‘ላገኘነው ሃይማኖታዊ ነፃነት የይሖዋ ምሥክሮችን አመስግኑ’
‘ላገኘነው ሃይማኖታዊ ነፃነት የይሖዋ ምሥክሮችን አመስግኑ’
ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በተባለ ጋዜጣ ላይ የወጣ አንድ ርዕስ “አንድ የይሖዋ ምሥክር ቤታችሁ ሲመጣ በራችሁን እላዩ ላይ ከመዝጋታችሁ በፊት ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ያለ አግባብ የተፈጸመባቸውን በደል እንዲሁም የመጀመሪያው ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ እንዲደረግና ሁላችንም ነፃነት እንድናገኝ ያበረከቱትን የላቀ አስተዋጽኦ ቆም ብላችሁ አስቡ” ይላል። የይሖዋ ምሥክሮች በ1940ዎቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ስደት ይደርስባቸው የነበረ ሲሆን ለዚህም አንዱ ምክንያት ለሰንደቅ ዓላማ ሰላምታ አንሰጥም ማለታቸው ነው።—ዘጸአት 20:4, 5
የዩ ኤስ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከ1938 እስከ 1943 ድረስ ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮችን የሚመለከቱ 30 ክሶችን መርምሯል። ጽሑፉ ሐሳቡን ሲቀጥል “ምሥክሮቹ የመጀመሪያው ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያን በተመለከተ በተደጋጋሚ ጊዜ መሠረታዊ ጉዳዮችን በማንሳታቸው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ሃርለን ፊስክ ‘የይሖዋ ምሥክሮች ከዜጎች መብት መከበር ጋር በተያያዘ ሕግ ነክ ለሆኑ ጉዳዮች ላስገኙት መፍትሔ ወሮታ ሊከፈላቸው ይገባ ነበር’ በማለት ጽፈዋል” ይላል።
ጽሑፉ በማጠቃለያው ላይ “[ለሃይማኖታዊ] ነፃነት መገኘት ሁሉም ሃይማኖቶች የይሖዋ ምሥክሮችን ማመስገን ይኖርባቸዋል” ሲል ጠቅሷል።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
ከበስተ ጀርባ የሚታየው፣ ሕንፃ:- Photo by Josh Mathes, Collection of the Supreme Court of the United States፤ ከታች በስተ ግራ፣ ዳኞች:- Collection of the Supreme Court of the United States