በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

መዝሙር 72:12 ላይ በተገለጸው ትንቢት መሠረት ኢየሱስ ‘ችግረኛውን የሚታደገው’ እንዴት ነው?

በግዛቱ ወቅት ሙስና ስለማይኖር ለሁሉም ፍትሕ ይሰፍናል። አብዛኛውን ጊዜ ድህነትን የሚያስከትለው ጦርነት ነው፤ ክርስቶስ ግን ፍጹም ሰላም ያሰፍናል። ለሰዎች ይራራል፤ እንዲሁም ሁሉም ሰው አንድነት እንዲኖረውና ለሰው ልጆች በቂ ምግብ እንዲኖር ያደርጋል። (መዝሙር 72:4-16)—5/1 ገጽ 7

• ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን “በድፍረት” የመናገር ችሎታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞቴዎስ 3:13፤ ፊልሞና 8፤ ዕብራውያን 4:16 NW)

ለሌሎች ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በቅንዓት ስንሰብክ፣ በተገቢ ጊዜ ውጤታማ ምክር ስንሰጥና ስናስተምር እንዲሁም አምላክ ጸሎቶቻችንን ሰምቶ እንደሚመልስልን እርግጠኞች በመሆን ያለምንም ገደብ የልባችንን አውጥተን ስንጸልይ በድፍረት የመናገር ችሎታ እንዳለን እናሳያለን።—5/15 ገጽ 14-16

• በሕጉ ውስጥ፣ ከፆታ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንዳንድ ተፈጥሯዊ ነገሮች ሰውን ‘እንደሚያረክሱ’ የተገለጸው ለምንድን ነው?

ሕዝቡ በወንድ ዘር መፍሰስ፣ በወር አበባና ልጅ በመውለድ ምክንያት ሊረክስ እንደሚችል ሕጉ ይናገራል፤ ይህ የሆነበት ምክንያት ጤናማና ንጹሕ የአኗኗር ዘይቤ እንዲከተል ለማስቻል ነው። በተጨማሪም የደምን ቅድስና እንዲሁም ደም ለኃጢአት ሥርየት አስፈላጊ እንደሆነ ለሕዝቡ በሚገባ ለማስገንዘብ ነው።—6/1 ገጽ 31

• አንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን ከፈለገ የመዝሙርን መጽሐፍ ማንበቡ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

የመዝሙር ጸሐፊዎች፣ አንድ ሰው ከአምላክ ጋር ያለው ጥሩ ዝምድና ደስታ ሊያስገኝለት እንደሚችል እርግጠኞች ነበሩ። (መዝሙር 112:1) ከሰዎች ጋር የመሠረትነው ማንኛውም ዝምድናም ሆነ ያለን ቁሳዊ ንብረት አሊያም ያገኘነው ስኬት “እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ” ከሚያገኘው ደስታ ጋር አይወዳደርም። (መዝሙር 144:15)—6/15 ገጽ 12

• የጥንቶቹ እስራኤላውያን ከአምላክ ጋር ምን ልዩ ዝምድና መሥርተው ነበር?

ይሖዋ በ1513 ከክርስቶስ ልደት በፊት እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር አዲስ ወዳጅነት እንዲመሠርቱና ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ። (ዘፀአት 19:5, 6፤ 24:7) ከዚያን ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን አምላክ ከመረጠውና ለእርሱ ከተወሰነ ብሔር የተወለዱ ቢሆኑም እንኳ እያንዳንዱ ግለሰብ አምላክን ለማገልገል የራሱን ምርጫ ማድረግ ነበረበት።—7/1 ገጽ 21-22

• ማንኛውንም ነገር ‘ሳናጉረመርም’ ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? (ፊልጵስዩስ 2:14)

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ማጉረምረም በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጉዳት እንዳስከተለ ያሳያሉ። በዛሬው ጊዜም ማጉረምረም መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል መገንዘብ አለብን። ፍጽምና የሌላቸው የሰው ልጆች የማጉረምረም ዝንባሌ ስላላቸው የዚህ ዓይነቱ መንፈስ ይታይብን እንደሆነ ለማወቅ ራሳችንን መመርመርና ለማስወገድ ንቁ መሆን ይኖርብናል።—7/15 ገጽ 16-17

በምሳሌ 8:22-31 ላይ የተገለጸው ጥበብ በጥቅሉ የጥበብ ባሕርይን እንደማያመለክት እንዴት እናውቃለን?

እዚህ ላይ የተጠቀሰው ጥበብ የይሖዋ ተግባሮች መጀመሪያ ‘መደረጉ’ ማለትም መፈጠሩ ተገልጿል። ይሖዋ አምላክ መጀመሪያ የሌለው ከመሆኑም በላይ ሁልጊዜ ጥበበኛ ነው። የይሖዋ ጥበብ የተፈጠረ አይደለም። በምሳሌ 8:22-31 ላይ የተገለጸው ጥበብ በአምላክ ዘንድ “ዋና ባለሙያ” የነበረ ሲሆን ይህ ደግሞ ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ ሆኖ የተወለደውንና በፍጥረት ወቅት ከይሖዋ ጋር ተቀራርቦ ይሠራ የነበረውን መንፈሳዊ ፍጡር ያመለክታል። (ቈላስይስ 1:17፤ ራእይ 3:14 የ1954 ትርጉም)—8/1 ገጽ 31