ወጣቶች፣ ለይሖዋ እንደሚገባ ተመላለሱ
ወጣቶች፣ ለይሖዋ እንደሚገባ ተመላለሱ
አንዳንድ ክርስቲያን ወጣቶች ለጊዜውም ቢሆን ከቤተሰቦቻቸውና ከጉባኤያቸው ርቀው ለመኖር የተገደዱበት ጊዜ አለ። አንዳንዶች ይህን ያደረጉት አገልግሎታቸውን ለማስፋት ሲሆን ሌሎች ደግሞ በዚህ ዓለም ጉዳዮች ረገድ የገለልተኝነት አቋማቸውን በመጠበቃቸው ምክንያት ነው። (ኢሳይያስ 2:4፤ ዮሐንስ 17:16) በአንዳንድ አገሮች ‘ቄሣር’ አቋማቸውን ለማላላት ፈቃደኛ የማይሆኑ ወጣቶች እንዲታሠሩ አሊያም ሕዝባዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈርዶባቸዋል። a—ማርቆስ 12:17፤ ቲቶ 3:1, 2
እነዚህ ወጣቶች በገለልተኝነት አቋማቸው ምክንያት ሲታሰሩ ረዘም ላለ ጊዜ መጥፎ ሥነ ምግባር ካላቸው ሰዎች ጋር ለመቆየት ይገደዱ ይሆናል። በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከቤታቸው መራቃቸውም ሥነ ምግባር የጎደላቸው ሰዎች ባሉበት አካባቢ እንዲሠሩ ያስገድዳቸዋል። እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ክርስቲያን ወጣቶች ወይም አዋቂዎች ‘ለአምላክ እንደሚገባ ለመመላለስ’ በሚያደርጉት ጥረት የሚገጥማቸውን ተጽዕኖ በተሳካ መንገድ መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው? (1 ተሰሎንቄ 2:12) ወላጆቻቸውስ ወደፊት ሊገጥማቸው ለሚችል አስቸጋሪ ሁኔታ ከወዲሁ ሊያዘጋጁአቸው የሚችሉት እንዴት ነው?—ምሳሌ 22:3
ወጣቶች የሚያጋጥሟቸው ለየት ያሉ ችግሮች
ከቤቱ ርቆ 3 ዓመት ከ1 ወር ለመቆየት የተገደደ ታኪስ የሚባል አንድ የ21 ዓመት ወጣት እንዲህ ይላል:- “ጥበቃቸው ከማይለየኝ ወላጆቼና አሳምረው ከሚያውቁኝ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጉያ መራቅ አስቸጋሪና የሚያስፈራም ነበር።” b አክሎም “አንዳንድ ጊዜ ያለ ረዳት የቀረሁ ምስኪን እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር” ብሏል። የ20 ዓመቱ ጴጥሮስ ደግሞ ከሁለት ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ ከቤት ርቆ ለመኖር ተገድዷል። እሱም “በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ መዝናኛንና የጓደኛ ምርጫን በሚመለከት ማንንም ሳላማክር የራሴን ውሳኔ ማድረግ ነበረብኝ። አንዳንድ ጊዜ የማደርጋቸው ውሳኔዎች ግን ትክክል አልነበሩም” በማለት ተናግሯል። ከዚያም “ያገኘሁት ተጨማሪ ነፃነት ያስከተለብኝ ከፍተኛ ኃላፊነት ያስጨንቀኝ ነበር” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር አዘውትሮ የሚገናኝ ታሶስ የሚባል ክርስቲያን ሽማግሌ “ወጣቶች ከተዘናጉና ጥንቃቄ ካላደረጉ እምነታችንን የማይጋሩ እኩዮቻቸው ጸያፍ አነጋገር፣ ዓመጸኝነትና ጠበኝነት በቀላሉ ሊጋባባቸው ይችላል” ብሏል።
እነዚህ ወጣቶች ለመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አክብሮት ከሌላቸው ሰዎች ጋር ሲኖሩና ሲሠሩ የእኩዮቻቸውን ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነና ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ አካሄድ እንዲኮርጁ የሚደርስባቸውን ፈተና ነቅተው መከላከል ያስፈልጋቸዋል። (መዝሙር 1:1፤ 26:4፤ 119:9) ዘወትር የግል ጥናት የማድረግ፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የመገኘትና በመስክ አገልግሎት የመካፈል ጥሩ ልማድ ማዳበር አስቸጋሪ መስሎ ሊታይ ይችላል። (ፊልጵስዩስ 3:16) መንፈሳዊ ግቦችን ማውጣትና እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ መጣጣርም ቀላል ላይሆን ይችላል።
