ኢየሱስ ‘የዓለምን ኃጢአት ያስወግዳል’
ኢየሱስ ‘የዓለምን ኃጢአት ያስወግዳል’
● መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኢየሱስ “የዓለምን ኃጢአት [እንደሚያስወግድ]” ተናግሯል። (ዮሐንስ 1:29) ይህ አባባል ኢየሱስ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆችን ለማዳን የሚጫወተውን ሚና ጎላ አድርጎ ይገልጻል።
ይሁንና ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን መሞት ያስፈለገው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ሕይወቱን በፈቃደኝነት መስጠቱ ምን ነገሮችን እንዲያከናውን አስችሎታል? ኢየሱስ በመሞቱ የሚጠቀሙት እነማን ናቸው? ኢየሱስ መሞቱ ለእርስዎ ምን ትርጉም አለው?
የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ለማክበር ይሰበሰባሉ። በዚህ ዓመት ይህ በዓል የሚውለው እሁድ፣ ሚያዝያ 9 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 17) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው።
የይሖዋ ምሥክሮች ከእነሱ ጋር በዚህ መታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝተው የኢየሱስ ሞት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንዲመረምሩ ሞቅ ያለ ግብዣ ያቀርቡልዎታል። መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የሚሰጣቸው መልሶችም ይብራራሉ።
እርስዎም በቤትዎ አቅራቢያ በሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች አዳራሽ ውስጥ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ መገኘት ይችላሉ። ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክዎ በአካባቢዎ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ያነጋግሩ።