በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከቀኖች ሁሉ የላቀው ቀን

ከቀኖች ሁሉ የላቀው ቀን

ከቀኖች ሁሉ የላቀው ቀን

የሰው ዘር ዘላለማዊ በረከት ማግኘት የሚችልበትን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ዕለት ነው። የዚህን ያህል በሰው ዘር የወደፊት ዕጣ ላይ ትልቅ ለውጥ ያስከተለ ሌላ ቀን የለም። ዕለቱ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበትን ዓላማ የፈጸመበት ቀን ነው። በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ ሲያጣጥር ከቆየ በኋላ “ተፈጸመ” ብሎ በሞት አንቀላፋ። (ዮሐንስ 19:30) ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለምን ዓላማ ነበር?

መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” ይላል። (ማቴዎስ 20:28) ኢየሱስ ከወረሱት ኃጢአትና ሞት ሰዎችን ለመዋጀት ሲል ነፍሱን ወይም ሕይወቱን ሰጥቷል። አዎን፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል።” (ዮሐንስ 3:16) የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት እንዴት ያለ ታላቅ ዝግጅት ነው!

ኢየሱስ የሞተበት ዕለት ከቀኖች ሁሉ የላቀ ቀን የሆነበት ሌላም ምክንያት አለ። በዚያን ዕለት የአምላክ ልጅ ሐዋርያቱ በታማኝነት እንዲጸኑ የሚረዳቸው ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷቸዋል። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በሰጣቸው ትምህርት ምንኛ ልባቸው ተነክቶ ይሆን! ኢየሱስ የሰጣቸው ትምህርት ምን ነበር? ለእነርሱ ከሰጣቸው ትምህርት ምን ጥቅም ማግኘት እንችላለን? የሚቀጥለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።