይ ወይም ብልህ ሰው ምን ያስተውላል? ምሳሌ 14:․․․
ገጽ 8 አምላክ ለራሱ ምን ስም አውጥቷል? ዘፀአት 6:․․․
ገጽ 20 ኃጢአት የሠሩት መላእክት ምን ሆነዋል? ይሁዳ․․․
ገጽ 26 “ቍጣን ማነሣሣት” ምን ያስከትላል? ምሳሌ 30:․․․
● መልሶቹ በገጽ 11 ላይ ይገኛሉ
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. ያዕቆብና ዮሐንስ።
2. ጴጥሮስና እንድርያስ።
3. የአጥማቂው ዮሐንስ።
4. ከወንድሙ ከጴጥሮስ ጋር፤ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆነ።