በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ሉቃስ 17:11-19ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

ለውይይት፦

በሥጋ ደዌ ተይዘው ከነበሩት አሥር ሰዎች አንዱ ከሌሎቹ የተለየ ምን ነገር አድርጓል?

ፍንጭ፦ ሉቃስ 17:15, 16ን አንብብ።

አንተስ የእሱን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ቆላስይስ 3:15ን እና 1 ተሰሎንቄ 5:18ን አንብብ።

በየቀኑ ማመስገን ያለብህ ማንን ነው?

ፍንጭ፦ መዝሙር 107:8ን እና ያዕቆብ 1:17ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዳችሁ ይሖዋ አምላክን፣ ከቤተሰባችሁ አባላት መካከል አንዱን እንዲሁም ከቤተሰባችሁ ውጭ ያለ አንድ የምትወዱት ጓደኛችሁን እንድታመሰግኑ የሚያደርጋችሁን ቢያንስ አንድ ምክንያት ጻፉ። ከዚያም ለሁሉም አመስጋኝነታችሁን በተግባር ማሳየት የምትችሉባቸውን መንገዶች በዝርዝር አስፍሩ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 21 ሙሴ

ጥያቄ

ሀ. ሙሴ የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት እንዲጽፍ ይሖዋ በመንፈሱ መርቶታል?

ለ. የሙሴ ወላጆች ․․․․․ እና ․․․․․ ይባላሉ። ሙሴን ያሳደገችው ․․․․․ ․․․․․ ናት።

ሐ. መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘውን ይህንን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ ሙሴ “የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ . . .”

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ሙሴ ተአምር የመፈጸም ችሎታ የተሰጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ የመጀመሪያው ሰው ሲሆን በጥንቷ እስራኤል ውስጥ የአምላክ ነቢይ፣ ፈራጅ፣ ሕግ ሰጪ እና መሪ በመሆንም አገልግሏል። እስራኤላውያን፣ ሙሴን የሚመለከቱት ብዙ አስደናቂ ነገሮችን የፈጸመ ሰው እንደሆነ አድርገው ነው።—ዘዳግም 34:10-12፤ ዘፀአት 4:1-9

መልስ

ሀ. ዘፍጥረት፣ ዘፀአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኍልቍ፣ ዘዳግም እና ኢዮብ እንዲሁም መዝሙር 90ን እና መዝሙር 91ን ጽፏል።

ለ. እንበረም፣ ዮካብድ፣ የፈርዖን ልጅ።—ዘፀአት 1:15–2:10፤ 6:20

ሐ. “. . . በጽናት ቀጥሏል።”—ዕብራውያን 11:27

ሕዝቦችና አገሮች

4. ማምፒዮኖና እባላለሁ፤ የስምንት ዓመት ልጅ ነኝ። የምኖረው በማዳጋስካር ነው። በማዳጋስካር ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 10,000፣ 24,000 ወይስ 62,000?

5. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከማዳጋስካር በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

 

መልስ

  1. በሥጋ ደዌ ተይዘው የነበሩት ሰዎች 10 እንጂ 11 አይደሉም።

  2. በዚህ ዘገባ ላይ የተጠቀሱት የሥጋ ደዌ በሽተኞች በሙሉ ወንዶች ናቸው።

  3. ተመልሶ የመጣው የሥጋ ደዌ በሽተኛ ኢየሱስን ያመሰገነው ‘እግሩ ላይ ተደፍቶ’ ነው።

  4. 24,000