በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

አንድ ክርስቲያን በስሜታዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሁኔታ ቢዝል ምን ሊያደርግ ይችላል?

በመጀመሪያ የድካም ስሜት የሚያስከትልብንን ነገር ለይተን ማወቅ ይኖርብናል። ልማዶቻችንንና ያሉንን ንብረቶች አንድ በአንድ መርምረን አላስፈላጊ ሸክም የሚፈጥሩብንን ማስወገድ ጠቃሚ ነው። ሁኔታችንን ግምት ውስጥ በማስገባት ልንደርስባቸው የምንችላቸው ግቦች ማውጣት እንችላለን። መንፈሳዊ ጤንነታችንን መንከባከባችን አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ወደ ይሖዋ አዘውትረን መጸለይና ማሰላሰል ይኖርብናል።—8/15 ገጽ 23-6

የይሖዋ ምሥክሮች 144,000 የሚለውን ቁጥር በምሳሌያዊ ሁኔታ ሳይሆን ቃል በቃል የሚረዱት ለምንድን ነው?

ሐዋርያው ዮሐንስ 144,000 ሰዎች ስለሚገኙበት ስለዚህ ቡድን በራእይ ከተገለጠለት በኋላ “አንድ እንኳ ሊቈጥራቸው የማይችል . . . እጅግ ብዙ ሰዎች” ተመልክቷል። (ራእይ 7:4, 9 የ1954 ትርጉም) 144,000 የሚለው ቁጥር ምሳሌያዊ ቢሆን ኖሮ በሁለቱ ቁጥሮች መካከል ያለው ንጽጽር ትርጉም አይኖረውም ነበር። ኢየሱስም ከእርሱ ጋር ስለሚገዙት ሰዎች ሲናገር “ታናሽ መንጋ” በማለት ጠርቷቸዋል። (ሉቃስ 12:32 የ1954 ትርጉም)—9/1 ገጽ 30

እስራኤላውያን ደሙ ሳይፈስስ የሞተ እንስሳን ለውጭ አገር ዜጋ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ለምንድን ነው?

የአይሁድን እምነት ያልተቀበሉ የውጭ አገር ዜጎችና መጻተኞች በሕጉ ሥር አልነበሩም። በመሆኑም እስራኤላውያን በዚህ መልክ የሞተን እንስሳ ለእነርሱ እንዲሰጡ ወይም እንዲሸጡ ተፈቅዶላቸዋል። (ዘዳግም 14:21) በሌላ በኩል ግን የአይሁድን እምነት የተቀበለ ሰው በሕጉ ሥር ስለነበር ደሙ ሳይፈስ የሞተን እንስሳ ሥጋ መብላት አይችልም ነበር። (ዘሌዋውያን 17:10)—9/15 ገጽ 26

ሰዎች ተፈጥሮን እንደሚኮርጁ የትኛው ምሳሌ ያሳየናል? ይህስ የክርስቲያኖችን ትኩረት የሚስበው ለምንድን ነው?

ዊልበር እና ኦርቪል የሚባሉ ወንድማማቾች ትልልቅ አሞራዎች እንዴት እንደሚበሩ በማጥናት አውሮፕላን ፈልስፈዋል። ክርስቲያኖች የሰው ልጆች ተፈጥሮን እየኮረጁ የሚሠሯቸውን ነገሮች ሲመለከቱ ለፈጣሪ ክብር እንዲሰጡ ሊያነሳሳቸው ይገባል።—10/1 ገጽ 9

በ2 ቆሮንቶስ 12:2-4 ላይ በራእይ ወደ ገነት እንደተነጠቀ የተገለጸው ማን ነው?

ጳውሎስ ይህን የተናገረው ሐዋርያነቱን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሌላ በየትም ቦታ ላይ እንዲህ ያለ ሁኔታ ስላጋጠመው ሰው ስለማይናገርና ስለዚህ ጉዳይ የተናገረው ጳውሎስ ብቻ ስለሆነ ይህን ራእይ የተመለከተው ራሱ ጳውሎስ መሆን አለበት።—10/15 ገጽ 8

ኢየሱስ በአምላክ የተሾመ መሪ ሆኖ ለመግዛት ብቁ የሚያደርጉት የትኞቹ ባሕርያቱ ናቸው?

ሐቀኛና መልካም ምግባር ያለው ስለነበር ከነቀፋ የጸዳ ሕይወት ኖሯል። ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ለአምላክ ሰጥቶ ነበር። ለሰዎች በጥልቅ ያስብ የነበረ ከመሆኑም በላይ ለሥራ አይለግምም።—11/1 ገጽ 6-7

በሺው ዓመት ግዛት ወቅት አጋንንት የት ይሆናሉ?

በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት ከሰይጣን ጋር በጥልቁ ውስጥ ታስረው ይቆያሉ እንድንል የሚያደርጉ አሳማኝ ምክንያቶች አሉ። (ራእይ 20:1-3) በዘፍጥረት 3:15 ላይ የእባቡ ራስ እንደሚቀጠቀጥ ትንቢት የተነገረ ሲሆን ይህ በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት በጥልቁ ውስጥ መታሰሩንም ይጨምራል። የእባቡ ዘር ክፉ መላእክትን ወይም አጋንንትን ያቀፈ ነው። ክፉ መናፍስት ጥልቁን በጣም መፍራታቸው ወደፊት በዚህ ቦታ እንደሚታሰሩ የሚያውቁ መሆናቸውን ያመለክታል። (ሉቃስ 8:31)—11/15 ገጽ 30-1

አንድ ሰው እስኪሰክር ድረስ የሚጠጣ ባይሆንም በአልኮል መጠጥ አወሳሰዱ ረገድ ጠንቃቃ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?

አንዳንዶች ብዙ ጠጥተውም እንኳ የስካር ምልክት ላይታይባቸው ይችላል። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነት ልማድ ያለው ሰው ይዋል ይደር እንጂ የአልኮል ጥገኛና ‘ሱሰኛ’ መሆኑ አይቀርም። (ቲቶ 2:3) ኢየሱስ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም . . . ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ” በማለት አሳስቧል። (ሉቃስ 21:34, 35) አንድ ሰው ስካር የሚባል ደረጃ ላይ ባይደርስም እንኳ የአልኮል መጠጥ በመጠጣቱ ምክንያት በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሁኔታ ሊደብተውና ሊዝል ይችላል።—12/1 ገጽ 19-21