ታማኝ የሆኑ ክርስቲያን ወጣቶች በጠባያቸውና በንግግራቸው ይሖዋን ማስደሰት እንደሚፈልጉ ጥርጥር የለውም። የሰማዩ አባታቸው “ልጄ ሆይ፣ ጠቢብ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኘው፣ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ” በማለት ያቀረበላቸውን ጥሪ በታማኝነት ምሳሌ 27:11) ያላቸው ጥሩ ጠባይ ሰዎች ለይሖዋና ለሕዝቡ በሚኖራቸው አመለካከት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ይገነዘባሉ።—1 ጴጥሮስ 2:12
ይቀበላሉ። (ደስ የሚለው እንደዚህ ካሉት ወጣቶች አብዛኞቹ ‘በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ ከደስታም ጋር በሁሉ በመጽናትና በመታገሥ ለጌታ እንደሚገባ ተመላለሱ’ በማለት ሐዋርያው ጳውሎስ እንደጸለየላቸው የመጀመሪያው መቶ ዘመን ወንድሞቻቸው ለመሆን የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። (ቆላስይስ 1:9-12) መጽሐፍ ቅዱስ ባዕድ፣ ክፉና ጣዖት አምላኪ በሆነ ሕዝብ መካከል ቢኖሩም ለአምላክ እንደሚገባ የተመላለሱ ፈሪሃ አምላክ የነበራቸው አያሌ ወጣቶችን ምሳሌ ይዞልናል።—ፊልጵስዩስ 2:14, 15
‘ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ነበረ’
የያዕቆብና የራሔል ተወዳጅ ልጅ የነበረው ዮሴፍ ገና በለጋ ዕድሜው ለባርነት ተሸጦ ፈሪሃ አምላክ ከነበረው አባቱ ርቆ በሚገኝ ቦታ እንዲኖር ወደ ግብፅ ተወሰደ። ወጣቱ ዮሴፍ በታታሪነቱ፣ እምነት የሚጣልበት በመሆኑና በሥነ ምግባራዊ አቋሙ የሚደነቅ ምሳሌ ትቷል። የይሖዋ አምላኪ ያልነበረው የጲጥፋራ ባሪያ ቢሆንም ዮሴፍ ጥንቁቅና ትጉ ስለነበረ የኋላ ኋላ ጌታው የቤቱን ጉዳይ ሁሉ ለእርሱ በኃላፊነት ሰጠው። (ዘፍጥረት 39:2-6) ዮሴፍ ለይሖዋ ታማኝ በመሆኑ ምክንያት ወደ ወህኒ ቢጣልም “ታማኝ መሆን ምን ዋጋ አለው?” የሚል መደምደሚያ ላይ አልደረሰም። በእሥር ቤትም ግሩም የሆኑ ባሕርያትን በማሳየቱ ወዲያው በግዞት ቤቱ ውስጥ ያሉትን ጥቃቅን ጉዳዮች እንኳን ሳይቀር እንዲቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጠው። (ዘፍጥረት 39:17-22) አምላክም የባረከው ሲሆን ዘፍጥረት 39:23 እንደሚናገረው “እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ።”
ዮሴፍ ፈሪሃ አምላክ ካላቸው ወላጆቹ ርቆ ቢኖርም አካሄዱን በዙሪያው ካሉት አረማውያን ጋር ማስማማትና የግብፃውያንን ሥነ ምግባር የጎደለው አኗኗር መኮረጅ ይቀለኛል ብሎ አላሰበም! ከዚህ ይልቅ ከባድ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም የአምላክን መሠረታዊ ሥርዓቶች የሙጥኝ በማለት ንጹሕ አቋሙን ጠብቋል። የጲጥፋራ ሚስት ከእርሷ ጋር ግንኙነት እንዲፈጽም በተደጋጋሚ ስትወተውተው “እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ሰጣት።—ዘፍጥረት 39:7-9
ዛሬም ወጣት ምሥክሮች ተገቢ ካልሆነ ባልንጀርነት፣ ከሥነ ምግባር ውጭ ከሆነ መዝናኛ፣ ከወሲባዊ ሥዕሎችና ጽሑፎች እንዲሁም ከወራዳ ሙዚቃዎች እንዲርቁ የሚሰጣቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ማስጠንቀቂያ ማዳመጥ ያስፈልጋቸዋል። ‘የይሖዋ ዓይኖች በስፍራ ሁሉ እንደሆኑና ክፉዎችንና ደጎችን እንደሚመለከቱ’ ይገነዘባሉ።—ምሳሌ 15:3
