በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ አገልጋዮች በዛፍ የተመሰሉት በምን መንገድ ነው?

የአምላክ አገልጋዮች በዛፍ የተመሰሉት በምን መንገድ ነው?

የአምላክ አገልጋዮች በዛፍ የተመሰሉት በምን መንገድ ነው?

መዝሙራዊው በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ደስ ስለሚለውና በሕይወቱ ውስጥ ተግባራዊ ስለሚያደርጋቸው ሰው ሲናገር እንዲህ ብሏል:- “እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።” (መዝሙር 1:1-3) ይህ ንጽጽር ተስማሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ዛፎች ለረጅም ዘመን ሊኖሩ ይችላሉ። ለአብነት ያህል፣ በሜዲትራኒያን አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ የወይራ ዛፎች ከአንድ እስከ ሁለት ሺህ ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው ይነገራል። በተመሳሳይም በመካከለኛው አፍሪካ የሚገኙት የባኦባብ ዛፎች ረጅም ዕድሜ ያላቸው ሲሆን ብሪስልኮን የተባለ በካሊፎርኒያ የሚገኝ የጥድ ዝርያ 4,600 ዓመታት ገደማ ዕድሜ እንዳለው ይገመታል። በደን ውስጥ ያሉ ትልልቅ ዛፎች ብዙውን ጊዜ ለአካባቢያቸው ጥቅም ይሰጣሉ። ለምሳሌ ረዣዥም ዛፎች ለጋ ለሆኑት ዛፎች ጥላ ይሆኗቸዋል፤ ከዚህም በላይ ከእነዚህ ዛፎች የሚረግፈው ቅጠል ለአፈሩ ማዳበሪያ ይሆናል።

በዓለም ላይ ያሉት አብዛኞቹ ረጃጅም ዛፎች የሚገኙት ጥቅጥቅ ባሉ ደኖች ውስጥ እርስ በርስ ተደጋግፈው ነው። እጅብ ብለው የበቀሉ ዛፎች ሥሮቻቸው እርስ በርስ ስለሚጠላለፉ ብቻውን ሜዳ ላይ ከሚገኝ ዛፍ ይልቅ አውሎ ነፋስን መቋቋም ይችላሉ። ብዙ ሥሮች ያሉት ዛፍ ከአፈር ውስጥ በቂ ውኃና ምግብ ማግኘት ይችላል። የአንዳንድ ዛፎች ሥሮች ከዛፉ ቁመት ይበልጥ ወደ መሬት ውስጥ ጠልቀው ሊገቡ ወይም ቅርንጫፎቻቸው ከሚሸፍኑት ቦታ የበለጠ ወደ ጎን ሊሄዱ ይችላሉ።

ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ‘በክርስቶስ ተተክለውና [‘ሥር ሰደውና፣’ የ1954 ትርጉም] ታንጸው፣ በእምነት ጸንተው መኖር’ እንዳለባቸው ሲናገር ዛፍን በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል። (ቆላስይስ 2:6, 7) በእርግጥም ክርስቲያኖች መጽናት የሚችሉት በክርስቶስ ሥር ሰደው ከቆሙ ብቻ ነው።—1 ጴጥሮስ 2:21

የአምላክ አገልጋዮች ከዛፍ ጋር ሊመሳሰሉ የሚችሉባቸው ሌሎች መንገዶች የትኞቹ ናቸው? በጫካ ውስጥ ያሉ ዛፎች እርስ በርሳቸው እንደሚደጋገፉ ሁሉ ከክርስቲያን ጉባኤ ጋር ተቀራርበው የሚኖሩ በሙሉ ከእምነት ባልንጀሮቻቸው ድጋፍ ያገኛሉ። (ገላትያ 6:2) በመንፈሳዊ ሥር የሰደዱ ታማኝና የጎለመሱ ክርስቲያኖች እንደ አውሎ ነፋስ ያለ ስደት በሚነሳበት ጊዜም እንኳ አዲሶችን በእምነት ጸንተው እንዲቆሙ ይረዷቸዋል። (ሮሜ 1:11, 12) አዳዲስ ክርስቲያኖች በጎለመሱ ክርስቲያኖች “ጥላ” ሥር ሆነው እድገት ማድረግ ይችላሉ። (ሮሜ 15:1) ከዚህም በላይ የዓለም አቀፉ የክርስቲያን ጉባኤ አባላት የሆኑ ሁሉ በትልልቅ “የጽድቅ ዛፎች” የተመሰሉት ቅቡዓን ቀሪዎች ከሚያቀርቡት ገንቢ መንፈሳዊ ምግብ ጥቅም ያገኛሉ።—ኢሳይያስ 61:3

የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ በኢሳይያስ 65:22 ላይ “የሕዝቤ ዕድሜ፣ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይረዝማል” በማለት ይሖዋ የገባው ቃል በእነርሱ ላይ ሲፈጸም የመመልከት ተስፋ ያላቸው መሆኑ ምንኛ አስደሳች ነው።

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Godo-Foto