በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

በቅርብ የወጡ የመጠበቂያ ግንብ እትሞችን አንብበሃልን? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 5:​3-5 ላይ ካሰፈረው ዝርዝር መካከል ተስፋን መጨረሻ ላይ የጠቀሰው ለምንድን ነው?

ጳውሎስ ክርስቲያኖች የሚያጋጥሟቸውን ነገሮች መከራ፣ ጽናት፣ የአምላክ ሞገስ እና ተስፋ በማለት በዝርዝር አስፍሯቸዋል። እዚህ ላይ የተጠቀሰው “ተስፋ” አንድ ሰው ገና መጀመሪያ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ሲማር የሚያገኘው ተስፋ ሳይሆን በጊዜ ብዛት የሚያገኘውን ይበልጥ የጠነከረ፣ የጠለቀና ከሕልውናው ጋር የተዋሃደ ተስፋ ነው።​—⁠12/15 ገጽ 22-3

በዛሬው ጊዜ አንድ ክርስቲያን በጥንቷ ግሪክ ይደረጉ ስለነበሩ የአትሌቲክስ ውድድሮች የማወቅ ፍላጎት ሊያድርበት የሚችለው ለምንድን ነው?

የእነዚያን ጨዋታዎች ምንነትና የሚካሄዱባቸውን ደንቦች ማወቃችን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ግልጽ እንዲሆኑልን ይረዳናል። ከእነዚህ ጥቅሶች አንዳንዶቹ ‘በደንቡ መሠረት መታገልን፣’ ‘ሸክምን ሁሉ ማስወገድና የኢየሱስን ምሳሌ መመልከትን፣’ ‘እስከ መጨረሻው መሮጥንና’ አክሊል ወይም ሽልማት ማግኘትን ይጠቅሳሉ። (2 ጢሞቴዎስ 2:​5፤ 4:​7, 8፤ ዕብራውያን 12:​1, 2፤ 1 ቆሮንቶስ 9:​24, 25፤ 1 ጴጥሮስ 5:​4)​—⁠1/1 ገጽ 28-30

ምሥራቹን በመስበክ ረገድ ከጥር 1914 ጀምሮ ጥቅም ላይ የዋለው አዲስ ዘዴ ምንድን ነው?

በዚህ ዓመት “የፍጥረት ፎቶ ድራማ” መውጣቱ ተነገረ። አራት ክፍሎች ያሉት ይህ ድራማ ተንቀሳቃሽ ሥዕሎችንና በመቶ የሚቆጠሩ ባለ ቀለም የስላይድ ፊልሞችን ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም አብዛኞቹ በሸክላ ላይ ከተቀዱ ንግግሮች ጋር ተቀነባብረው የተቀረጹ ናቸው። ሃያ ቅጂዎች ያሉት ይህ ድራማ የተዘጋጀውና በሰፊው ጥቅም ላይ የዋለው የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለሰዎች ለማስተማር ነው።​—⁠1/15 ገጽ 8-9

የአስተዳደር አካሉን ከሕጋዊው ማኅበር የሚለየው ምንድን ነው?

የሕጋዊው ማኅበር ዲሬክተሮች የሚመረጡት በአባላቱ የድምፅ ብልጫ ሲሆኑ የአስተዳደር አካል አባላት የሚሾሙት ግን በሰው ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ማኅበራት ዲሬክተሮች የግድ የአስተዳደር አካል አባላት መሆን አያስፈልጋቸውም። የፔንሲልቬኒያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር በቅርቡ ባደረገው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ፣ የማኅበሩ ዲሬክተሮችና ኃላፊዎች ሆነው ያገለግሉ የነበሩት የአስተዳደር አካል አባላት ኃላፊነታቸውን በፈቃደኝነት ለቅቀዋል። ‘ከሌሎች በጎች’ ክፍል የሆኑ የጎለመሱ ወንድሞች በቦታቸው ተተክተዋል። (ዮሐንስ 10:​16) ይህም የአስተዳደር አካል አባላት መንፈሳዊ ምግብ ለማዘጋጀትና የዓለም አቀፉን የወንድማማች ማኅበር መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት የበለጠ ጊዜ እንዲያገኙ ያስችላል።​—⁠1/15 ገጽ 29, 31

የተስፋ መቁረጥ ስሜትን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ለመማር የትኞቹን ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች መመርመር እንችላለን?