ሙሴ “በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ” ርቋል
ሙሴ ያደገው ጣዖት አምልኮና ተድላ ማሳደድ ጎልቶ በሚታይበት የፈርዖን ቤተ መንግሥት ነበር። መጽሐፍ ዕብራውያን 11:24, 25
ቅዱስ እርሱን በሚመለከት “ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ . . . ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ” በማለት ይናገራል።—በዓለም ካሉ ሰዎች ጋር መወዳጀት አንዳንድ ጥቅሞች ሊኖሩት ቢችልም ጥቅሙ ጊዜያዊ ነው። እጅግ ቢበዛ የሚቆየው ይህ ዓለም እስከሚጠፋበት ጊዜ ድረስ ነው። (1 ዮሐንስ 2:15-17) ታዲያ የሙሴን አርዓያ መከተሉ የተሻለ አይሆንም? መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴ ‘የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአል’ በማለት ይናገራል። (ዕብራውያን 11:27) ትኩረቱን ፈሪሃ አምላክ ለነበራቸው የቀድሞ አባቶቹ በተሰጣቸው መንፈሳዊ ውርሻ ላይ አድርጓል። የይሖዋን ዓላማ እንደ ዓላማው አድርጎ በመመልከት የአምላክን ፈቃድ መፈጸምን የሕይወቱ ግብ አድርጎታል።—ዘጸአት 2:11፤ ሥራ 7:23, 25
ለአምላክ አክብሮት በሌለው ክፉ ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወጣቶች በግል ጥናት አማካኝነት “የማይታየውን” አምላክ ይበልጥ በማወቅ ከይሖዋ ጋር ያላቸውን የግል ዝምድና ማጠናከር ይችላሉ። ወጣቶች በጉባኤ ስብሰባዎች አዘውትሮ መገኘትንና በመስክ አገልግሎት መካፈልን በመሳሰሉ ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴዎች የተሟላ ተሳትፎ ማድረጋቸው አእምሯቸው በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ይረዳቸዋል። (መዝሙር 63:6፤ 77:12) እንደ ሙሴ ያለ ጠንካራ እምነትና ተስፋ ለማዳበር መጣር ይኖርባቸዋል። የይሖዋ ወዳጅ የመሆን መብታቸውን በአድናቆት በመመልከት አስተሳሰባቸውና ድርጊታቸው በእርሱ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ አለባቸው።
አንደበቷን አምላክን ለማመስገን ተጠቅማበታለች
ከቤተሰቧ ርቃ ብትኖርም በጥሩ ምሳሌነት የምትጠቀሰው ሌላዋ ወጣት ደግሞ የአምላክ ነቢይ በነበረው በኤልሳዕ ዘመን በሶርያውያን ተማርካ የተወሰደችው እስራኤላዊት ወጣት ነች። እዚያም የሠራዊት አለቃ ለነበረው ለለምጻሙ ለንዕማን ሚስት አገልጋይ ሆነች። ይህች ወጣት “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር” በማለት ለእመቤቷ ነገረቻት። በዚህ የተነሳ ንዕማን በእስራኤል ወደሚገኘው ወደ ኤልሳዕ ሄዶ ከመፈወሱም በላይ የይሖዋ አምላኪ ሆኗል።—2 ነገሥት 5:1–3, 13-19
የዚህች ወጣት ምሳሌነት ወጣቶች ከወላጆቻቸው ኤፌሶን 5:4፤ ምሳሌ 15:2) በገለልተኝነት አቋሙ ምክንያት እሥር ቤት ገብቶ የነበረው በ20ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ የሚገኘው ኒኮስ የተባለ ወጣት “ከወላጅና ከጉባኤ ቁጥጥር ርቄ ከአንዳንድ ወጣት ወንድሞች ጋር የእርሻ ሥራ በሚያካሂድ እሥር ቤት ሳለሁ አነጋገራችን እየተበላሸ እንደሄደ አስተዋልኩ። አነጋገራችን በእርግጥ ለይሖዋ ክብር የሚያመጣ አልነበረም” በማለት ትዝታውን ያወሳል። ደግነቱ ኒኮስም ሆነ ሌሎች ጳውሎስ በዚህ ጉዳይ ላይ “ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኩሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ” በማለት የሰጠውን ምክር ተቀብለዋል።—ኤፌሶን 5:3
