በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሃይማኖት ለሰላም የቆመ ኃይል ነው?

ሃይማኖት ለሰላም የቆመ ኃይል ነው?

ሃይማኖት ለሰላም የቆመ ኃይል ነው?

በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቅዱስ ሴፐልከር ቤተ ክርስቲያን አንዳንዶች ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እጅግ ቅዱስ አድርገው ቢያዩትም ሌሎች ደግሞ የግጭትና የጥላቻ ተምሳሌት አድርገው ይመለከቱታል። አፈ ታሪክ እንደሚለው ከሆነ ይህ ቤተ ክርስቲያን “ክርስቶስ የተገደለበትና ከሞት የተነሳበት ስፍራ እንደሆነ ተደርጎ በሚታሰብ ቦታ ላይ የተገነባ” ነው። ይሁን እንጂ እንደ ቅዱስ የሚታየው ይህ ቦታ በርካታ ግጭቶችንም አስተናግዷል። ክርስቲያን ነን የሚሉ ስድስት ቡድኖች ቤተ ክርስቲያኑን ከመጠቀም መብት ጋር በተያያዘ ለረጅም ጊዜ እርስ በርስ ሲጋጩ ኖረዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በመካከላቸው ያለው ግጭት ተባብሷል። እንዲያውም በአንድ ወቅት መሣሪያ የታጠቁ ፖሊሶች በተከሰተው ግጭት ውስጥ ጣልቃ ገብተው ቤተ ክርስቲያኑን ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ግድ ሆኖባቸው ነበር።

በግጭት የተሞላ ታሪክ

በቅዱስ ሴፐልከር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሰቱት ነገሮች በደም መፋሰስና በጭፍጨፋ የተሞላው ረጅም ዘመን ያስቆጠረው የሃይማኖት ታሪክ ክፍል ናቸው። ቫዮለንስ ኢን ጎድስ ኔም የተሰኘው መጽሐፍ በቅርብ ጊዜ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ ባቀረበው ግምገማ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ከኢንዶኔዥያ እስከ ሰሜን አየርላንድ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ እስከ ካሽሚር፣ ከሕንድ እስከ ናይጄሪያ፣ ከባልካን አገሮች እስከ ስሪ ላንካ፣ ክርስቲያኖች፣ ቡዲስቶች፣ አይሁዶች፣ ሂንዱዎች፣ ሙስሊሞችና ሲኮች ለምን ግጭት ውስጥ እንደገቡ ሰበብ ሲያቀርቡ ሃይማኖታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንደሆነ ይናገራሉ።”

ሆኖም አብዛኞቹ ሃይማኖቶች መሠረታዊ መመሪያቸው ሰላምና ስምምነት እንደሆነ ይናገራሉ። በዘመናት ሁሉ ሃይማኖቶች ሰውን መውደድንና ለሰው ሕይወት አክብሮት ማሳየትን የመሳሰሉ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆኑ መርሆዎችን ሲሰብኩ ኖረዋል። ታዲያ ሃይማኖት ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር ኃይሉን ሰላም ለማምጣት መጠቀም አይገባውም ነበር? ቅን ልቦና ያላቸው ሃይማኖተኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ቆም ብለው እንዲያስቡ እናበረታታቸዋለን።