ከምንወደው ሰው የተላከ ደብዳቤ
ከምንወደው ሰው የተላከ ደብዳቤ
● ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ ያነበበች አንዲት ሴት መጽሐፉን ከምንወደው ሰው ከተላከ ደብዳቤ ጋር በማመሳሰል እንዲህ ብላለች፦ “እያንዳንዱ ምዕራፍ ልብን በጥልቅ የሚነካ ሲሆን ይሖዋን ይበልጥ እንድትወዱት ያደርጋል። መጽሐፉን አንድ ጊዜ አንብቤ ጨርሻለሁ። ከምትወዱት ሰው የተላከላችሁን ደብዳቤ ደግማችሁ እንደምታነቡት ሁሉ እኔም መጽሐፉን እንደገና እስከምጀምረው ቸኩያለሁ።” ሌሎች ደግሞ ምን እንዳሉ ተመልከት።
በካንሳስ የምትኖር መጽሐፉን ያነበበች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ወደ ሰማዩ አባቴ ይበልጥ እንደቀረብኩ ይሰማኛል። ልቤ ለይሖዋ ባለኝ ፍቅር ተሞልቷል። . . . በየዕለቱ ጠዋት ተጨማሪ የመጽሐፉን ክፍሎች ለማንበብ እናፍቃለሁ። መጽሐፉን ወደፊትም ደግሜ ደጋግሜ አነብበዋለሁ።”
በሜን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት ሴት ደግሞ “መጽሐፉ ስለ ይሖዋ ሕልውና ያለኝን ግንዛቤ በእጅጉ አሳድጎልኛል” ስትል ጽፋለች፤ አክላም በገጽ 74 ላይ ያለው ስለ ትንሣኤ የሚናገረው ሐሳብ በእጅጉ እንዳጽናናት ገልጻለች። በአላስካ የምትኖር አንዲት ሴት ተመሳሳይ ሐሳብ አላት፦ “መጽሐፉ ልቤን ስለነካው እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም። . . . ወደፊትም ደጋግሜ አነብበዋለሁ፤ እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን አንዳንዶቹን ሐሳቦች ተመልሼ እመለከታቸዋለሁ።”
እርስዎም ይህን መጽሐፍ ቢያነቡ እንዲህ እንደሚሰማዎት እንተማመናለን። መጽሐፉ ከመጀመሪያዎቹ ሦስት የመግቢያ ምዕራፎች በኋላ “ታላቅ ኃይል ያለው፣” “ፍትሕን ይወዳል፣” “ልቡ ጠቢብ” እንዲሁም “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በሚሉ አራት ክፍሎች ተከፋፍሏል። የሚደመድመውም “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” በሚል ምዕራፍ ነው።
ይህን ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
❑ ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
❑ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።