ንቁ! ኅዳር 2014 | ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልጉ ነገሮች

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ደስተኛ ለመሆን የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል። ከእነዚህ ውስጥ አራቱን እንደ ምሳሌ እንመልከት።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ የኢኳዶር መንግሥት የአማዞንን ደን ለመጠበቅ የያዘውን እቅድ መተዉ፣ ደም በኤች አይ ቪ የተበከለ መሆን አለመሆኑን በምርመራ ማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑ፣ እንደ ውሻና ድመት ባሉ የቤት እንስሳት የባለቤትነት ጥያቄ ዙሪያ የሚነሳ ክርክር

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልጉ ነገሮች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ምክር ደስተኛ እንድትሆን ሊረዳህ ይችላል? ይህ ርዕስ በዚህ ረገድ ውጤታማ የሆኑ አራት ነገሮችን ይዳስሳል።

አስደናቂ የምሕንድስና ጥበብ የሚታይባቸው የሮም የውኃ ማስተላለፊያዎች

በጥንት ዘመን የነበሩት ሮማውያን የውኃ ማስተላለፊያዎችን የገነቡት ለምንድን ነው? እነዚህን የውኃ ማስተላለፊያዎች አስደናቂ የሚያደርጋቸውስ ምንድን ነው?

ለቤተሰብ

ልጃችሁ ሲዋሽ

ልጃችሁ ሲዋሽ ምን ማድረግ አለባችሁ? በዚህ ርዕስ ላይ የቀረቡት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ምክሮች፣ ሐቀኛ መሆን ያለውን አስፈላጊነት ለልጃችሁ ለማስተማር ይረዷችኋል።

የሕይወት ታሪክ

በጣም በሚያስፈልገኝ ወቅት ያገኘሁት ተስፋ

ሚክሎሽ ሌክስ በ20 ዓመቱ በደረሰበት አሳዛኝ አደጋ ምክንያት መንቀሳቀስ የማይችል ሰው ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ እንዲኖረው የረዳው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ንጽሕና

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ንጹሕ እና ጤናማ እንዲሆኑ የረዷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች ተመልከት።

“ግልጽና ጠንካራ መልእክት ያዘለ መታሰቢያ”

በጃፓን ሂሮሺማ ሲቲ ውስጥ በ1945 በከፊል የፈራረሰ አንድ ሕንፃ ቆሞ የሚታየው ለምንድን ነው? ለየት ስላለው ስለዚህ ሕንፃ እና ይህ ሕንፃ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከገባቸው ተስፋዎች ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው አንብብ።

በተጨማሪም . . .

ሌሎችን መርዳት ያለብኝ ለምንድን ነው?

ለሌሎች ጥሩ ነገር ማድረግ ቢያንስ በሁለት መንገዶች ጥቅም ያስገኝልሃል። እነዚህ ሁለት ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

ወጣቶች ስለ ገንዘብ የሰጡት ሐሳብ

ገንዘብን መቆጠብ፣ በአግባቡ መጠቀም እንዲሁም ለገንዘብ ተገቢ አመለካከት መያዝ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት

ሚርያም የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ

ሚርያም የተጫወተችው የሙዚቃ መሣሪያ ምን ይባላል? ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ በማውረድ መልሱን ማወቅ ትችላለህ።