አንደኛዋ ምሳሌ የሳሙኤል እናት የነበረችው ሐና ነች። የእስራኤል ሊቀ ካህን የነበረው ዔሊ ድርጊቷን በመጥፎ ሲተረጉምባት ተስፋ ልትቆርጥ ትችል ነበር። ከዚህ ይልቅ በግልጽ ሆኖም በአክብሮት እውነቱን አስረድታዋለች። ከዚህም በተጨማሪ ሐና በዔሊ ላይ ቂም አልያዘችበትም። ሁለተኛው ምሳሌ ማርቆስ ሲሆን ማርቆስ ሐዋርያው ጳውሎስ በሚስዮናዊ ጉዞው አብሮት እንዲሄድ ባልፈለገ ጊዜ ቅር ተሰኝቶ መሆን አለበት። አብሮ የመሄድ መብቱን ሲነፈግ ቅስሙ እንዲሰበር ከመፍቀድ ይልቅ ከበርናባስ ጋር በመጓዝ አገልግሎቱን ቀጥሏል።​—⁠2/1 ገጽ 20-2

ክርስቲያኖች የኮምፒውተር ሶፍትዌር ፕሮግራም ቅጂዎችን ለሌሎች መስጠትን ወይም ከሌሎች መቀበልን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባቸው ለምንድን ነው?

የኮምፒውተር ጨዋታዎችን ጨምሮ አብዛኞቹ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች የተጠቃሚነት ፈቃድ የሚኖራቸው ሲሆን ይህም ባለንብረቱ/ተጠቃሚው ፕሮግራሙን ከአንድ በላይ ኮምፒውተሮች ውስጥ እንዳይጨምር ያግደዋል። ቅጂዎቹን የምንሰጠው በነፃ ቢሆንም እንኳ አባዝቶ ለሌሎች መስጠት ስለ ባለቤትነት መብት የወጣውን ሕግ የሚጥስ ነው። ክርስቲያኖች ‘የቄሣርን ለቄሣር በመስጠት’ ለሕግ ተገዥ መሆን ይፈልጋሉ። (ማርቆስ 12:​17)​—⁠2/15 ገጽ 28-9

ሲረል እና መቶድየስ እነማን ናቸው? ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያበረከቱት አስተዋጽኦስ ምንድን ነው?

ሲረል እና መቶድየስ በዘጠነኛው መቶ ዘመን ግሪክ ተሰሎንቄ ውስጥ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ለስላቭ ቋንቋዎች ፊደል የቀረጹ ሲሆን አብዛኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወደ ስላቮን ቋንቋ ተርጉመዋል።​—⁠3/1 ገጽ 28-9

“ስለ መንፈስ ማሰብ” የሚለው አነጋገር ምን ማለት ነው?​—⁠ሮሜ 8:​6

ስለ መንፈስ ማሰብ ማለት በይሖዋ አንቀሳቃሽ ኃይል ሥር መሆን፣ ለእሱ ራስን ማስገዛትና በዚያ መመራት ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና በማጥናት፣ የአምላክን ሕግ ከልብ በመታዘዝ እንዲሁም መንፈሱን ለማግኘት በመጸለይ የአምላክ መንፈስ በውስጣችን እንዲሠራ መፍቀድ እንችላለን።​—⁠3/15 ገጽ 15

ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚረዱን ቢሰማን ምን ማድረግ እንችላለን?

ጉዳዩን በፍቅር መንፈስ በግልጽ ማስረዳቱ አስፈላጊ ነው። በዚህ መንገድ የማይሳካ ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ። ‘ልብን የሚመዝነው ይሖዋ’ ሁኔታውን እንዲገነዘብልህና እንዲረዳህ ጸልይ። (ምሳሌ 21:​2፤ 1 ሳሙኤል 16:​7)​—⁠4/1 ገጽ 21-3