ርቀው በሚኖሩበት ጊዜም እንኳን አንደበታቸውን አምላክን በሚያስከብር መንገድ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ በጥብቅ ያሳስባል። ይህች ወጣት ‘የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ’ የመናገር ልማድ ቢኖራት ኖሮ አጋጣሚው ሲፈጠር አፏን ሞልታ መናገር ትችል ነበር? (ይሖዋ ለእነርሱ እውን ነበር
በጥንቷ ባቢሎን የዳንኤል ጓደኞች የነበሩት የሦስቱ ዕብራውያን ተሞክሮ ኢየሱስ በትንሹ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ እንደሚሆን ለተናገረው ሐቅ ምሥክር ነው። (ሉቃስ 16:10) በሙሴ ሕግ የተከለከሉ ምግቦችን እንዲበሉ በተጠየቁ ጊዜ በባዕድ አገር ምርኮኞች ስለሆኑ ከመብላት ሌላ ምንም ምርጫ እንደሌላቸው ማሳበብ ይችሉ ነበር። ሆኖም ትንሽ ይመስል የነበረውን ይህን ጉዳይ አክብደው በመመልከታቸው ምንኛ ተባርከዋል! ከንጉሡ ማዕድ ከተመገቡት ሌሎች ምርኮኞች ይልቅ ጤነኞችና ጥበበኞች ሆነው ተገኙ። በጣዖት ምስል ፊት ወድቀው እንዲሰግዱ ትልቅ ፈተና በገጠማቸው ጊዜ ከአቋማቸው ዝንፍ እንዳይሉ የረዳቸው በእነዚህ ጥቃቅን ነገሮች ታማኝ መሆናቸው ስላበረታቸው እንደሚሆን አያጠራጥርም።—ዳንኤል 1:3–21፤ 3:1-30
ይሖዋ ለእነዚህ ሦስት ወጣቶች እውን ነበር። ከቤታቸውና ከይሖዋ አምልኮ ማዕከል ርቀው ይኖሩ የነበረ ቢሆንም የዓለም እድፍ እንዳይጋባባቸው ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል። (2 ጴጥሮስ 3:14) ለእነሱ ከይሖዋ ጋር ያላቸው ዝምድና እጅግ ውድ ስለነበር ሕይወታቸውን እንኳን መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኞች ነበሩ።
ይሖዋ አይተዋችሁም
ወጣቶች ከሚወዷቸውና ከሚያምኗቸው ቤተሰቦቻቸው ርቀው ሲኖሩ ግራ ሊጋቡና ስጋት ሊያድርባቸው ይችላል። ይሁን እንጂ ‘ይሖዋ እንደማይጥላቸው’ ሙሉ በሙሉ በመተማመን ፈተናዎቻቸውንና ችግሮቻቸውን መዝሙር 94:14) እንደዚህ ያሉ ወጣቶች ‘ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባቸው’ ይሖዋ ከእነሱ ጋር በመሆን “በጽድቅ መንገድ” መሄዳቸውን እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል።—1 ጴጥሮስ 3:14፤ ምሳሌ 8:20
ሁሉ ሊጋፈጡ ይችላሉ። (ይሖዋ ዮሴፍን፣ ሙሴን፣ እስራኤላዊቷን ወጣት አገልጋይና ሦስቱን ታማኝ ዕብራውያን ወጣቶች ሁልጊዜ ያበረታቸው እንዲሁም በእጅጉ ይባርካቸው ነበር። ዛሬም “የዘላለምን ሕይወት” ግብ አድርገው “መልካሙን የእምነት ገድል” የሚጋደሉትን ለመደገፍ ቅዱስ መንፈሱን፣ ቃሉንና ድርጅቱን በመጠቀም ላይ ነው። (1 ጢሞቴዎስ 6:11, 12) አዎን፣ ለይሖዋ እንደሚገባ መመላለስ በእርግጥ ይቻላል፣ ደግሞም እንዲህ ማድረጉ የጥበብ አካሄድ ነው።—ምሳሌ 23:15, 19
[የግርጌ ማስታወሻ]
a የግንቦት 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-20ን ተመልከት።
b አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።
[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ወላጆች—ልጆቻችሁን አዘጋጁአቸው!
“በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፣ የጎልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው።” (መዝሙር 127:4) ፍላጻ ወይም ቀስት እንዲሁ በአጋጣሚ ዒላማውን አይመታም። በትክክል መነጣጠር አለበት። በተመሳሳይም ልጆች ተገቢውን የወላጅ ሥልጠና ካላገኙ ከቤተሰባቸው ርቀው በሚኖሩበት ጊዜ የሚያጋጥማቸውን ችግር መቋቋም አይችሉም።—ምሳሌ 22:6
ወጣቶች በስሜታዊነት አንድ ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ ወይም “ለጎልማሳነት ምኞት” ለመሸነፍ የተጋለጡ ናቸው። (2 ጢሞቴዎስ 2:22) መጽሐፍ ቅዱስ “በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፤ ያልተቀጣ ብላቴና ግን እናቱን ያሳፍራል” በማለት ያስጠነቅቃል። (ምሳሌ 29:15) አንድ ወጣት የልጅነት ባሕርይውን የማያሻሽል ከሆነ ከቤት ርቆ በሚኖርበት ጊዜ የሚያጋጥመውን ችግርና የኑሮ ጫና ለማሸነፍ ብቃቱ አይኖረውም።
ክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸው በዚህ ሥርዓት ያሉትን ችግሮች፣ ተጽዕኖዎችና የሕይወት እውነታዎች እንዲያውቁ ግልጽ በሆነና ኃላፊነት እንዲሰማቸው በሚያደርግ መንገድ ማስረዳት ይኖርባቸዋል። በአሉታዊ ጎኑ ላይ ብቻ ሳያተኩሩ አንድ ወጣት ከቤቱ ርቆ ሲኖር ሊያጋጥሙት ስለሚችሉት መጥፎ ሁኔታዎች ሊገልጹለት ይችላሉ። ይህ ሥልጠና ከአምላክ የሚገኘው ማስተዋል ታክሎበት ‘ለአላዋቂዎች ብልሃትን ለጎበዛዝትም እውቀትና ጥንቃቄን ይሰጣል።’—ምሳሌ 1:4
በልጆቻቸው ልብ ውስጥ አምላካዊ እሴቶችንና የሥነ ምግባር መመሪያዎችን የሚተክሉ ወላጆች ልጆቻቸው የሕይወትን ችግሮች እንዲያሸንፉ ያስችሏቸዋል። ዘወትር በቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት፣ ግልጽ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግና ለልጆች ደህንነት ከልብ ማሰብ ለስኬታማነት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ይህ ባይደረግ ደግሞ ኪሳራው የዚያኑ ያህል ይሆናል። ወላጆች ለልጆቻቸው መለኮታዊ ሥልጠና ሲሰጡ ሚዛናዊ ሆኖም አዎንታዊና ምክንያታዊ በመሆን የኋላ ኋላ የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ ብቃት እንዲኖራቸው ሊያዘጋጅዋቸው ይችላሉ። እናንተ ራሳችሁ ምሳሌ በመሆን ልጆቻችሁ በዓለም ቢኖሩም የዓለም ክፍል አለመሆን እንደሚችሉ አስተምሯቸው።—ዮሐንስ 17:15, 16
[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አንዳንድ ክርስቲያን ወጣቶች ከቤታቸው ርቀው ለመኖር ይገደዳሉ
[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ወጣቶች ተፈታታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም የዮሴፍን ምሳሌ ሊኮርጁና በሥነ ምግባር ንጹሕ ሆነው ሊኖሩ ይችላሉ
[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አንደበቷን ይሖዋን ለማመስገን የተጠቀመችውን እስራኤላዊት ወጣት ምሰሉ